ያሬድ ሀይለማርያም
* “ብሔር ከሌለህ ጋብቻ መፈጸም አትችልም፤ ብለው መልሱኝ!!!”
አቶ ግርማ ሞገስ ከመገደሉ 2 ቀን በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የለጠፈው
* የቆምንለት ዓላማ ገዳይ ሲመጣ የምንሸሸለት አይደለም!
አቶ ግርማ ሰይፉ
በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲፈጸምበት የነበርው የኢዜማ አባል እና እጩ አቶ ግርማ ሞገስ በቢሸፍቱ ከተማ በጥይት ተመቶ መገደሉ እጅግ አሳዛኝ እና የምር
ጫውንም ሂደት ከወዲሁ ችግር ውስጥ የሚከት ነው። በቅርቡ በኦሮሚያ ብልጽግና በኩል በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ስማቸው እየተጠራ ሲጠለ
ሽ እና ሽብርተኛ ሲባሉ ምርጫ ቦርድ ድርጊቱን ያወገዘ ቢሆንም ሰሚ ያገኘ አልመሰለኝም።
ገዢው ፓርቲ ለዚህ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ ያለውን ቁርጠኝነት ከወሬ በዘለለ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች በቂ ጥበቃ እና ድጋፉን ከወዲሁ ማሳየት ይኖርበታል። ይህ እጅግ መጥፎ ምልክት ነው።
የወንድማችንን አቶ ግርማ ሞገስ ነፍስ ይማር! ለቤተሰቦቹ እና የትግል አጋሮቹ ለሆኑት የኢዜማ አባላት መጽናናትን እመኛለሁ።
የቆምንለት ዓላማ ገዳይ ሲመጣ የምንሸሸለት አይደለም!
የብልፅግና ሰዎች በግልፅ ወጥተው በግርማ ሞገስ ሞት ያላቸውን አቋም መግለፅ አለባቸው፡፡ በተለይ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ ዋቅጅር ምክትል ዓቃቢ ሕግና የቢሾፍቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ይህን ጉዳይ ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዝምታ ውድ የሆነ ትርጉም አለው፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎች አጋር የሌላቸው መሆኑን የምናውቀው በአደባባይ ይህን ሲያደርጉ ብቻ ነው፡፡ መግደል መሸነፍ ነው! ብሎ መፈክር ብቻ ዋጋ የለውም፡፡ በተግባር ግድያን እና ወንጀልን ማውገዝ፤ ከግፉዋን ጎን መቆም ያስፈልጋል፡፡ የቆምንለት ዓላማ ገዳይ ሲመጣ የምንሸሸለት አይደለም! ለልጆቻችን የምንመኛትን የነፃ ዜጎች አገር በነፃ እንደማይገኝ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡