>
1:53 pm - Tuesday June 6, 2023

የትግራይ ፖለቲካ መዳረሻዉ ምን ሊሆን ይችላል? ( ሸንቁጥ አየለ)

የትግራይ ፖለቲካ መዳረሻዉ ምን ሊሆን ይችላል?

ሸንቁጥ አየለ
ወያኔ የተመኘዉን የጾሎቱን ዉጤት አግኝቷል

በአሁኑ ሰዓት ወያኔዎች አብደዋል::በጣም ተናደዋል::በራሳቸዉ ግፍ እና ጸሎት ያገኙት እድልም አስደንግጧቸዋል::እና የሚሰሩት ነገር ሁሉ ምን እንደሆነም አያስተዉሉ::ለነገሩ ወያኔዎች ሀያ ሰባት አመታት እግዚአብሄር ስልጣን ላይ ቢያስቀምታቸዉም አንድም ቀን የሚሰሩትን ነገር አስተዉለዉ አያዉቁም::ከአንድ የክርስቲያን ማህበረሰብ ከወጣ ሀይል ሳይሆን ከኢአማኝ ማህበረሰብ እንደወጣ አረመኔ ደም መጭ የሰዉ ደም በመምጠጥ ከፍተኛ እርካታን ሲጎናጸፉ ነበር::
ዛሬም ተሸንፈዉ ያዉ ያለማስተዋል በሽታቸዉ ቀጥሏል:: የቀድሞ ጠሎታቸዉን እና ምኞታቸዉን አሁንም ይዘዉ ቀጥለዋል:: የኢትዮጵያን ባንዲራ ያቃጥላሉ::የአማራን ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለመጨፍጨፍ ይዝታሉ::ያጓራሉ::ኢትዮጵያዊ አይደለንም ካሁን ብኋላ ትግራይን ገንጥለን እንመሰርታለን እያሉ እንቡር እንቡር ይላሉ::ከኢትዮጵያዊ ጋር በተለይም ከአማራ ጋር አትጋቡ የተጋባችሁ ተፋቱ ይላሉ::
ደግሞ ፈልገዉ የሚያቃጥሉት ንጹሁን የኢትዮጵያን ባንዲራ ነዉ::ብልጽግና የተባለዉ ሀይል ወያኔን የተዋጋት በንጹሁ ባንዲራ ነዉ ብለዉ ያስባሉ::አሁንም በኢትዮጵያ መንግስት የሚመለከዉ ባንዲራ እነሱ አንባሻ የለተፉበት ባንዲራ መሆኑን ይክዳሉ::
ሙሉ ለሙሉ ወያኔዎች የሚስማሙበት አንድ ትርክት ፈጥረዋል::ቀጥቅጦ ያጠፋን የአማራ ልዩ ሀይል ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል::የብልጽግና መከላከያ የሚባለዉን አጥፍተንዉ ነበር::ያልቻልነዉ የአማራን ልዩ ሀይል ነዉ ብለዉ ይጮሃሉ::በሌላ መልክም በጣም አስገራሚ ትንታኔም አላቸዉ::ኤርትራ ወሮናል ብለዉ ሲያበቁ ኤርትራ ወዳጃችን ነዉ ይላሉ::ጠላታችን አማራ ብቻ ነዉ የሚል ትርክታቸዉን ያስነኩታል::የተሸነፈዉ ህዉሃት ዋና የትርክቱ ማጠንጠኛ የ1967 ዓም የህዉሃት ማኒፌስቶ ላይ ሙጭጭ ማለቱን ቀጥሏል::እንዴዉም አንዳንዴ “አቢይ አህመድ እራሱ አማራ ነዉ ይላሉ::አቢይ አህመድ ኦሮሞ አይደለም::ኦነጎች/ኦህዴዶች አሁንም ከኛ ክህዉሃቶች ጋር ናቸዉ” ሲሉም ይደመጣሉ::በዉጭ ሀገርም ከኦነጎች/ኦህዴዶች ጋር ልዩ ግንኙነት ይፈጥራሉ::
ብልጦቹ ኦህዴዶች/ኦነጎችም “አዎን ከእናንተ ጋር ነን” እያሉ አብረዋቸዉ ያላቅሷቸዋል::ህዉሃት የአዕምሮ ችግርም ያለባቸዉ ሰዎች ስብስብ ነዉ::ለምሳሌ ህዉሃቶች በስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ የሚያስቡት ኦህዴዶች/ኦነጎች ዘላለማቸዉን የኛ አሽከር ሆነዉ ስለሚኖሩ ደህንነቱንም: ፖሊሱንም: ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩንም: መከላከያዉንም: ኢንሳንም ኦነጎች/ኦህዴዶች እስከያዙት ድረስ ስጋት የለብንም የሚል እምነት ስለነበራቸዉ ሁሉንም ነገር ጠቅልለዉ ለኦነግ/ኦህዴድ አሸክመዉት ነበር::
“የሰዉ ሞኝ በምድር ላይ የለም” የሚለዉን አንድ ህጻን ልጅ የማይስተዉን ነገር የሳቱ የጭንቅላት በሽተኞቹ ወያኔዎች በኦህዴድ/ኦነግ ተንፈርፍረዉ ተበልተዋል:: የህዉሃቶች አንድ የቤት ስራ አማራ የሚባል ባለስልጣንን አንደኛ ወደ ስልጣን አለማምጣት ማረጋገጥ ሁለተኛ ድንገት አልፎ አልፎ የመጡም ካሉ እነሱን ማሰለል መጠበቅ እና ስልጣን እንዳይነጥቁን ብሎ ተጨንቆ መከታተል ነበር::ይሄዉ በሽተኛ የህዉሃት አስተሳሰብ ደህና ዋጋ አስከፍሏታል::መቀበሪያዋን::
የሆነዉ ምንድን ነው? የሆነዉ በአጭሩ የወያኔ ጸሎት ነዉ የደረሰለት::ይሄ ጸሎት ምንድን ነበር? “ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እናጠፋለን ኢትዮጵያን ከብሄር ብሄረሰብ ማንነት በታች እናደርጋታለን::አማራ የሚባል ህዝብ እናጠፋለን::ኦርቶዶክስ የሚባል ህዝብ እናጠፋለን::ኦርቶዶክስ ወይም አማራ የሆነ ወደ ኢትዮጵያ ስልጣን እንዳይመጣ እናደርጋለን” ብለዉ በአዋጅም:በፖለቲካ ፕሮግራምም በፕሮፖጋንዳም እንደለፉት የፈለጉትን አግኝተዋል::
አሁን ሀገሪቱ የምትመራዉ በአማሮች አይደለም::አሁን ሀገሪቱ የምትመራዉ በኦርቶዶክሶች አይደለም::አሁን ኢትዮጵያ ከብሄር ብሄረሰቦች ማንነት ያነሰ ማንነት ነዉ ያላት::አሁን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ በሰራዉ ተቋማዊ ደባ ፕሮፖጋንዳ እና ህገመንግስታዊ ተንኮል ለመጥፋት እየተንገዳገደች ነዉ::አሁን አማሮች በመላ ሀገሪቱ መታረዳቸዉን መሳደዳቸዉን ቀጥለዋል::ሀያ ሰባት አመታት ወያኔ እራሱ አማራን ሲያሳርድ እንደነበረዉ አሁን ደግሞ ኦነጋዊ/ኦህዴዳዊ ሀይል አማራን ማሳረዱን ቀጥሏል::ህዉሃት ዋና ጸሎቱ ኦርቶዶክስም አማራም ያልሆነ ሀይል በኢትዮጵያ ምድር አነግሳለሁ የሚል ነበር::ተሳክቶለታል::ዛሬ ኦርቶዶክስም አማራም ያልሆነ ኦነግ/ኦህዴድ በኢትዮጵያ ነግሶለታል::ለህዉሃታዉያን ግን ኦነግ/ኦህዴድ አሁን ላይ የሚታያቸዉ አማራ ሆኖ ነዉ::
የሆነ ሆኖ የህዉሃት ጸሎቱ ሰምሮለታል::ህዉሃት እሰይ ጸሎቴ ሰመረ ብሎ መጨፈሪያዉ ሰዓት ነበር እንጂ እንዲህ ማልቀሻዉ ሰዓት አልነበረም::ሆኖም የሆነዉ ነገር ህዉሃት ያልተበቀዉን መራራ እዉነት አስከትሎ መጥቷል እና ህዉሃት ወደ ለቅሶ ገብታለች::በአንድ ሀገር ሁለት ንጉስ አይኖርም::ወይ ህዉሃት ወይም ኦነግ/ኦህዴድ ማሸነፍ ነበረባቸዉ እና ህዉሃት በኦነግ/ኦህዴድ ተቀጥቅጣ ወደዳር ወጥታለች::
ህዉሃታዉያን ሲያስቡ ሁል ጊዜም ኦነግ/ኦህዴድ የተባለዉን ሀይል ፈረስ እና ጋሪ አድርገን እየጫንነዉ እንኖራለን ብለዉ ነበር::ግን ሁሉ ሰወ በእግዚአብሄር ክቡር የህሊና ባለቤት ነዉና ህዉሃትን አታሎ እና አቂሎ ኦነግ/ኦህዴድ አንፈርፍሮ በልቷታል::ለዚህ ድል ብአዴን ቁልፍ ድርሻዉን ቢጫወትም ስልጣኑን እሱ ከሚወስደዉ ወያኔ እንደተመኘችዉ ኦነግ/ኦህዴድ እንዲመራዉ ፈቅዷል::ኦነግ/ኦህዴድ በህዉሃት እጅ የህሊና እጥበት የተደረገበት ሀይል ስለሆነ እንጂ  ብአዴን ስላደረገለት ዉለታ ሲል እንኳን የአማራን ነገድ ከመግደል እና ከማሳረድ መቆጠብ ነበረበት::ሆኖም ኦነግ/ ኦህዴድ አሁንም የአማራን ነገድ ወያኔ እንዳስተማረችዉ ማጥፋቱን ቀጥሏል::በዚህም ወያኔ ተሳክቶላታል::ምኞትና ህልሟ ይሄ ነበርና::
ሆኖም ወያኔ አሁንም የምትደነፋዉ አማራ አክሱም ገብቶ ገረፈኝ:አማራ ከኢትዮጵያ አባረረኝ ስለዚህ ከኢትዮጵያ እገነጠላለሁ እያለች ነዉ::ወያኔ መቼም ቆሟ ማንሰላሰል ባታዉቅም ለፈራረሰችዉ ወያኔ አሁንም ጥያቄ ሊቀርብላት ይገባል::ኦነግ/ኦህዴድ እናንተ ወያኔዎች እንደምትፈልጉት ኢትዮጵያን እየመራላችሁ ኢትዮጵያንም ይበልጥ እያፈራረሰላችሁ ሳለ አማራ ላይ ጣታችሁን የምትቀስሩት ምን ሆናችሁ ነዉ? ለምሆኑስ ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን የምትሉት ከየትኛዋ ኢትዮጵያ ነዉ?ኢትዮጵያን እኮ አፍርሳችኋታል ! ለመሆኑስ የተመኛችሁት አማራ ባልሆነ: ኦርቶዶክስ ባልሆነ ሀይል መገዛት/መቀጥቀጥ አልነበረም እንዴ? ነዉ ወይስ ኦርቶድክስ/አማራ ያልሆነዉ ሀይል ሲነግስ እናንተ ያዉ በወያኔነት እየተኮፈሳችሁ የምትቀጥሉ መስሏችሁ ነበር?
ለማንኛዉም ወያኔ የእጇን: የጸለዬችዉን እና የተመኘችዉን አግኝታለች::እንደተመኘችዉም ኦርቶዶክስም አማራም ያልሆነ ሀይል በገዥነት ተቀምጦ እያጠፋት ነዉ::እሰይ እንኳንም እንዲህ ሆነ::እግዚአብሄር የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ነዉና እንኳንም እንደተመኛችሁት አማራም ኦርቶዶክስም ባልሆነ ሀይል አስጠፋችሁ:: ቅዱሳ ሲጸልዩ “ሀጢያተኛን እዚያዉ በሀጢያተኛ አጥፋዉ” እንዲሉ ሁሉም ነገር እግዚአብሄር በሚያዉቀዉ ሆኗል::
ምንም እንኳን አሁንም በከፋ እና በከረፋ መልኩ አማራ እና ኦርቶዶክስ ላይ የዘር ፍጅቱ በኦህዴድ/ኦነግ ሀይል የቀጠለ ቢሆንም ይሄንንም እግዚአብሄር በጥበቡ ይቀለብሰዋል::ሀይልን ያስነሳል::ኢትዮጵያን ያድናል::ወያኔ ግን ከኢትዮጵያ እገነጠላለሁ:የአማራን ባንዲራ አቃጥላለሁ:አማራን አጠፋለሁ እያልክ ለዘላለም በራስህ ሀጢያት ትጠፋለህ::ከእንግዲህ ከኢትዮጵያ እጣ ፋንታም የለህ::
መዳረሻዉ ምን ሊሆን ይችላል?
እናም ወደ ትልቁ ጥያቄ ልሸጋገር::የትግራ ፖለቲካ ወደፊት መዳረሻዉ ምን ሊሆን ይችላል ወደ ሚለዉ:: የትግራይ ፖለቲካ ወደፊት ሶስት መዳረሻዎች አሉት::አንደኛዉ አማራጭ የወያኔን ማኒፌስቶ እስከ መጨረሻዉ ሙጥኝ ብሎ የትግራይን ህዝብ ለዘላለም ከአማራም ከኢትዮጵያም ነጥሎ በጥላቻ የሰከረ ፖለቲካ እያራመዱ በጥላቻ የኮሰመነ እና የከሰመ ሀይል ሆኖ መቀጠል ነዉ::ይሄ ለትግራይ ህዝብ እጅግ አደገኛዉ እና መራራዉ የመከራ መንገድ ይሆናል::ምናልባትም ወያኔ እራሱ አስቦት የማያዉቀዉ መዓት እና መከራ::
ሁለተኛዉ አማራጭ ከኢትዮጵያዊ ማንነት የታረቀ :ከተዋህዶ ማንነት የታረቀ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ ጋር የታረቀ እና የተመጋገበ ፖለቲካዊ ህሳቤን በመቅረጽ ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ የሚሰራ ሀይል የመነሳቱ ተስፋ ነዉ::ይሄ ተስፋ አንዴ መነሻ መሰረት ካገኘ በቀላሉ የህዉሃትን መርዛማ አስተምህሮት ጠራርጎ የመጣል ሀይል አለዉ::ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ ማንነቱ የተዋህዶ ማንነት ስለሆነ በተዋህዶ ላይ የተነዛዉን የወያኔ መርዝ በቀላሉ መንቀል ይቻላል::በኢትዮጵያዊነት ላይ ወያኔ የሰራዉን ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳም በቀላሉ ማክሰም ይቻላል::ከአማራ ህዝብ ጋር ያለዉን ሀሰተኛ ትርክትም በማክሸፍ መልካም ወንድማማዊነት የሰፈነበትን መሰረት በመጣል ትልቅ ኢትዮጵያን መስራት የሚያስችል ግብዓት መሆን የሚችሉ ማህበረሰቦችን በጋራ ማናበብ የሚችል ይሆናል:: ሆኖም ይሄ ተሳፍ አሁን ባለዉ የትግራይ ልሂቃን:የትግራይ ፖለቲከኞች እጅግ እሩቁ አማራጭ ነዉ::ሙሉ ለሙሉ የማይቻል ነዉ ባይባልም በጣም የቀጠነ እድል ያለዉ ነዉ::ግን ትክክለኛዉ መንገድ እና አማራጭ ይሄ ነዉ::
ሶስተኛዉ አማራጭ አሁን ወያኔዎቹ እንደሚደነፉት ትግራይ ተገንጥላ ሀገር ትሆናለች::ይሄኛዉ አማራጭ መቼም የሚሆን አይመስልም::ግን አይሞከርም አይባልም::ትግራይ ሀገር ብትሆን እራሷን ችላ መቆም የማትችል የኢኮኖሚ መሰረቷ በራሱ መራራ ዋጋ የሚያስከፍላት ስለሚሆን የትግራይ ብዙሃን ህዝብ ይሄን አማራጭ አይቀበለዉም::
ለማኛዉም ሶስቱም አማራጮች ያሉት እና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉት በትግራይ ልሂቃን:ምሁራን እና ፖለቲከኞች እጅ ነዉ:: የትግራይ ፖለቲካ መዳረሻዉ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉ ጥያቄ ግን በዋናነት ቁርኝቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መዳረሻ ምን ሊሆን ይችላል ከሚለዉ ነጥብ ጋር የተሳሰረ ነዉ::
በአሁኑ ሰዓት የትግራይን  ብዙሃን ህዝብ ለመከራ የማገደዉ የህዉሃት ካንሰራማ የፖለቲካ ፍልስፍና መላዋን ኢትዮጵያንም ለመከራ ማግዷት ሄዷል::ህዉሃት እና ህዉሃታዉያን ግን ኢትዮጵያ ገፋችን እያሉ ያፈረሷትን ኢትዮጵያ ልንገነጠልልሽ ነዉ እያሉ ያስፈራሯታል::በእነሱ ቤት እኮ ተዉ አትገንጠሉ የምትላቸዉ ኢትዮጵያ ያለች መስሏቸዋል::ኢትዮጵያዉያን እንዳይበታተኑ የምትንሰፈሰፈዉን ኢትዮጵያ እማ አማራ የሰራት ኢትዮጵያ ናት ብለዉ ሙሉ ለሙሉ ካፈረሷት እማ ቆዩ::
አንዳንዶቹም ሳያፍሩ 96% ኦርቶዶክስ የሆነዉ የትግራይ ህዝብ መከራ ሲደርስበት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አላወገዘችልንም ብለዉ ተዋህዶን ይወቅሷታል::ሆይ ሞኝነት ! ተዋህዶን እኮ እናንተ ህዉሃታዉያን አፍርሳችኋታል:: Demoblizing Orthodox/ኦርቶዶክስን ማክሰም በሚለዉ ፖሊሲያችሁ እኮ አዋርዳችኋታል::ቤተክርስቲያናቷ ምዕመናኗ እንዲቃጠሉ ሀያ ሰባት አመታት ሰርታችኋል::ለዛሬዉ የኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን/ጀዋራዉያን ተዋህዶን መዳፈር/ማቃተል/ማጥፋት ዋና መሰረቱን የጣላችሁት እኮ እናንተ ህዉሃቶች ናችሁ::
ተዋህዶ ከኢትዮጵያ ፈጽማ እንድትጠፋ አንድም የተዋህዶ አማኝ ስልጣን ላይ እንዳይመጣ እኮ ስርታችኋል::አሁንም ከጀዋራዉያን/ኦነጋዉያን ጋር እየተባበራችሁ እኮ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኖቿን እያቃጠላችሁ እኮ ነዉ::ተዋህዶ መከራ ሲወርድባት የታገልንለት አላማ ነዉ ብላችሁ እግራችሁን አንስታችሁ ስቃችሁባታል እኮ::ሰዉ እንዳይኖራት:ጳጳስ እንዳይኖራት: ካህናት እንዳይኖራት:ዲያቆናት እንዳይኖራት:አገልጋይ እንዳይኖራት ሰርታችሁባታል እኮ::ከሌሎች እምነቶች እንድታንስ የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኋል እኮ::እና የትኛዋ ኦርቶዶክስ ዛሬ ስለ እናንተ ትጩህላችሁ? ያጠፋችኋት ተዋህዶ ትጩህላችሁ?  በተዋህዶ ዉስጥ ያለዉን ማጥፋታችሁን ዞር ብላችሁ ማሰብ አትፈልጉም::ህሊናም የላችሁ እና የምትናገሩትን አታዉቁምና ብትዘላብዱ አይገርምም:: እግዚአብሄር የረገማችሁ እግዚአብሄር ልጄ ከሚለዉ ኢትዮጵያዊነት ጋር የተጣላችሁ ምናምንቴዎች ናችሁ እና ስራችሁ በሙሉ ተነቅሎ ከኢትዮጵያ ይጠፋል::
መደምደሚያ
ለማንኛዉም ከወያኔ ህሳቤ ዉጭ ላላችሁ የትግራይ ምሁራን:ልሂቃን እና ፖለቲከኞች ለትግራይ ህዝብ የተሻለዉን የፖለቲካ መዳረሻ እንድትመርጡ አሳስባለሁ::ይሄም የተሻለ አማራጭ ከኢትዮጵያዊ ማንነት የታረቀ:ከተዋህዶ ማንነት የታረቀ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ ጋር የታረቀ እና የተመጋገበ ፖለቲካዊ ህሳቤን በመቅረጽ ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ  የሚሰራ የፖለቲካ ህሳቤን ይዞ ወደፊት መምጣት ነዉ:: ይሄ ተስፋ አንዴ መነሻ መሰረት ካገኘ በቀላሉ የህዉሃትን መርዛማ አስተምህሮት ጠራርጎ የመጣል ሀይል አለዉ::ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ ማንነቱ የተዋህዶ ማንነት ስለሆነ በተዋህዶ ላይ የተነዛዉን የወያኔ መርዝ በቀላሉ መንቀል ይቻላል::በኢትዮጵያዊነት ላይ ወያኔ የሰራዉን ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳም በቀላሉ ማክሰም ይቻላል::ከአማራ ህዝብ ጋር ያለዉን ሀሰተኛ ትርክትም በማክሸፍ መልካም ወንድማማዊነት የሰፈነበትን መሰረት በመጣል ትልቅ ኢትዮጵያን መስራት የሚያስችል ግብዓት መሆን የሚችሉ ማህበረሰቦችን በጋራ ማናበብ የሚችል ይሆናል::
Filed in: Amharic