>
5:26 pm - Sunday September 17, 2828

ሜጊል ዳየስ  እነ እስክንድርን እንዳይጠይቁ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ከለከለ...,!!! (ባልደራስ)

ሜጊል ዳየስ  እነ እስክንድርን እንዳይጠይቁ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ከለከለ…,!!!

ባልደራስ 

 

“…የኩላሊት ህመም ይበልጥ እያስነከሰኝ ነው – ለመንቀሳቀስ ተቸግሬያለሁ… !!!”
አቶ ስንታየሁ ቸኮል
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የፅህፈት ቤት ሓላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ እና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሜጊል ዳየስ የባልደራስን አመራሮች ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት አምርተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የአቶ ገለታው ባለቤት ወይዘሮ ሜጊል የውጭ ሀገር ዜጋ በመሆናቸው እስክንድር ነጋን፣ ስንታየሁ ቸኮልን፣ አስቴር ስዩምን እና አስካለ ደምሌን እንዳይጠይቁ ተከልክለው ተመልሰዋል። ይህም የእስረኞችን ከወዳጆቻቸው ጋር የመገናኘት መብት የጣሰ ነው። ከዚህ በፊት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች እየተፈቃደላቸው እሥረኞችን ይጠይቃሉ:: ወይዘሮ ሜጊል ዳየስ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚታገሉ መሆናቸው ይታወቃል።
በተያያዘ ዜና አቶ ስንታየሁ ቸኮል የኩላሊት ህመማቸው ዛሬ ተባብሶበቸው እንዳደረ ገልፀዋል። “ይበልጥ እያስነከሰኝ ነው። ለመንቀሳቀስ ተቸግሬያለሁ ብሏል። የወህኒ ቤቱ ሀኪም ቤት ውስጥ እንደሚታከም ቢነገረኝም እስከ አሁን ገቢራዊ አልተደረገም” ብለዋል አቶ ስንታየሁ። የህሊና እስረኛው በግል የህክምና ተቋም ውስጥ እንዲታከሙ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠይቋል። ሆኖም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አልሰጠም።
Filed in: Amharic