>

አበሻ የማይለምደው የለም:-  የወገንን እልቂት የዘር ጭፍጨፋንም ለምዶት ቁጭ አለ...?!? (መርእድ እስጢፋኖስ)

አበሻ የማይለምደው የለም:-

 የወገንን እልቂት የዘር ጭፍጨፋንም ለምዶት ቁጭ አለ…?!?
መርእድ እስጢፋኖስ

 

*…. የህዝብ ልጆች ነን የምትሉትስ አርቲስቶች ዘፋኞች ሰአሊዎች የት አላችሁ? የሽገር ፓርክ ግብዣ ላይ ዘፈን ካልዘፈንን ብላችሁ ስታለቅሱ የነበራችሁ የታላችሁ? “ሰውየው ” እያላችሁ መፅሀፍ ያሳተማችሁ የት አላችሁ?።
ድምፅ ያላችሁ አትሌቶቻችን የት አላችሁ።?
ምናልባት ከተጨፈጨፉት መካከል ቤተሰብ ቢሆኑ ዝም ትሉ ነበር? የት አላችሁ የኢትዮጵያ ሙሁራን ? የአዲስ አበባ ሰዎችስ? ነብሰ በላዎቹ …..ቤንሻንጉል ጉምዝ ብቻ የሚቀሩ መሰሏችሁ? ጉራፈርዳ የሚቀሩ መሰሏቹሁ? መቆሚያቸው ኮንሶ ላይ ብቻ መሰላችሁ? አዎ አዲስ አበባ በር ላይ ቆመው እያንኳኩ ነው።አዎ በሩንም ሰብረው ይገባሉ። እራት ግን አበረዋችሁ አይበሉም። ምክንያቱም እናንተ ራሳችሁ ናችሁና እራታቸው።


ባለፈው 48 ሰአታት ብቻ በቤንሻንጉል ጉምዝ በመተከል እና በኮንሶ ከ300 ሰው በላይ አልቋል።በውጭ ሚድያዎች ከፈተኛ ሽፋን አግኝቷል።ከፍተኛ ድንጋጤም ፈጥሯል።
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ውዴት እየሄደች ነው ብለው እየጠየቁ ያሉ ብዙ ናቸው። በተለይ ደግሞ ተመሳሳይ ጭፍጨፋና ግድያ እንዳይኖር የሚሆንበት መንገድ አለ ወይስ በየሳምንቱ 300 መቶ ሰዎች እልቂት መስማት ልንቀጥል ነው የሚሉም አሉ።
ለሁለቱም ግን መልስ የለም።
የዛሬ 3 ሳምንት 260 እናቶች ህፃናቶች አባቶች ወጣት ሴቶች እና ውንዶች ባለቁበት ወቅት አለምን እንዲሁ ያስደነገጠ ሁኔታነበረ። መንግስት እርምጃ የወስዳል ነገሩ መፍትሄ ያገኛል ተብሎ ነበረ። በመሆኑም የመተከል ዞን በጠ/ሚ አብይ አህመድ ጥበቃ ስር ሆነ። በቃ ከዚህ በኋላ ይህ በፍፁም አይደገምም ተብሎ ተደመደመ።
ግን ጭፍጨፋው ቀጠለ። ያንኛው እየረሳን ይኽኛውን እያወራን። ቀን መጥቶ ቀን በሄደ ቁጥር ሰው እየታረደ ቀጠለ። 20ሰው… 30ሰው…50 ሰው በየቀኑ እልቂት እየሰማን ሞትን ተለማመድን ሄድን።
ሰው ግፍን እና ግድያን እልቂትን እንዴት ይለምዳል?
ይለምዳል… ሰው የማይለምደው ነገር የለም። በተለይ ኢትዮጵያዊ የማይለምደው የለም።ሞትን እንኳ…. ግፍን እንኳ… ጭፍጨፋን እንኳ ቢሆን ይለምዳል።ብቻ እንዴት አርጎ ማለማመድ እንደሚቻል ማወቁ ላይ ነው ቁምነገሩ ።የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት ደግሞ ለዚህ የተካነ ነው።
ዶ/ር የአብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከላይ እንደተጠቀሰው ትንሽ በትንሽ መሞት ጀመርን ።ግፍን እና ግድያን በየቀኑ ትንሽ በትንሽ መለማመድ ጀመርን።
አሁን ለአንድ ኢትዮጵያዊ ጥዋት ተነስቶ በማህበርዊ ሚዲያም ይሁን በአለም አቀፍ ሚዲያ ሰዎች የተጨፈጨፉ ቢባል ስንት ?ማለት ጀምሯል።ከ20-50ሰዎች ከሆነ ምን አላት? የለመድነው ነው። ስለሆነ ኮታ መጨመር ጀመርን።
80-100 ሰው ተጨፈጨፋ 2019 አ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ መስማት ጀመርን። አሁንም ትንሽ ደነገጥን ግን ቀጠለ ።ትንሽ ተጨነቅን ግን ቀጠልን።
2020 አ.ም ገባን በቃ መቶ ቁጥር ሆነ ።200 መቶ እና ከዚያ በላይ ደግሞ አዲሱ የጭፍጨፋ ቁጥር ሆነ።ዛሬ ደግሞ በከፍተኛ እድገት አሳይተን 300 ሰው በቀን ገባ።
በቃ ሞትን ለመድነው።ግፍን ለመድነው። እንደሰው መቃወም ራሱ ትተን ግፍን እንደግፍ መጥላት ትተን እለታዊ ዜና ሆነ በቃ። the new normal.
በነዚህ ሁሉ ሂደቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ ሬድዮ ከጥዋት ጀምሮ እስከማታ የሚመግቡን የኢትዮጵያን ልማት ነው።
የኢትዮጵያን እድገት ነው። የኢትዮጵያን በኢኮኖሚ አድጋ ….አድጋ ከ30 አመት በኋላ ከአለም ሁለተኛ እንደምትሆን ነው።delusional!
ይሄ እንግዲህ ሞትን ለምደነዋል ።እልቂትን ለምደነዋል ።ያል ለመድነው የኢኮኖሚ እድገትን ስለሆነ መወራት ያለበት ስለሽገር ፓርክ ፥ስለ እንጦጦ ፓርክ ሆነ። ሌት ተቀን ማውራት የተያያዙት….ኢቲቪ።
ታላቁ መሪያችን።አስተዋዩ መሪያችን።ጥበበኛው መሪያችን።ልክ “መለስ ዜናዊን “ስናሞካሽበት በነበረው ቃላት” ቢያንስ ቃሉን እንኳ ዘመን ሄዶ ዘመን ሲመጣ መቀየር አልቻሉም ።ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ።
እኔ የምለው እነዚህ የማድነቂያ ቃሎች ቋሚ ተቀጣሪ ናቸው እንዴ? በኢትዮጵያ ማስሚዲያ ውስጥ።
አዎ በዚህ በያዝነው 48 ሰአት ውስጥ ስለመተከል እልቂት ምንም የመንግስት ሚዲያዎች አለመዘገባቸው መንግስትን የጠቀሙት መስሏቸዋል።ነገር ግን የመንግስት እጅ አለበት እያሉ በጥርጣሬ የአውሮፓ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።ለምን? መንግስት ግድ ስላልሰጠው ።በሌላ መልኩ ለምን በጠራራ ፀሀይ የተፈፀመን የዘር ማጥፋት ሊደብቅ ቻለ በሚል። back fire ይሉታል ፈረንጆቹ።ማምለጫ መንገድ ብለህ ያደረከው ራስህን ሊበላህ ይመጣል እንደሚሉት ነው(coming to hunt you)።
ልክ እንደትግራዩ ጦርነት ማለት ነው።መንግስት በትግራዩ ጦርነት ህግን የማስከበር ሙሉ መብት አለኝ አለ። መንግስት አለም አቀፍም ይሁን የአገር ውስጥ ኮምንኬሽን እንዳይኖር አደረገ።ምንም አይነት መርጃ እንዳይወጣ አደረገ። የአውሮፓ መንግስታት “ኢትዮጵያ መንግስት የደበቀው ነገር አለ ሲሉ ሰንብተዋል።አሁን ግን ባልተረጋገጠ ጦር ወንጀለኝነት እየተከሰሰ ነው።ይሄ ሁሉ ከየት የመጣ ? ። በመንግስት መረጃን አፈና እንደስትራቲጂ በመያዙ።በመንግስት የመሸፋፈን ያመጣው ጣጣ ነው።ገና ዋጋ ያስከፍል ይሆናል። እድሜ ከሰጠን ይህን ለማየት ሩቅ አይደለም።
ከዚህ ድርጊቱ ያልተማረው መንግስትና የመንግስት ሚዲያ በመተከል በቤንሻንጉል በኮንሶ ያለውን በመደበቅ ላይ ተሰማርቷል ይሄ ግን አይጠቅምም።ሊዘግቡት ከቶውንም አይፈልጉም።ለምን?መንግስትን የጠቀሙት ስለመሰላቸው።ወይም የመንግስትን ገፅታን የሚያበላሽ ስለመሰላቸው።
ስለውደፊቱ የሽገር ገበታ ማውራት ሊመጣ ስላለው የጠ/ሚ አብይ የእራት ግብዣ ፕሮግራግራም ማውራት። ስለኮይሻ ፥ጎርጎራ፥ስለ ወንጪ ፓርክ ማውራት ብቻ የሚጠቅም ስለመሰላቸው።
ለመሆኑ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን እና ሬድዮ መንግስት ሳይሆን የሚከፍላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን የሚያውቁት ይሆን? ትላንት የተጨፈጨፉት ገብሬዎች ናቸው እኮ የዛሬ” ምሳ መብያቸውን” የከፈሉት።
ትላንት የሞቱት ናቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያ ሰራተኞች ወርሀዊ ደመውዝ የሚከፍሉት።እና ሞያና ባለሞያን እንተወው።የጋዜጠኝነት ሞያንም እንርሳው።እንዴት ያበላችሁና ያጠጣችሁ እሱ ሞቶ የሚኖራችሁ ወገናችሁ በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ እንደሰው እንዴት ሳይሰማችሁ ቀረ? እንዴት ሳያማችሁ ቀረ?እንዴት ይሄን አልቀበለውም የማለት ሰውነት አጣችሁ? ለሚያኖራችሁ ህዝብ ድምፅ መሆን አቃታችሁ? እናንተ ላይ ስላልደረሰ?
የህዝብ ልጆች ነን የምትሉትስ አርቲስቶች ዘፋኞች ሰአሊዎች የት አላችሁ? የሽገር ፓርክ ግብዣ ላይ ዘፈን ካልዘፈንን ብላችሁ ስታለቅሱ የነበራችሁ የታላችሁ? “ሰውየው ” እያላችሁ መፅሀፍ ያሳተማችሁ የት አላችሁ?።
ድምፅ ያላችሁ አትሌቶቻችን የት አላችሁ።?
ምናልባት ከተጨፈጨፉት መካከል ቤተሰብ ቢሆኑ ዝም ትሉ ነበር?
የት አላችሁ የኢትዮጵያ ሙሁራን ?
የአዲስ አበባ ሰዎችስ? ነብሰ በላዎቹ …..ቤንሻንጉል ጉምዝ ብቻ የሚቀሩ መሰሏችሁ? ጉራፈርዳ የሚቀሩ መሰሏቹሁ?
መቆሚያቸው ኮንሶ ላይ ብቻ መሰላችሁ? አዎ አዲስ አበባ በር ላይ ቆመው እያንኳኩ ነው።አዎ በሩንም ሰብረው ይገባሉ። እራት ግን አበረዋችሁ አይበሉም።ምክንያቱም እናንተ ራሳችሁ ናችሁና እራታቸው።
ሩቅ አይደለም በመላ አዲስ አበባ ቅርስ አፍርሰው ኦሮሙማን እየተከሉ ነው።አዲስ አበቤዎች እኛ ጋር አልደረሰም ብላችሁ ይሆናል።
ጭንቅለታችሁ ድራጎኑ ውስዶታል የቀረው ጭራችሁ ነው።ኢሎሄ ከድራጎኑ እንደምን ታስጥለናለህ? እንፀልያለን …!
Filed in: Amharic