>

የመ/አ ኦላና ለሙ የዶ/ር መረራ ጉዲና አቋምን ተከትሎ የተሰማ እጅግ ምስጢራዊ ማንነት ( ወንድወሰን ተክሉ)

“መረራ ጉዲና ፀረ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ኦሮሞም የሆነ ገንዘብ አምላኪ ነው” 
 
* የመ/አ ኦላና ለሙ የዶ/ር መረራ ጉዲና አቋምን ተከትሎ የተሰማ እጅግ ምስጢራዊ ማንነት 
ወንድወሰን ተክሉ

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ሰባት ተፎካካሪ ድርጅቶች የተካፈሉበት ሀገራዊ /ብሄራዊ መግባባት ኮንፍረንስ ላይ የዶ/ር መረራን ንግግር ያዳመጠው ወዳጄ የቀድሞ የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ መስራችና የኢብሶ ድርጅት መሪ የነበረው የመቶ አለቃ ኦላና ለሙ “መረራ ጉዲና በተጠናወተው የገንዘብ ፍቅር የሚንቀሳቀስ ፀረ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ፀረ ኦሮሞም የሆነ ገንዘብ አምላኪ ነው ” ሲል አስደመመኝ:: እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ? ምን ማስረጃስ አለህ?
አንተስ ከዶ/ር መረራ ጋር በአካል ተገናኝተህ ታውቃለህ?? ተገናኝተህውስ ከሆነ ከአንደበቱ የሰማህው ነገር አለ ? ምንድነውስ ? ለሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎቼ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ከጄ/ል ዊንጌት ትምህርት ቤት ጀምሮ ተሳትፎ በማድረግ እድሜውን የሰዋው የመ/አ ኦላና ለሙ አስደናቂ Revelation በዶ/ር መረራ ጉዳይ በፅሞና አጫውቶኛልና እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ::
ስዊድን ስቶክሆልም 2001 – የዶ/ር መረራ እና የሻእቢያ ምስጢራዊ ግንኙነትና ለስለላ መመልመል መረራ ጉዲና በ2001 (አመተ ምህረቱ በሙሉ እንደ ኤሮፓዊያን አቆጣጠር ነው) ላይ በሆላንድ የPHD ትምህርቱን እየተማረ በነበረበት ወቅት ስዊዲን ስቶክሆልም የሚኖር የአምቦ ተወላጅ የሆነና የድርጅታችን ኢብሶ አባል የነበረ ፕ/ር ግርማ ገብረሰንበት ወደ ስዊዲን እንዲመጠ ጥሪ ተላለፈለት። የጥሪውም ዋና አላማ መረራ ጉዲናን ከኤርትራው ተወካይ ኮ/ል ጣእመ ጋር ለማስተወወቅ ነበር። ኮ/ል ጣእመን እኔ በኢብሶ መሪኔቴ በ2000 እና በ2002 ላይ አስመራ በሄድኩበት ወቅት የማውቀው የኢሳያስ ከፍተኛ ባለስልጣን ሲሆን በኤርትራ ካሉት እጅግ በርካታ የውጪ ሀገራት ተቃዋሚዎች ውስጥ የኦሮሞ ድርጅቶችን እንዲያስተዳድርና ጉዳያቸውን እንዲፈፅም በእራሱ በኢሳያስ የተሾመ በጣም Influential እና የለየለት ፀረ ኢትዮጵያ arrogant የሆነ ባለስልጣን ነው።
ኤርትራ የገባ ማንኛውም አይነት የኦሮሞ ድርጅት ከራሳችን ኢብሶ ጀምሮ ኦነግ ብትል የጃራ አባገዳ IFLO የዋቆ ጉቱ ድርጅት ብትል የማን – ብቻ የኦሮሞ ድርጅቶች በአጠቃላይ የማያገኙት ይህንን ኮ/ል ጣእመ የተባለውን የኢሳያስ ተወካይ እንጂ ኢሳያስን አንዳችንም በአካል ማግኘት አንችልም የማንችልበትን ስራ የሚሰራ ሰው ነው።
መረራ የአምቦ ተወላጅ በሆነውና የድርጅታችን ኢብሶ አመራር አባል በሆነው በፕ/ር ግርማ ገብረሰንበት እንደተጠራ ስዊዲን ስቶክሆልም በመጋዝ በኮ/ል ጣእመ ጋር ተዋውቆ በፕ/ር ግርማ ቤት ለሁለት ቀናት በማደር ምስጢራዊ ስምምነትን ለመስማማት የቻለበት አመት ነበር። በወቅቱ ሻእቢያ ለእኛ ለኢብሶና ለሌች ኤርትራ ሄደው ለተሰበሰቡ ድርጅቶች የ30ሺህ ዶላር ድጋፍ ያከፈፋለበት ውቅት ስለነበረ መረራ ጉዲናም ከኮ/ል ጣእመ የ30,000$ ዶላር ክፍያ በአባላችን ፕ/ር ግርማ ገብረሰንበት ቤት ተከፍሎት ወደ ሆላንድ እንዲመለስ ተደረገ። ይህ ከሆነ በኃላ ብዙም ሳይቆይ የሻእቢያው ኮ/ል ጣእመ ከመረራ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት ከፕ/ር ግርማ ቤት ለውጦ ዱባይ በማድረግ በዱባይ መረራንና የኦነጉን ዳውድ ኢብሳን በማስተዋወቅና የስራ እቅድና ፕላን በመስጠት ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ። በእለቱ በሻእቢይ ትእዛዝ ድውድና መረራ በጋራ ለመስራት የተነገራቸው ስራ መረራ በሀገር ውስጥ ባለው የኦነግ Cell በመጠቀም ወደ ምርጫ ገብቶ በኦሮሚያ ላይ አሸናፊ ኃይል ሆኖ በመውጣት በፓርላማ ውስጥ ሚና እንዲኖረውና ሁለንተናዊ ሪፖርት (ስለላ ) ስራን በተገቢው ሁኔታ እንዲፈፅም ነው።
በዚህ ስምምነት መሰረትም ሁሉቱም tactical የሆነ የእርሰበርስ መጠቃቃት እንዲያቆሙ ተደርጎ መረራም በየጊዜው ከሀገር እየወጣ በዱባይ በአውሮፓ ከሻእቢያ ጋር እየተገናኘ እጅግ ጠቀም ያለ ገንዘብ ሲከፈለው ሲሆን በአፀፋው ግን መረራ ለሻእቢያዎች ምን አይነት መረጃ ሲያቀብል እንደነበረ ማወቅ አልቻልኩም። በ2005 በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የመረራOromo National Congress ONC የእኔ ድርጅት ኢብሶ አባል የሆነበትን ህብረት ድርጅት ስም ባደረገው የምረጡኝ ዘመቻ ኦነግ በውስጥ ሴሎቹ በኩል ባስተላለፈው የኦብኮን ምረጡ ቅስቀሳ ለመጀመሪያ ጊዜ 48መቀመጫን ማግኘት የቻለ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 42ቱ የኦነግ ቀጥተኛ አባልና ተወካይ የሆኑት ክድሬዎች ነበሩ። ሆኖም መረራ ፓርላማ ከገባ በኃላ ሁሉንም ለብችዬ በማለቱ ከኦነግ ጋር የተጋጨሲሆን ከዚያ በኃላ በተደረጉት የ2010 እና የ2015 ምርጫ ላይ በዜሮ ለመሳተፍ በቅቷል።
2004 እና 2005 አሜሪካ የመረራ ጉዲና እና የመ/አ ኦላና ለሙ ግላዊ ግንኙነትና ውይይቶች ከመረራ ጋር በአሜሪካን የህብረት ስብሰባ ላይ ለበርካታ ግዜያቶች እየተገናኘን ከተሰበሰብንበት ድርጅታዊ ስብሰባዎች ባሻገር ባሉ አጀንዳዎች ላይ ስለሀገራችንና ስለህዝባች ጉዳይ ሀሳብ ለመለዋወጥ በቻልኩበት አጋጣሚ ስለእሱ ያስተዋልኩት ሀቅ ቢኖር ሰውዬው ስለኦሮሞህዝብ ትግል ፈፅሞ እማይቆረቆር እጅግ ገንዘብና ስልጣን አፍቃሪ መሆኑን አይቼያለሁ። ይህም ለገንዘብ ያለው ፍቅር የሻእቢያ ሰላይ እንዲሆን እንዳደረገውና ባለኝ መረጃ መሰረት በ1990ዎቹ መገባደጃ ላይ ግብፅ ሄዶ ገንዘብ በመውሰድ ቤት ለመገንባት እንዳበቀውና ዛሬም ከዳው መራሹ ኦነግ ጋር ህብረት መፍጠር እቅቶት ከጃዋር ጋር ህብረት እንዲፈጥር ያስቻለው የገንዘብና ስልጣን ፍቅር እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ብሎ እንዳልሆነ ነው መረዳት የቻልኩት። ለምሳሌ ያህል በትክክለኛ ሁኔታ ለኦሮሞ ህዝብ ትግልና ህልውና የሚያስብና የሚያምን ሰው ቢሆን ኖሮ ድርጅታዊ ስልጣንንም በመልቀቅ የኦሮሞ ድርጅቶችን አሰባስቦ የጋራ ህብረትን ሲፈጥር እናይ ነበር። ዛሬ ግን ያየነው ገንዘብ ያለውን ጃዋርን ይዞ ከእሱ የባሰ ከፋፋይ ነገር ሲገልፅ የሚታይ ሰው ሆኗል።
በአዲስ አበባ በተካሄደውንሀገራዊ/ብሄራዊ መግባባት ኮንፍረንስ ላይ ስለተንፀባረቀው የመረራ አቋምን በተመለከተ መረራ “አሁን ያለው ኦሮሞ ከአኖሌ ጭፍጨፋ የተረፈ ነው” የሚለው statement ሀገሪቷ አሁን ካለችበት ብሄርና እምነት ተኮር ጥቃቶችና ግጭቶች አኳያ – – በተለይም የኮንፍረንሱ ዋና አላማ ይህንን የተወጠረን ፖለቲካዊ አየር ለማላላት ተብሎ በተጠራ ስብሰባ ላይ ከአንድ እራሱን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ነኝ ብሎ ከሚናገር ሰው እማይጠበቅና ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ሆን ብሎ ትርምስና እልቂት እንዲፈጠር ከመሻት የመነጨ ነው ብዬ አምናለሁ።
ይህ ሴራ ደግሞ የራሱ የመረራ ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት የሻእቢያ መሰሪ አላማና ትእዛዝ ነው ብዬ የምረዳው:::  መረራ ጉዲና ስለአኖሌ ታሪክ ምን የሚያውቀው ነገር ኖሮ ነው እንዲህ የሚናገረው?? ለምንድነው አፄ ምንሊክ እምዬ ምንሊክ የሚል ቅፅል ስም የወጣላቸው ?? ምክንያቱም መሀሪና ሩህሩህ ስለሆኑ ነው ። በአኖሌ ላይ ተፈፀመ የተባለውን ጭፍጨፋ የሚመሳሰል ሌላ ጭፍጨፋዎችን ተፈፀሙ ሲባል ለምን አንሰማም? አርሲ በተለየ ሁኔታ እንዴት ትነጥላ ሊፈፀምበት ቻለ? መረራ የእውነተኛ የታሪክና ፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ቢሆን ኖሮ እነዚህን ወሳኝ ጥያቄዎችን በጥናት በምርምር ደርሶበት ለህዝብ ይፋ ማድረግ ይችል ነበር::: በማለት ሰፊ ማብራሪያ ወዳጄ አጫውቶኛል።
(መዝጊያ – የሐረር ጦር አካዳሚ ምሩቅ የሆነው የመ/አ ኦላና ለሙ በዊንጌት ት/ቤት ከእነ ለገሰ ዜናዊ (መለስ) ዳውድ ኢብሳ ብርሃኔ ገብረክርቶስ እና መሰሎች ጋር በአንድ ክፍል ወይ ቀድሞ ወይ ተቀድሞ ሲማር የነበረ ሲሆን ከሀረር ጦር አካዳሚ ተመርቆ ከወጣ በኃላ ወደ ሀረር ገጠራማ ስፍራ ሄዶ የመጀመሪያእን የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ መልምሎ በማሰልጠን የፈጠረና እነ ባሮ ቱምሳ ወደ ጫካ ሲገ ቡ ተቀብሎ ካዘጋጀው የኦነግ ጦር ጋር ያቀላቀለ ሰው ነው። እራሱ ከመሰረተው የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ በኦነግ አላማ ባለማመን ከማንም በፊት ቀድሞ የለቀቀ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ)
Filed in: Amharic