>

ለ30 ዓመታት በአማራ ደም የራሰው የወለጋ ምድር....!!! አንሙት አብርሃም

ለ30 ዓመታት በአማራ ደም የራሰው የወለጋ ምድር….!!!

አንሙት አብርሃም
*….ሸረሪቷን ጨርሰን የሸረሪት ድሯን እየጠረግን ነው ከተባለ ወዲህ ወለጋ የማይቋረጥ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየተደረገ መሆኑን እየሰማን ነው!!!
 
ታጥቆ የገባውን የኦነግ ጦር ማስወገድ ያልፈቀደው የሽመልስ አብዲሳ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት ፡ አማራ አርሶአደሮችን ትጥቅ ፍቱ በማለት የክልሉ ፖሊስ ሳይቀር እንዲወጋቸው እያደረጉ ነው።
ገዳይ ታጣቂ የተሠማራባቸው አርሶአደሮች ደግሞ ትጥቅ ከምንፈታ ሞትን እንመርጣለን ብለዋል። በወለጋ ከተሠማራው ጠላት ሊታደጋቸው ያልቻለ ክልል ትጥቅ ፍቱ ማለት እንግደላችሁ ማለት እንጂ ሌላ ገፅታ የለውም።
[ስልጣን ላይ ያለው ከነ ሌንጮ ለታ አመራር የቀጠለ የአማራ ዘር ማፅዳት እየመራ ያለ አዲስ ትውልድ ነው። አማራን የመስበር ሕልማቸው አካል ነውና ያን ለማረጋገጥ እያስፈፀሙት ያለ ነው።]
ዛሬም ወያኔን ሰበብ አድርገው ለመቅረብ እንደማያፍሩ ቢታወቅም ኦነግ-ሸኔ በኦሮሞ ብልፅግና የሚቀለብ የኃይል ሚዛን አስጠባቂ ጦር መሆኑን መገመት ስህተት አይደለም።  እያንዳንዱን ስሌትና ሁኔታ አጢነው።
አማራ የቸገረው ሀሞት ያለው ፣ አማራ ሆኖ መቆም የሚችል አመራር ነው።  በማጎብደድ ጀርባው የጎበጠ አንደበቱ የታሠረ  የጠላት አሽከር ሲወክልህ መቆጣትም ማዘንም የማይችል ፡ የማትችል ያደርግሃል።
 መናቅን ያለማምድሃል። ዘርህ ተመርጦ መገደልህን ያመቻምቸዋል።   “ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ”!
የዚህ አመራር አስተሳሰብ ወራሹ ልሒቅም ከአገርቤት እስከ ውጭ አገር ዝም ብሏል። የወያኔ ደጋፊ ልሒቅ ግን የአውሮፓ ሕብረትና UN ደጆችን እያጨናነቀ ይገኛል። አማራ እየተጨፈጨፈ ዝም ብሏል። ዝም በል የሚልህ ይበዛል
የጠላቶች የፍርድ ቀን ሩቅ አይደለም!
Filed in: Amharic