>

የሌባ ተቀባይ ኃጢኣት ከሌባው ኃጢኣት ቢበልጥ እንጂ አያነስም  (ይድረስ ለነአብርሃ ደብረጽዮን ደስታ ገ/ሚካኤል) - አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ

የሌባ ተቀባይ ኃጢኣት ከሌባው ኃጢኣት ቢበልጥ እንጂ አያነስም 

(ይድረስ ለነአብርሃ ደብረጽዮን ደስታ ገ/ሚካኤል)

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ


Email: martyrof2011@gmail.com)


አብርሃ ደስታን ለመግለጽ ቃላት አጥቼ ብዙ ተቸገርኩ፡፡ ልፍጠር ብልም “ማን ይረዳኛል?” ብዬ ተውኩት፡፡ አማርኛ ግና ጥሩ ጥሩ አባባሎች ስላሉት የማውቃቸውን ያህል ላስታውስ፡፡ “የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ” ፣ “የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ” ፣ “የእባብ ልጅ እባብ ነው” ፤ “እባብ የወጣበትን ጉድጓድ አይረሳም”፣ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ”፣ “የማን ዘር ጎመን ዘር”፣ የማን ነሽና ትባረኪያለሽ”፣ … በቃኝ፡፡

ሁሉም አባባሎች በስተቀሮች አሏቸው፡፡ “Every generalization has an exception.” ለማለት ነው በዓለም አቀፍ ቋንቋ አገላለጥ፡፡ ስለዚህም አብርሃ ደስታ የተማረና የተመራመረ ሆኖ ሳለ አባቶቹ ከአማራ የዘረፉትን ግዛትና ሀብት ንብረት ዐይኑን በጨው አጥቦ “ ወልቃይንና ራያን መልሱልኝ፤ አለበለዚያ ጫካ ገብቼ እፋለማለሁ፤ በዚያም ብቻ ሳልወሰን ትግራይን ከኢትዮጵያ እገነጥላለሁ” እያለ በሲብስቴ ዘመን የማስፈራሪያ ሥልት “ቀልባችንን መግፈፉ” እንደተጠበቀ በሌላ በኩል ደግሞ ራስ መንገሻ ሥዩም ወይም ሥዩም መንገሻና የኢትዮሰማዩ ድረገጽ አዘጋጅና ባለቤት ጌታቸው ረዳ ከመሰል ጥቂት ተጋሩ ጋር “ትግራይ ከተከዜ ወንዝና ከማይጨው ወዲያ አስተዳድራ አታውቅም፤ ይህ ጊዜ ሰጠኝ ብሎ የሰውን ግዛት መውረርና ወደራስ ማስገባት አያዋጣንም…” የሚሉ ሃቀኛ ትግራውያን መኖራቸው ቁጥራቸው ቢያንስም የበረሃ ምንጭ ናቸውና ዘር ይውጣላቸው፡፡ (ጌች ብፍላይ ክሳብዚያ ንጸብየላ ዘመን ጸኒእናሲ ብኣካል ንምርርዓይ … ፡፡)

አብርሃ ደብረጽዮን ደስታ ገ/ሚካኤል ከቢጤዎቹ ጋር ሰሞኑን ሲያብድ እያየን ነው፡፡ አእምሮ ያለው ሰው እንዲህ በሰው ንብረት ሊንቀዠቀዥ ባልተገባው፡፡ አባቶቹ በሰው ደምና በሰው ሀብትና ንብረት የቆረቡ በመሆናቸው እሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ሲጋት የኖረውን የሀሰት ትርክት ተቀልቦ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ነው፡፡ ያዝልቅለት፡፡ መንገዱንም ጨርቅ ያድርገለት ብዬ እንዳባቱ መለስ ከመመረቅ ውጪ የምለው የለም፡፡ አማራ በደሙና በአጥንቱ የተዋለበትን ግፍና በደል ከላዩ አሽቀንጥሮ ጥሏል፡፡ ከእንግዲህ አማራን ማሞኘት አይቻልም፡፡

እኔ ዕድሜየ ወደ 60ዎቹ እየተጠጋ ነው፡፡ ይህ ዕድሜየ ግሳንግሱና ሥነ ሕይወታዊው (ባዮሎጂካል) እንጂ የማምንበት ዕድሜ አይደለም፡፡ ካደረሰኝ በጊዜው ወደሥሌቱ እገባለሁ፡፡ ለማንኛውም በልጅነቴም ይሁን በወጣትነቴ የማውቀው ታሪክ ወልቃይትና ራያ የጎንደርና የወሎ ግዛቶች ሆነው ነው፡፡ ለምሣሌ የኮረም ከተማ ከንቲባ የራሴው ዘመድ እንትና የሚባልና አሁንም ድረስ በሕይወት ያለ በሰሜን ወሎ መስተዳድር የተመደበ ነበር፡፡ አፄ በጉልበቱ ወያኔ አገር ምድሩን ስትቆጣጠር ግን የትግራይን አዋሳኝ ለም መሬቶች ጠቅልላ ወደ ትግራይ አስገባችና አፍንጫችሁን ላሱ አለች፡፡ አማራጭ አልነበረም፡፡ ወያኔ እንኳንስ የኢትዮጵያን መሬትና ሀብት ንብረት ቻድና ኒጀርንም ልቆጣጠር ብትል የሚያግዳት የነበረ አይመስለኝም፡፡ ጥጋቧ ጥጋብ አልነበረም፡፡ መንግሥተ ሰማይንም ለመቆጣጠር እኮ ስንት ቦጦሊዮን እንደሆነ አላውቅም እንጂ ልካለች አሉ፡፡ ግን ከደመና በላይ ሳይዘልቁ በመብረቅ ተመቱና ወደ ሲዖል ወረዱ አሉ – መቼም አሉ ነው፡፡ እናም ወያኔ የወሰደችው እርምጃ ሁሉ ትክክል ነበር ብሎ መጃጃል ለተጨማሪ ትዝብትና ለከፋ ጉዳት መዳረግ ነው ጅሌ፡፡

የዚህ ጥቁር ታሪክ ወራሽ እንሁን የሚሉን አዲሶቹ የትግራይ መስተዳድር “የካቢኔና የሚኒስትር አባላት” እየተናገሩት ያለው እጅግ አሳፋሪ ነው፡፡ እኔ እነሱን ብሆን “ውድ የአማራ ሕዝብ ሆይ! ሕወሓት አማራንና ኦሮቶዶክስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በማኒፌስቶ በተደገፈ ሰነድ ሳይቀር ብዙ ለፍቷል፡፡ አባቶቻችን ያጠፉት ጥፋት ምድርና ሰማይ አይችሉትም፤ ተነግሮም አያልቅም፡፡ አማራን በጅምላ ገድለዋል፤ በጅምላ አሳደዋል፤ አስረዋል፤ አኮላሽተዋል፤ ሊነገር የሚዘገንን ጸያፍ ግፍና በደል አድርሰውበታል፡፡ በዚህም ሳይወሰኑ ወልቃይትንና ራያን የመሳሰሉ የአማራ ቀደምት ግዛቶች ወደ ትግራይ ጠቅልለው በማስገባት ትውልዱን በላም አለኝ በሰማይ አሳስተዋል፡፡ በወልቃይትና በራያ የዜጎችን ማንነት ለማስቀየር ከለየለት ጭፍጨፋ እስከመብት ረገጣ ያላደረጉት ነገር የለም፡፡ ይህንን ሁሉ ግፍና በደል አዲሱ የትግራይ ትውልድ ጠንቅቆ ይገነዘባል፡፡ ፈጣሪም ያንን ሁሉ ሕወሓታዊ ግፍና በደል መዝግቦ ይዞ አሁን ትግራይ ላይ ፍርዱን በመስጠቱ ስቃይ ላይ እንገኛለን፡፡ ያለፈን የታሪክ ጠባሳ ማስተካከል ከባድ ቢሆንም የመላው ትግራይ ሕዝብ አንገቱን ደፍቶ የአማራን ሕዝብ ከልብ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ከይቅርታ በላይ ለሆኑ ወንጀሎች ደግሞ ወንጀለኞችን ይዘን ለህግ በማቅረብ ተበዳዮችን እንክሳን፡፡ ትግራይ ተስተካክላ በጥሩ አቋም ላይ ስትሆን ደግሞ ሕወሓት ባደረሰችው በደል ለተጎዱ የአማራ ቤተሰቦችና ለአማራ ሕዝብ ባጠቃላይ ትግራይ በተቻላት አቅም ካሣ ለመክፈል ጥረት ታደርጋለች፡፡ ለሆነው ሁሉ በኅያው እግዚአብሔር ስም በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡…”  በማለት አዲስ ታሪክ እሠራ ነበር፡፡ ይህን ለማለት ግን እርግጥ ነው ከትልቅ ሆድ ይልቅ ትንሽም ቢሆን አእምሮ ያስፈልጋል፡፡ ግን ግን ዘረኝነት እንዴት ያሳብዳል?

አማራ ጸሎቱ ሥሙር ነው፡፡ በጠበንጃ ከሚዘርራቸው ይልቅ በጸሎቱ ድባቅ የሚመታቸው ይበልጣሉ – በተደጋጋሚ አየነዋ! አማራ ብዙ ግፍና በደል ደርሶበታል፡፡ መሰቃየት፣ መገደል፣ መሰደድ፣ መታሰርና መንገላታት ለአማራ ሕዝብ “ባህላዊ ጨዋታ”ው ነውና ብርቁ አይደለም፡፡ ነገ ግን ሌላ ቀን መሆኑን በተለይ ተረኞች ሊያውቁት ይገባል (በነገራችን ላይ በተረኞች ቂልነት ከመገረም አልፌ መሣቅ ጀምሬያለሁ)፡፡ በመገደል እንደሚገኝ ያለ ድል በመግደል አይገኝም፡፡ በመሞት እንደሚገኝ ያለ ደስታና ፍስሃ በመወለድ አይገኝም፡፡ ስማኝማ …. ዛሬ “ባጃሃ፣ በጃሃ” ሲባል እየሰማን ነው፡፡ ነገ ደግሞ “ማሎ፣ ማሎ” ሲባል እንሰማለን ፡፡ ለዚህ ደግሞ የመተከል ንጹሕ ደም፣ የወለጋ ንጹሕ ደም፣ ኦሮሚያ በሚባለው ክልል የሚፈሰው ንጹሕ ደም ምስክሬ ነው፡፡ ስለዚህ አክራሪ ዘረኝነትን ተጠየፍ ወንድማለም፡፡

የዛሬ ስንት ዓመት ገደማ ምን ብዬ ነበር መሰለህ – ላስታውስህ፡፡ “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”፡፡  ሲሉ ሰምቼ ከተናርኩት ደግሞ ሌላ ልጨምርልህ – “ ፈጣሪ ሆይ! ምን በድየህ ነው ትግሬ አድርገህ የፈጠርከኝ?” የሚባልበት ዘመን ይመጣል፡፡ ቀንም ሆነ፣ ሌትም ሆነ፣ ሁሉም ሆኖ ግን አንዱ ብቻ ቀረ! ጽንስ እናቱን ቢያሰቃይም በቀኑ ይወለዳል፡፡      

Filed in: Amharic