>

እስክንድርን ይቅርታ ጠይቁ!!!  (ሂሩት ሀይሉ)

እስክንድርን ይቅርታ ጠይቁ!!! 

ሂሩት ሀይሉ

እውነትን ተሸክሞ ለእውነት የሚሞተው፣ የሀገሩና የህዝቡ ስቃይ የሚያመውና እንቅልፍ የሚነሳው፣ ለእውነት ግምባሩን ሰጥቶ ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ የሚጮህ፣ ለድምፅ አልባዎች ድምፅ በመሆን እንደፈሪዎች አገር ጥሎ ሳይፈረጥጥ፣ እዛው ከአምባገነን ገዢዎች ፊት ሆኖ ሲታገል፣ ብዙ ዋጋ የከፈለ ሀቀኛና አሁንም በያዘው እውነት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ፣  አዲሳባን የመውረርና የመዋጥ እቅድ ይዞ የተነሳው የኦሮሙማ ፓለቲካ ፣ 5 የኦሮሞ የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በመሆን “አዲስ አበባ” የኛ ናት ብለው አስደንጋጭ መግጫ ካወጡበት ቀን ጀምሮ፣ አዲሳባን ለማዳን ትግሉን ከጀመረበትና እስከታሰረበት እለት ድረስ በአዲሳባ እየተደረገ ያለውን በመረጃ ሁሉ እያጋለጠ ህዝብ እንዲያውቅ ሲያደርግ፣ ጥቅማቸው የተነካባቸውና ትናንት በዲያስፓራው  በየስብሰባው የእስክንድርን ፎቶ እየሸጡና የሱን ስም በመጠቀም ሲነግዱ የነበሩት የፓለቲካ ነጋዴዎች፣ በአንድነት ስም የተደበቁ አስመሳዮች ጋር በጋራ በመተባበር በእስክንድር ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈቱበት፣ እንዲታሰርም ወተወቱ፣ አይምሮውን ያመዋል ብለውም ተሳለቁበት፣ አሾፉበት፣ ዛሬ ከራሳቸው ከመንግስት ባለስልጣናት አዲሳባ ላይ ወረራ መፈፀሙን በይፋ ተናገሩ! እውነት ተደብቃ አትቀርም!
በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት ስም የምታጭበረብሩ ፣ አብራችሁ የዘረፋችሁና ያዘረፋችሁም ጉዳችሁ ይወጣል!
Filed in: Amharic