ወንድወሰን ተክሉ
*….10ቱ ተፈጻሚ የብልጽግና/ኢዜማ አጀንዳዎች፤
*. ..ለመላው ኢትዮጵያዊ ምርጫ ውሳኔ ማለት ምን ማለት ስለመሆኑ፦
• የጀርመኑ ናዚ ሂትለር፣የጣሊያኑ ፋሺስት ሞሶሎኒና የ21ኛው ክፍለ ዘመኑ ናርሲሲቱ የአሜሪካው ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን የመጡት በምርጫ ድምጽ ነው፦
በአሜሪካን 240በላይ ታሪክ ውስጥ የ74ዓመት አዛውንቱን ዶናልድ ትራምፕን የመሰለ እጅግ ራስ ወዳድ ናርሲሲት ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን መጥቶ አያውቅም፡፡ ግን ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዘ በኃላ የፈጸማቸው አሳፋሪ ተግባራቱ በሙሉ በ2016 የምርጫ ዘመቻ ለመፈጸም ቃል ሲገባ የነበረውን ቢሆንም ስልጣን የያዘው ግን በምርጫ መሆኑ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለመምረጥ ከቀረበልን የብልጽግና ፓርቲ ጋር እያነጻጸርን እንድንመለከት በማስፈለጉ ነው ይህንን ንጽጽር ለማቅረብ የተፈለገው፡፡
በጀርመን በተካሄደው የ1932ምርጫ አሸናፊ ሆኖ በ1933 የጀርመን ቻንስለር የሆነው አዶልፍ ሂትለርና እሚመራው የናዚ ፓርቲ ወደ ስልጣን የመጣው በመፈንቅለ መንግስት ወይም እንደ መለስ፣የዩጋንዳው ሙሴቪኒና የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ በትጥቅ ትግል ሳይሆን በምርጫ ነው፡፡ የጣሊያኑን ፋሺስት ሞሶሎኒንም ብንጠቅስ ወደ ስልጣን የመጡበት መንገድ በምርጫ ነው፡፡
ከአዶልፍ ሂትለር እስከ የዘመናችን ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ማን ምን አይነት አጀንዳና አላማ እንዳላቸው ቁልጭ አድርገው ሲገልጹ የነበሩ በመሆናቸው ስልጣን ላይ ከወጡ በኃላ የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ተግባራቶችን በከፊል የህዝቡን ይሁንታን ያገኘ እና ተጠባቂ የሆነ ተግባር ነው እንጂ ያልተጠበቀና ያልተገመተ አዲስ እርምጃን ሲወስዱ አልታየም፡፡
ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሊካሄድ በታቀደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡት ድርጅቶች ውስጥ ከሚያዚያ 2ቀን 2018 ጀምሮ መንበረ ስልጣኑን የያዘው አቢይ አህመድ አሊ መራሹ ብልጽግና እና ኢዜማ ይገኙባቸዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የወቅቱ ገዢ ፓርቲ መሆንና በምርጫው ላይ ተጠባቂ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የመሆኑ ጉዳይ ይህ ድርጅት ከአጋር ተለጣፊ ኢዜማ ድርጅት ጋር ተወዳድሮ አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ ማግኘት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያመላክቱ ነጥቦችን /አጀንዳዊ ተግባራቶችን/እንደሚከተለው አስቀምጫለሁ
• ብልጽግና/ኢዜማን መምረጥ ማለት ምን ማለት ነው????
• 1ኛ-በመላው የአማራ፣የአዲስ አበባ፣የድሬደዋ፣የወላይታ፣የጌዴኦ፣የኮንሶጋሞ ኦሞ ህዝብ ህልውና ላይ የዘር ተኮር ጭፍጨፋን ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 2ኛ- ላለፉት 30ወራት ሀገርን የመራው የህግ የበላይነት ሳይሆን የስልጣን፣የኦነጋዊ አጀንዳን የበላይነትን ያስጠበቀውን መንግስታዊ ፖሊሲንና አጀንዳን ለቀጣዩ አምስት የስልጣን ዘመን በተጠናከረ መልኩ እንዲጧጧፍ ሙሉ በሙሉ ተስማምቶ ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 3ኛ- ላለፉት 30 ወራቶች ውስጥ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል የአማራአገው ተወላጆችንና የክርስትና ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ለይቶና ነጥሎ የማጥፋት ዘመቻን በይበልጥ አሳፋፍቶ ዘርና እምነት ተኮር የማጽዳት ዘመቻውን ሙሉ በሙሉ ግቡን እንዲመታ የሚያስችል ማንዴትን በመስጠት ማጽደቅ ማለት ሲሆን በደቡብ ኮንሶ፣ጌዴኦ ወላይታን የመሰልቀጥን ዘመቻ ተፈጻሚ ለማድረግ ተጨማሪ አምስት የስልጣን ዘመንን መፍቀድና ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 4ኛ-በአዲስ አበባ፣በድሬደዋና በሀረር ከተሞች ላይ የተነሳውን የተስፋፊውን ኦነጋዊ የባለቤትነትን ጥያቄያዊ አጀንዳን ሙሉ በሙሉ ፍትሃዊ አድርጎ በመቀበል ሶስቱን ከተሞች በኦሮሚያ ስር ተሰልቅጠው ህልውናዊ ማንነታቸውን እንዲያጡ ፈቅዶ ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 5ኛ-ላለፉት 30ወራት ውስጥ በሚያሰቅቅ ሁኔታ እየተፈጸመ ያለውን የህዝብና የሀገር ሀብትና ንብረትን እያጋበሱ የመዝረፍን ስራ ህጋዊ አድርጎ ለተጨማሪ አምስት የዘረፋ አመታትን ስልጣንን ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 6ኛ- አዲስ አበባን፣ሀረር ድሬደዋን፣ወላይታ ኮንሶን፣ጋምቤላ ቤኒሻንጉልን፣ጌዴኦ ሰሜን ሸዋንና ወሎ ራያን ሰልቅጦ ለመፍጠር የታቀደውን ታላቂቱን የኦሮሚያ ክልልን በመፍጠር ወደ የኦሮሚያ ፌዴሬሽንነት ደረጃ እንድትደርስ ተጨማሪ አምስት የስልጣን ዘመናትን ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
•7ኛ-በትግራይ እና በአማራ መካከል የማያባራ ጦርነትና ጠላትነት እንዲቀጣጠል መፍቀድና የትግራይም ህዝብ እራሱን በራሱ የሚመራበትን መብትና ስልጣኑን ገፍፎ በማገድ በአቢይ አሻንጉሊት ምስለኔ ህዝቡን ለመድፈቅና ለመርገጥ ተስማምቶ ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 8ኛ-መላው የአማራ ህዝብ እራሱን በራስ የመምራት ተፈጥሮአዊ ስልጣንና መብቱን ነጥቆ በመያዝ የአቢይ አሻንጉሊት በሆኑ ጸረ አማራ ምስለኔዎች (አዴፓ) እጅ ሆኖ እየተረገጠ እየተጨፈጨፈና እየተመዘበረ እንዲገዛ ተስማምቶ ማጽደቅ ማለት ነው
• 9ኛ-የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ስርዓተ ግንባታን ጥረት አምክኖ የዴሞክራሲ ተቋማቱን አሽመድምዶና ሽባ አድርጎ ለአንድ ሰውና ፓርቲ ፍጹማዊ አገዛዝ ምቹ በማድረግ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድ ሰሜን አሜሪካ በማድረግ ዛሬ ሀገረ ኤርትራ ያለችበትን አገዛዝ የተካች ሀገር ለማድረግ ተስማምቶ ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
• 10ኛ-በእነዚህ ስድስቱ አጀንዳዎች ተፈጻሚነት ምክንያት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውና እና ሉዓላዊ ግዛት ፈራርሶ በምትኩም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ አዳዲስ ሀገራትን ለመፍጠር የሚያስችልን ስምምነታዊ ውሳኔን ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
ብልጽግና/ኢዜማን መምረጥ ማለት ከላይ ለቀረቡት አስር አጀንዳዊ ተግባራቶች ተፈጻሚነት ተስማምቶ ማጽደቅ ማለት ነው፡፡
እናም እርስዎ የዚህ ተግባር አካል መሆን ይፈልጋሉ???
******