>

ልክ ስላልሆነ በቃ ልክ አይሆንም...!!! ( አሌክስ አብርሀም)

ልክ ስላልሆነ በቃ ልክ አይሆንም…!!!

አሌክስ አብርሀም
 
♦” ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር ተጠያቂው ለህገወጡ ሰልፍ ቡራኬ የሰጠው መንግስትና ይህን የለየለት ጠብ አጫሪ ድርጊት ለህዝብ ያስተላለፉት ሚዲያዎች ናቸው “

እና ምርጫ ቦርድ  ከትላንት  ወዲያ የተካሄደው ሰልፍ ላይ ለሌሎች ፖርቲዎች የተሰጠውን የ”አሸባሪነት” ስምና ማስፈራሪያ  ልክ ስልጣን የሌለው ህዝብ እንደሚለው “እንዳይለመዳችሁ ዋ” ብሎ አለፈው ማለት ነው ?  ይሄን ማለት የነበረባቸውኮ የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ነበሩ ! “የኮቪድ ስርጭት አስጊ በሆነበት ወቅት እንዲህ አይነት ጥንቃቄ የጎደለው ሰልፍ እንዳይለመዳችሁ ዋ!” ዓይነት ምክር!
ለማንኛውም አብንም ሆነ ባልደራስ ለአገሪቱ የነገ እጣ ፋንታ ሲባል ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት መውሰድ እንዳለባቸው ይሰማኛል! በዚህ ምርጫ በተዛተባቸው ፖርቲዎች አባላት በደጋፊዎቻቸውም ይሁን እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብ ላይ ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር ተጠያቂው ለህገወጡ ሰልፍ ቡራኬ የሰጠው መንግስትና ይህን የለየለት ጠብ አጫሪ ድርጊት ለህዝብ ያስተላለፉት ሚዲያዎች  ይሆናሉ!
ይህ አብንንም ሆነ ባልደራስን የመደገፍ ጉዳይ አይደለም ሁላችንም መብት ላይ  በተለይም ዴሞክራሲያዊ ይሆናል የተባለለት ምርጫ ላይ ከወዲሁ   የተሰነዘረ ህገወጥ ጠብ አጫሪነትን የመቃዎም ነው !! ልክ አይደለም! ስለዚህ በየትኛውም ስልጣን ላይ ያለ ሰው ስላሞካሸው ልክ አይሆንም!!
Filed in: Amharic