>

"...ሀገር ስታምጥ!" የሁላችንም ታሪክ ነው ብታነቡት ታተርፋላችሁ....!!!" እስክንድር ነጋ- ከቃሊቲ

“…ሀገር ስታምጥ!” የሁላችንም ታሪክ ነው ብታነቡት ታተርፋላችሁ….!!!”

እስክንድር ከቃሊቲ

ቀለብ ስዩምን ለማወቅ የቻልኩት የኢትዮጵያ ህዝብ ግንቦሩን ለጥይት በመሰጠት ገ ዢዎቻችን ሳይወዱ በግዱ 2010 ዓ.ም ከእስር ቤት እንዲለቁን  ካስገደዳቸው በኃላ ነበር ። ያሳለፍነው  የእስር ዘመን በእጅጉ አድካሚ የነበር በመሆኑም ብዙዎች ከእኛ በላይ መሰዋት የሆነለት ዲሞክራሲ እና ከእስር መለቀቅ እውን አለመሆኑ ቀጣይ ትግል እንደሚጠይቅ በመተማመን ጊዜ አልፈጀብንም በዛ መንግድ ተጉዘንም ይሄው አሁንም ቃሊቲ እስር ቤት እንገኛለን ።
ይህች ኢትዮጵያዊት ጀግና ሴት በዚህ እስር ቤት ሁና የፃፈችውን ይህን መፅሐፍ ለማንበብ ዕድሉን ባላገኝም መነበብ የሚገባው መፅሐፍ መሆኑን አልጠራጠርም ። የእሷ ታሪክ የህዝብ ታሪክ ክፋይ ነውና ። የዚችን ዕልፈት ጀግኒት ታሪክ እንድታነቡት በታላቅ ትህትና የምጋብዛችሁ ብዙ ቁምነገር እንድምታገኙበት በመተማመን ነው ።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት
                        እስክንድር ነጋ
                   ( ከቃሊቲ እስር ቤት)
Filed in: Amharic