>

"ቪቫ ምኒልክ!!!" የሚባለው ተወዶ ብቻ አይደለም...!!! (መስከረም አበራ)

“ቪቫ_ምኒልክ!!!” የሚባለው ተወዶ ብቻ አይደለም…!!!

መስከረም አበራ

*…. የጥቁር ህዝብ የነፃነት አርማ የሆነውና ለእኛ  ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ የኩራታችን ምንጭ የሆነው የአድዋ ድል በዓል መከበር ያለበት በወያኔም ሆነ በዱላ ተቀባዩ ብልፅግና ሰባራ ሚዛን ሳይሆን  አድዋን በእውነት በሚገልፅ ግዝፈት ነው መሆን ያለበት…!
 
በ1983 ስልጣን የያዘው ወያኔ ሞቱን እስከሞታት ድረስ የአድዋ ድል በዓልን የሚያከብርበት መንገድ እጅግ አስተዛዛቢ ነበር። ወያኔ ከአድዋ ድል በዓል ይልቅ ሰባቱ የወያኔን መስራች የአንድ ወንዝ ልጆች ወንድማቸውን ለመውጋት ደደቢት የገቡበትን ቀን አድምቆ ያከብር ነበር – ሰባራ ሚዛን አንድ!
 ወያኔ ሞቱን በሁለት አመት ውስጥ ቀስ እያለ ከሞታት ወዲህ ዘንድሮ አድዋ በተሻለ ድምቀት እየተከበረ ያለ ይመስላል። በዘንድሮው የአድዋ ድል አከባበር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የአፄ ምኒልክንና የእቴጌ ጣይቱን ስም ላለማንሳት ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ነው በዓሉን ለማክበር እየጣሩ ያሉት- ሰባራ ሚዛን ሁለት!
የጥቁር ህዝብ የነፃነት አርማ የሆነውና ለእኛ  ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ የኩራታችን ምንጭ የሆነው የአድዋ ድል በዓል መከበር ያለበት በወያኔም ሆነ በዱላ ተቀባዩ ብልፅግና ሰባራ ሚዛን ሳይሆን  አድዋን በእውነት በሚገልፅ ግዝፈት ነው መሆን ያለበት።
 የአድዋ ግዝፈት በምሉዕ ማንነቱ ሲገለፅ ደግሞ አፄ ምኒልክን/ እቴጌ ጣይቱን ጥሎ ጥሪውን ሰምተው የመጡ ጀግኖችን አንጠልጥሎ ወይም ከሃገር ዳርቻ ደማቸውን ሊያፈሱ የንጉሳቸውን የአፄ ምኒልክን ጥሪ ሰምተው የመጡትን ጀግኖች ጥሉ አፄ ምኒልክን/እቴጌ ጣይቱን አንጠልጥሎ መሆን የለበትም።
 ተወደደም ተጠላ የአድዋ ገቢራዊነት ምኒልክነትን/ጣይቱነትን ግድ ይላል! ከሃገር ዳርቻ ተሰብስቦ ወደ አድዋ ሊዘምት ለመጣው ጀግና ኢትዮጵያዊ  መሰብሰቢያው ምኒልክነት ነው። ይህን ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ ጣሊያኖች እያቃራቸው የተቀበሉት፣ በንዴትም ቢሆን፣ወደው ሳይሆን ተገደው የተቀበሉት ንጥር ሃቅ ነው። ሳይወዱ በግድ ” #ቪቫ_ምኒልክ” ያስባላቸውም ይህ ሃቅ ነው !
” #ቪቫ_ምኒልክ”የሚባለው ተወዶ ብቻ አይደለም ፤ ሃቅ የሚያንቀው ሁሉ ይህን ሊገነዘብ ይገባል! ጣሊያን እንኳን  የተገነዘበው ይህ ሃቅ ሊገባው ያልቻለ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ የሚያታልለው ራሱን ነው!
 #ቪቫ_ምኒልክ
#ክብር_ሞተው_ላቆሙን_ኢትዮጵያዊያን_ሁሉ
Filed in: Amharic