>
5:26 pm - Tuesday September 15, 3125

ኮስተር ብሎ ለመታገል በአማራ ላይ የተጋረጠውን አደጋና መራሩን እውነት መጋፈጥ ያስፈልጋል...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ኮስተር ብሎ ለመታገል በአማራ ላይ የተጋረጠውን አደጋና መራሩን እውነት መጋፈጥ ያስፈልጋል…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የመተከሉ ፍጅት ዋናው ተጠያቂ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስፈጻሚው ዐቢይ አሕመድ ቢሆንም ፍጅቱ ያለ ከልካይ በየለቱ እንዲቀጥል ያደረገው ግን ቆሞ የሚሄደውና ከጭፍጨፋ የተረፈው በማንነቴ ተጠቃሁ ብሎ የሚጮህ፤ ባንድ ወር ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ ድኃ እናቶችና ሕጻናት በማንነታቸው ምክንያት በጅምላ ሲጨፈጨፉና ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ድኆች ከቀያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ሲጣሉ ደም የሚያስተፋ ቁጣ የሚያሰማ፤ ንጹሐን በተኙበት ተጨፍጭፈው እንደ ቆሻሻ በግሬደር ተዝቀው በጅምላ ሲቀበሩ ስርዓት ተፋለሰ ብሎ የሚበሳጭ  ብሔርተኛ ነን የሚሉትን ጨምሮ የአማራ ድርጅት  ባለመኖሩ ነው።
ብሔርተኛ ነን የሚሉ የሌሎች ነገዶችን ድርጅቶች ያየን እንደሆነ “ብሔራችን” ከሚሉት ማኅበረሰብ ውስጥ አንድ ሰው እንኳን ቢጠቃ የማንንም ፍቃድ ሳይጠይቁ ደም የሚያስተፋ ቁጣ በማሰማት በቶሎ ምላሽ ይሰጣሉ፤ ቁጣቸውም አገዛዙን ውድ ዋጋ ስለሚያስከፍለው ጥቃቱ ወዲያው ይቆማል። በየቀኑ ተባብሶ የቀጠለው የመተከልና የወለጋ አማራ ጅምላ ጭፍጨፋ የሚያረጋግጥልን ነገር ቢኖር “የአማራ ብሔርተኛ” ነን ብለው የተደራጁት የአማራ ስብስቦች [በመንግሥትነት ተሰይመናል የሚሉትንና በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉት መጭሮ] እንደሚሉት የአማራ ብሔርተኛ አለመሆናቸውን ነው። አማራ ነበር፤ አለ፤ ይኖራል፤  በአማራ ስም የተደራጁት ቡድኖች ብሔርተኛ ነን ቢሉም  የአማራ ብሔርተኛ ድርጅት ግን የለም።
አገር፣ መንግሥትና የሚደርስለት ድርጅት የሌለው የተናቀው፣ የተበደለውና ተለይቶ  በየሰርኩ እየተፈጀ ያለው የአማራ ሕዝብ የመከራ ጽዋው ሞልቶ እየፈሰሰ በመሆኑ በቅርቡ ለአመጽ መነሳቱ አይቀሬ ነው። የአመጽ ምዕራፍ መክፈቻ እንዲሆንለትም የሚከተለውን የአባቶቹን እንጉርጉሮ ያሰማል፤
ታርሶም ተሸምቶም ይበላል እንጀራ፤
እንዴት አለሽ ጥቃት የሞት ባልንጀራ!
አማራ ፍጅቱን፣ ጥቃቱንና ውርደቱን ለመሸከም የሚችልበት ትከሻው እየተሰበረበት ነው። ውርደቱን የሚያሰተናግድበት የታጋሽነት ኅሌናው የተሟጠጠጠውና  የትዕግስቱ ከረጢት ሞልቶ እየተተረተረ በመሆኑ ትእግስቱን ወደ ንዴት ነበልባልና ደም ወደሚያስተፋ ቁጣ ለውጦ በቅርቡ ለአመጽ ይነሳል። ያን ጊዜ የሚያቆመውና የሚገታው ኃይል አይኖርም። ወያኔ ይህንን ኃይል አይቶታል።
ፍትሕና ርትዕ በጎደልበት፤ አማራን መጅምላ ጨፍጭፎ በጅምላ መቅበር አዲሱ የኦሮሙማ ፖለቲካ በሆነበት አገር ውስጥ አንድ ቋጫ ዕምባ ቢያፈስሱት አዛኝና ሰሚ ስለሌለ አማራው ለበደሉ ሰሚ ይኖራል በማለት እየተጠቃ የውርደት ኑሮ እየገፋ መኖር ስለሌለበት ካጋጠመው ብሔራዊ ሐዘን ሰልስት በኋላ አማራን የግፍ ሁሉ መሞከሪያ ያደረጉት ጠላቶቹና እንደራሴያቸው በኩል ተጨማሪ ፍጅትና ውርደት ይዘውለት እስኪመጡ ድረስ ከሚጠብቅ  በየእለቱ በጅምላ ከሚጨፈጨፍበት የምድራሲ ሲዖል ኑሮ ኑሮ ለመገላገል  “ቻይ ካመረረ ፤ በግ ከበረረ” እንደሚባለው ተገማች ቻይነቱን ወደ ቁጣ በመቀየር መተማመን ፈጥሮ በአንድነት ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣውን ማሰማት አለበት። የአማራን የሰክር የጅምላ ፍጅት ለማስቆም ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
Filed in: Amharic