ይግጠመው በሀሳብ የሚሻል ሰው ካለ፤
ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
አዕምሮ አስጨንቆ
አሳስቆ ያወቅነው፤
ይጫወትብናል
እየተጫወትነው።
እዚያ ማዶ ሆኖ፤
በሥም ተሸፋፍኖ።
አሊያም ተመሳስሎ
እስ ስት ባሕርይ ይዞ፤
ኮንከር ሴካ መዝዞ።
አይደለም ጨዋታው
የሐገር ገበታው።
ብላኝ እና ልብላህ
በፍጹም አይደለም፤
አስብ ነው ሚስጥሩ
ተሻለም አልተሻለም።
እናም አንስተህ
መጓዝ ስትጀምር፤
ጠላት ይገጥምሃል
አስብበት የምር።
ይሄ ጨዋታ ነው
ባንድ ቦርድ የሚታይ፤
የጀምርነው አለ
በሕይወታችን ላይ።
የሌባና ፖሊስ
የሚጥሙ ዓይነቶች፤
ሚስጥራቸው ረቂቅ
አወይ የልጅነቶች።
ይሄ ግን ያመራል
ከጨዋታም በላይ
ብዙ ያመራምራል።
ሕጉንና መንገዱን
ቀድሞ ማወቅ ደግሞ፤
መገፍተር መጣል ነው
ባሸናፊነቱ
ዘውዱን ተሸልሞ።
ይሄው ነው ጨዋታው፤
የሐገር ገበታው።
ከጓዳ ተቀምጦ ከኮምፒዩተር ላይ፤
የሚጨበጥ የለም በገሃድ የሚታይ።
አዎን ተገቢ ነው ዘምኖ መግጠሙ፤
ስልጣኔን መሻት ኑሮን ማጣጣሙ።
ሆኖም በኀላፊነት የሕዝብ አደራ ይዞ፤
ችግሮችን መፍታት አይሆንም ተክዞ።
እንኳን አገርና ቤተሰብም ቀርቶ፤
ራስንም መምራት ይጨንቃል አውርቶ።
እናም ተጠንቅቀን እያንዳንዷን ጉዞ፤
ስንራመድ እንወቅ ምን ያመጣል ይዞ።
የጨዋታው ምጥቀት አዕምሮ ፈታኝ ነው፤
ይጫወትብናል
እየተጫወትነው።