>

ሱዳን ኢትዮጵያን የወረረችባቸው 10 ምክንያቶች (መስፍን ሙሉጌታ)

ሱዳን ኢትዮጵያን የወረረችባቸው 10 ምክንያቶች

መስፍን ሙሉጌታ


1) ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ስለታረቀች የፖርት ሱዳን ደረቅ ወደብ የሚያከራዩበት ጥቅም ስለሚያሳጣቸው። አቅም አጥታ ነው እንጂ ደግሞም ትንሽ ቀምሳ ነው እንጂ ጅቡቲም የወደብ ኪራይ ስለሚቀርባት በአፋር በኩል ሰላም ልታሳጣን ተፍጨርጭራ ነበረ:፣
2) የሱዳን ድንበር ጠባቂ ወታደሮቻችን ለአስኳይ ግዳጅ ወደ ትግራይ ስለተሰማሩ፣
3) ፕ/ት ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባና እኛ ከተነካን በኢትዮጵያ ላይ ፍላጎት ያላቸው አካላት ይገባሉ ብሎ ስዩም መስፍን በተናገረው መሰረት ህዋሀት ከሱዳንና ከግብፅ ጋር በጌታቸው ረዳ በኩል ተስማምተው ነበረ። በዚህ ስራው ህዋሀት በግብፅ  በኩል 9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ አግኝቶ ነበረ ይባላል።
4) የሱዳን የሽግግር ዘብ የሚሊተሪ ዘርፍ ሀላፊው ጄኔራልና ሲቪል መንግስቱ እንዳልተስማሙ የሚያስመስሉበት ምክንያት ታክቲክ ነው።   ባይሆን ኖሮ ሚሊተሪው መፈንቅለ መንግስት አያረግም ነበረ?
5) አሳማው ትራምፕ ለሱዳን መንግስት ደውሎ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ለምትወስዱት እርምጃ የኛ ድጋፍ አይለያችሁም ስላላቸው የልብ ልብ ተሰምቷቸው፣
6) ሱዳንን ተደግፋ እየወጋችን ያለች ግብፅ ነች። ከአባይ በቱቦ የምታገኘው የውሀ ድርሻ  ማለትም የኤል ሰላም የትቦ ውሀ  ይቀንስብኛል ብላ ስለምትሰጋ እስራኤልም ከግብፅ፣ ከሱደንና ከትራምፕ ጀርባ ስላለች፣
7) ከትግራይ ወንጀል ሰርተው የኮበለሉ የሳምሪ አባላት በሱዳን ካምፕ ስላሉ ጦርነት ከተጀመረ በቅድሚያ እነሱን ለማገዶነት ልታቀርብ በማሰብ። በተመሳሳይ ብዙ የጉሙዝ ማህበረሰብ በሱዳን ስላለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተልኮ ጦርነት እያደረጉ ናቸው። እኛ ግን የዘር ማጥፋት ብቻ አድርገን ነው ያየነው። በቤኒሻንጉል ክልል ጦርነት ውስጥ ነን በዚህ ደረጃ ነው መነገር ያለበት።
8) ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ ተዳክማለች በዚህ ሰዓት ሱዳን የበላይነት ወስዳ የፈለገችውን ማስፈፀም ትችላለች ብላ የተሳሳተ ግምት በመውሰዷ። ሱዳንም የውስጥ ጉዳይ እንዳላት  ዘንግተዋል።
9) ኢትዮጵያን እንደ ሊቢያ ለማፈራረስና የአረብ ሊግ አባል ለማድረግ  በቀጠናው ረጅም ጊዜ የቆየ ትልም በመኖሩ፣ እንደ ኦነግ ያሉ አማፅያንን እያስታጠቁ ሰላም ሲነሱን በሞቆየታቸውና
10) ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በሙሉ አቅሙ ስራ ስታስጀምር ግድቡ በራሱ እንደ ጦር መሳሪያ ይሆናል የሚል ትንተና ስላላቸው። ኢትዮጵያ ሀያል ሀገር ትሆናለች። በቅርቡ የባህር ሀይል አደራጅታለች። ከሩሲያ ሁለት ሚሳኤሎች ገዝታለች። የኒውክለር ባለቤት ለመሆን ስላቀደችና የሳቴላይቶች ባለቤት ስለሆነች ኢትዮጵያን ሳይቃጠል በቅጠል እንታገላት ብለው። የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ ግብፅ ዙሪያችንን ቆፍራ ነበረ። ሆኖም እንዳሰበችው አልቀለላትም። ሶማሊያን፣ ጅቡቲን፣ ሱዳንን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ሀያላን ሀገራትን ደጅ ፀንታ ነበረ።  ኢትዮጵያ በብሄር ስለተበጣጠሰች የእምቧይ ካብ መስላቸው ነበረ። በነፃነት ጉዳይ ኢትዮጵያውያን የምንናደፉ ንቦች ግን የማንቸኩል መሆናችንን አልተረዱም። ይህ ሁሉ መንፈራገጥ በሚቀጥለው ክረምት ግድባችንን ውሀ እስክንሞላ ነው። ከዚያ በኋላ ከፈለግን ውሀ እንደ ነዳጅ እንሸጥላቸዋለን። ግን እንደዛ ለማድረግ አላቀድንም በጋራ እንጠቀም ነው ያልነው።  ከፈለግን ህዝባችን በመስኖ ውሀ አትክልትና ፍራፍሬ አምርተን እናጠግባለን 14 ሚሊዮን ህዝብ ያላት እስራኤል 114 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገርን የምትረዳበት ምክንያት ማብቃት አለበት። ኢትዮጵያውያን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ነቅተን፣ ልዩነቶቻችን አቆይተን፣ አንድነታችንን አጠንክረን፣ ሀሳብ አዋጥተን ከመከላከያችን ጎን ቆመን ጠላቶቻችን አፍረው ሲመለሱና ኢትዮጵያን ሲማፀኑ ብሎም የዚቺ ድንቅ ሀገራችን ትንሳዔን ለማየት እንጓጓ። ደግሞም ትንሳኤያችን ሩቅ አይደለም።
ድል ለኢትዮጵያ! ሁሌም! 
Filed in: Amharic