>

ተቆርጦ የቀረው የህወሃት ግንባር ...!!! (መስቀሉ አየለ)

ተቆርጦ የቀረው የህወሃት ግንባር …!!!

(መስቀሉ አየለ)

ዮሃንስ አብራሃም ይባላል። የህወሃቱ ጎበዝ አለቃ ሰዬ አብርሃም የወንድም ልጅሲሆን ተወልዶ ያደገው እዚያው አሜሪካ ውስጥ ነው። ትምህርቱን እንደጨረሰ የፑብሊክ ኢንጌጅመንት እና ኢንተርጋቨርመንታል አፌይርስ ዳይሬክተር፣ የባራክ ኦባማ አማካሪና የቅርብ ጓደኛ የነበረችው ቫለሪ ጃሬት ጋር እንዲሰራ የተመቻቸለት ገና በጠዋቱ ነበር።
ዮሃንስ በመጀመሪያው ዙር የኦባማ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት የካውካስ አካባቢ አስተባባሪ በመሆን ጀምሮ በሂደት ቀስ እያለ ወደላይኛው መሰላል የወጣ ሲሆን የባይደን አስተዳደር ወደ ኋይት ሐውስ ሲገባ የችፍ ኦፍ ስታፉን ቦታ ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በአሁን ሰዓት የባይደንና ሃሪስ አድሚንስትሬሽን የፖሊሲ ትግበራ ውስጥ በኤክስኪዩቲቭ ይሬክተርነት ቦታ ላይ ያገለግላል።
ዛሬ የህወሃት ፍርክስካሾች ከደሃ ህዝብ ዘርፈው በውጭ ያከማቹትን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ጭምር በማንቀሳቀስ፣ የነጭ ሎቢ ጭምር በመቅጠርና ለዘመናት የውስጥ ቁስል ሆነውብን ከኖሩት እንደ ጀንዳ ፍሬዘር ከመሳሰሉት ነውረኞች ጋር  በመሳለጥ የመጨረሻውን እስትፋቻቸውን የሚያወራጩት እንደ ዮሃንስ አብርሃም አይነቶቹን ጭምር በመጠቀም በመሆኑ የባይደን አስተዳደር በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ይህ ችግር በከፋ መልኩ መቀጠሉ ስለማይቀር በዚህ ግምባር በኩል የተጠና እስትራቴጅ ሊኖር ግድ ነው።
እንግዲህ ይህ ሰው በላ ስርዓት ለእሩብ ክፍለ ዘመናት ያህል የአገሪቱ መንበር ላይ ፊጥ ብሎ በማንነታችን ላይ ሲዘምትና የእናት ኢትዮጵያን ቀሚስ ጭምር ገልቦ በአህዛቦች ሲያስደፍር “ከፊደል ገበታ የተወለድን ነን” ያሉና ፈረንጅኛ መናገር የሚቀናቸው ፖለቲከኞቻችን በአሜሪካኖቹ ክንድ ሊሰበር ካልቻለው የቪየትናሙ ሆችሜን ይልቅ የጋንዲንና የማንዴላን ታሪክ ያለቦታው እየጠቀሱ ህዝባችንን ሲያዘናጉና በደነዘዘ ቢላላዋ ሲያስዝገዘግዙን ነፍሳችን አልወጣ ብሎ እዚህ ብንደርስም ቅሉ ነገር ግን በዚህ መሃል እረጅም እድሜ ያገኙት ደደቢታውያን በየቀኑ ሲተክሉት የኖሪትን ጋሬጣ እንዲህ ስር ሳይሰድ ለመንቀል እንችልባቸው የነበሩ  ወርቃማ ዓመታቶች የውሃ ላይ ኩበት ሆነው ቀርተዋል።
በዚህም የተነሳ ሜዳው የተከፈተለት ጉጅሌ ከአገር ውስጥ አልፎ ዛሬ ጥፍሩን ያልተከለባቸው አለማቀፍ ተቋማት፣ የውጭ ኤምባሲዎች፣ ሲቪኪ ኢንስቲቱሽንስ፣ የውጭ መገናኛ ብዙሃን የሉም ማለት ይቻላል:: Red Cross,  White House,  US Aid, UK Aid, UN, UNHCR, UNISICO, WHO, Amnesty International, Human Rights Watch, BBC, Reuters, New York Times, Washington Post etc..etc..etc ጥቂቶቹ ናቸው።  ዛሬ እነዚህ በየቦታው የተሰገሰጉ የጉጅሌው ትርፍራፊዎች በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየታገዙ ህወሃትን እንደ አላዛር ከመቃብር ሊጠሩት ይሞክራሉ።
Filed in: Amharic