>

የአፄ ምኒልክ የግብር ኣዳራሽ፤ (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

የአፄ ምኒልክ የግብር ኣዳራሽ፤

 ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ


ዛሬ መኳንንት ሳይሆን በሕዝብ የተከበሩ፤
ትናንት ለኢትዮጵያ የሞቱም ይጠሩ።
ለሥልጣን ተሹመው በስም የተቀመጡ፤
የተፈሩ ቀድሞም ይቅሩ እንጂ አይምጡ።
ለሕዝብ ብልጽግና ከሐብታቸው ያልሳሱ፤
በፈጠራ ጥበብ በዕውቀት የሚክሱ፤
በጀግንነት አልፈው ዛሬም የተረሱ፤
አዳራሹ መጥተው
ሁሉም ፅዋ ያንሱ።

ቅቅሉን እንቁላል ልንገብር ቀርቶ፤
ነፃነት ለነሳን  ማርያምን ብለናል
ኣንለቀውም ሞቶ።
በትግሬ የደገሰልንን የባርነት ቀንበር፤
ድፍን ዓለም ዐይቷል አድዋ  ሲቀበር።
የሚያሳዝነው ግን ከታሪክም ያልተማሩ፤
ቅጥረኞችም እንዳቅምቲ ትናንትና ተቀበሩ።
ኢትዮጵያዊ አበሻ ተባልን አልተባለም፤
ግብራችን እንቁላል በፍፁም አይደለም።
ምንሊክ አምርሮ ጋሻውን አንስቶ ፤
በኢትዮጵያዊነቱ ከሕዝቡ ጋር ዘምቶ።
የወላዲትን ልጅ ክርስቶስን ገዳይ፤
ሥመ ገናናውን እኔ ነኝ ጀግና ባይ።
የሮማን ሰራዊት ገጥሞት አድዋ ላይ፤
አዋርዶታል ባለም በግልጽ ባደባባይ።
ያኔ ባሕር ተሻግሮ ሰማይንም አልፎ፤
ኢትዮጵያን ሊወራት መጣ አሰፍስፎ።
ሰልጥኛለሁ ብሎ ብረት ተመክቶ፤
ጣሊያን ባርነትን ሊያስጀምር ተዋግቶ፤
በቂ ምሽግ ይዞ ጎረቤት አድብቶ፤
ነጭ ለባሾችን በዲናሬ ገዝቶ፤
ድፍን በኢትዮጵያ ሰልሎ እና ዘርቶ፤
የቻለውን ሲያደርግ ዐይኑ ልቡን ሳያይ፤
ምኒልክ ገባለት ኣጨደው ያን ገዳይ።
ልቡን አሸንፎ በጦርነት ወግቶ፤
የጠላትን አንገት ሠይፎና ቀልቶ፤
እንደ አንበሳ በክርን ሲያስደቁሰው ዘምቶ፤
በድል አንበርክኳል ያን ሁሉ ሰላቶ።

ለሰው ፍቅር ግና እምዬ በልቡ፤
ይታወቃል ድሉን በእምነት ቃል ማሰቡ።
እንኳንስ ለወዳጅ ለጠላት ነው ቡቡ፤
በዕምነቱ የጸና ሟች ነው ለማህተቡ።
ከጦር ሜዳው ምህረት ያደላቸው ቢኖሩም፤
ይልቅስ ለበቀል ይመጣሉ አይቀሩም።
የሮማንን ተንኮል እምዬ ስለሚያውቁ፤
በልቡ እንዲፋለም ትውልድ አስጠነቀቁ።
ዓለምን በጦሩ ሮማው ቢገዛም፤
በኢትዮጵያ ላይ ግን ጉራውን ኣልነዛም።
ይኼው በእኛም ትውልድ ታሪኩን አየነው፤
ብንሞትም ብንኖርም የእኛ ኅላፊነት ነው።
የሮማው ጦር ስሙ ኣዲስ ፋሺሽት ሆኖ፤
በዔሮፓ ነግሶ ስሙ ባለም ገንኖ።
መጣ ከትናንትና ወዲያ በቀሉን አስቦ፤
ዳግም ተዋረደ በቀል ተከናንቦ።
ትናንት ከድፍን ትግሬ ባንዳዎች ቢያምፁ፤
በእምዬ ኣለንጋ በሕግ ተገሰዑ።
ወጪና ወራጅን ጠላትና ወዳጅን፤
ለጋስና ንፉግ ታማኝና ከጂን፤
እምዬ ባለድል ምንም ችግር ሳይቀር፤
በሥልጣኔ ውስጥ ያሳዩንም ነበር።
እናም ግብር ብሎ በባርነት ነጋሽ፤
በፍፁም አይንኖርም
በእምዬ አዳራሽ።

Filed in: Amharic