
አማራዎች በተገደሉባቸው ቀናቶች የተሰሙ ሰበር ዜናዎች….?!?

አሳዬ ደርቤ
➺16 ዐማራዎች ወለጋ ሆሮጉድሩ ውስጥ የተገደሉ ቀን… ‹‹ወ/ሮ ኬርያ ተያዘች›› አሉን፡፡
➺መተከል ላይ 261 ንጹሐን ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ እለት…. የደንቢዶሎ ነዋሪዎች ዱላ ይዘው ኦነግ ሸኔን ጫካ ውስጥ ሲፈልጉ መዋላቸውን እና በርካታ የትሕነግ መኮንኖች መያዛቸውን የሚገልጽ ዜና ቀረበልን፡፡
➺ኢሰማኮ በቤኒሻንጉል ክልል ‹‹ከመቶ የሚበልጡ ንጹሐን መገደላቸውን እና ከጥቃቱ በፊት መከላከያ ሠራዊቱ እንዲወጣ መደረጉን›› የገለጸ ቀን….. ‹‹ጃል መሮ ተገድሏል›› የሚል ሰበር ዜና ተነገረን፡፡
➺ኮንሶ ላይ 66 ዜጎች መገደላቸው የተሰማ እለት…. ‹‹ደብረ ጽዮን ተደመሰሰ›› የሚል የሐሰት ዜና ለቀቁብን፡፡
➺ሆሮ ጉድሩ ላይ 54 ንጹሐን ተጨፍጭፈው ያደሩ እለት…. በአል-ነጃሺ መስጂድ ላይ ጉዳት መድረሱን ከሚገልጽ ፎቶ ጋር እነ ሴኮ ቱሬ መደምሰሳቸውን ሰማን፡፡
➺ኢሰመኮ ‹‹መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር›› የሚል መግለጫውን ያወጣ እለት …
በርካታ የትሕነግ ኮሎኔሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አበሰሩን፡፡
➺በሁለት ቀን ውስጥ መተከል ላይ ከ160 በላይ ንጹሐን የተጨፈጨፉ እለት ‹‹እነ አባይ ጸሐዬ ተደመሰሱ›› የሚል ሰበር ዜና ተነገረን፡፡
ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
መተከል፣ ወለጋ- በደረሰ ጥቃት፤ እንደ ፋሲካ በግ
አማራ ሲታረድ- ባደረበት ማግሥት፤ መረጃው ሲወጣ- ፎቷቸው ሲለቀቅ፤ ፍትሕን ተውና
ሞቱን የሚያስረሳ- ሰበር ዜና ጠብቅ፡፡
ይህን ሁኔታ የተከታተለው ዶ/ር ሰማህኝ ጋሹም ይህን ብሏል
በእያንዳንዷ የአብይ ሰበር ዜና ውስጥ በመቶ ሺ ዎች የሚቆጠር የአማራ የታፈነ የዋይታ ድምጽ አለ…!!