>

የአድዋ በዓል እና ምርጫው የተምታታባቸው   የብልጽግና ካድሬዎች ....!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

የአድዋ በዓል እና ምርጫው የተምታታባቸው   የብልጽግና ካድሬዎች ….!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

 አሁን ማን ይሙት አድዋና አብይን ምን አገናኛቸው? አደዋን ለአደዋ ጀግኖች ትተው አብይን ከአቻው ጋር ቢያሰልፋት ለሱም ክብር ነው። በግራና በቀኝ የተለጠፉትን ፎቶዎች ስታዩ አብይ ከአድዋው ጀግና ከደጃዝማች ከባልቻ አባነፍሶ ጋር ለቀጣዩ ምርጫ ለውድድር የቀረቡ ነው የሚመስለው። በጦቢያ የግጥም ምሽት የአድዋን በዓል ድንቅ በሆነ ልዩ ዝግጅት አክብሬ እና በሀሴት ተሞልቼ ለመድረኩ አዘጋጆች ያለ የሌለ ምርቃቴን አሟጥጬ እቤቴ ስገባ ይሄን ጉድ አየሁ። ልሳቅ እንጂ በስንቱ ተቃጥሎ ይቻላል።

ታሪክን ትሰራዋለህ እንጂ አንዴ የተሰራን ታሪክ በጉልበት አትቀይረውም…!!!

ወያኔ ተንደርድራ ገብታ መውጫ የተቸገረችበትን የክህደት ቁልቁለት ብልጽግናዎች ባትሞክሩት ጥሩ ነው። ከቻላችሁ ታሪክ ሥሩ። ካልሆነላችሁም እንዲሁ በክብር እለፉ። በአጥንት እና በደም የተመሠረተን ታሪክ ለመቀየር መውተርተር ግን የወያኔን ውድቀት በጊዜ መመኘት ነው የሚሆነው።

ባየሁት ፎቶ ስቄ ሳበቃ እንደገና መናደድ ጀመርኩ። በእውነት አሳፋሪ ድርጊት ነው። ካድሬ ነውር የሚባል ነገር አያውቅም። ከትላንትም፣ ከዛሬም፣ ከነገም ጋር የሚጣላ ካድሬ ብቻ ነው። እባካችሁ ከወደቁት ተማሩ።

Filed in: Amharic