>
5:26 pm - Thursday September 17, 4043

የባንዳነት የክፋት ጥጋችሁንማ አንረሳውም...!!!  (ሙክታሮቪች አስማኖቭ)

የባንዳነት የክፋት ጥጋችሁንማ አንረሳውም…!!! 

ሙክታሮቪች አስማኖቭ

ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት ልንሰራ ነው፣ ሲሚንቶ መንግስት ይልክልናል ተብለን ሶስት ወር ሙሉ አንድ ጉድጓድ አስቆፈሩን። 
እኛ ጉዳችንን ሳናውቅ “አይበቃውም ወይ?” ብለን እንጠይቃለን። “ገና ነው ቆፍሩት” እያሉ አለቆቻችን ያዝዙናል። በመሰላል እየገባን አፈር እየተቀባበልን ቆፈርነው። ለካንስ እኛን በዘር መርጠው ለሚገድሉን የጅምላ መቃብራችንን ኖሯል ሲያስቆፍሩን የነበረው። እግዚአብሄር ግን ውጤቱን ቀየረው!!!” 
በቦታው የነበረ ወታደር የነገረኝ!
ከነዚህ ከይሲዎች ጋር የምታለቅሱ እፈሩ። የሰሜን እዝን እንዲህ ነው የዛሬ አራት ወር የከዱት።
መዋሸት የነሱ ተፈጥሮ ነው። መዋሸት ታክቲካቸው ነው። ውሸት ብልጣብልጥነት ነው። ማመን መታመን ቂልነት ነው።
የሰሜን እዝን አንበጣ እንዲያባር ካስደረጉ በኋላ፣ የምስጋና ምሽት ብለው እራት ጋብዘው። አዳክመው። ጠጣ ድገም ብለው። መሳሪያውን ወደ መጋዘን አስገብተው የጥይት እሩምታ የከፈቱበት ልክ በዚህ ሰዓት ነው።
ከአራት ወር በፊት።
አንድ ከዚህ የጥይት እሩምታ በተኣምር የተረፈ ወታደር የተናገረውን ነገር በፍፁም አልረሳም።
“አብረን እራት ሁለት ሰዓት አከባቢ የበላን የትግራይ ተወላጅ ወዳጄ ወታደር፣
አምስት ሰዓት ወደ እኔ ሲተኩስ አየሁት።
ይህ መከዳትን ማመን አልቻልኩም”
ይህን አሳፋሪ ታሪክ አብሮ ለመኖር ብለን ብንደብቅ ጭራሽ ተበዳይ ይኮንልኛል?
አንረሳም! 
በፍፁም!
ባንዳ!!!!
Filed in: Amharic