በአዲስ አበባ የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል ተመሰረተ…!!!
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ በአንጋፋዋ የኪነጥበብ ባለሙያ ዓለምፀሃይ_ወዳጆ መስራችነት “የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል” ተመሰረ፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ለባህል ማዕከሉ አገልግሎት እንዲውል ከዛሬ 117 ዓመት ተገንብቶ የቆየውና በቅርስነት የተመዘገበውን የቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤልን መኖሪያ ቤት ለጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል አስረከበ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሐግብሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ የትላንቱ ትውልድ ያስቀመጣቸውን መልካም አሻራዎች እንዳይደበዝዙ ፣ከነጥንታዊነታቸው እና ፋይዳቸው እንዲሁም ከነታሪካቸው ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል ብለዋል።
“በከተማዋ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች በቅርስነታቸው ብቻም ሳይሆን በዘመን ተሻጋሪነታቸው ታሳቢ ተደርገው ልንጠቀምባቸውና ልንከባከባቸው ይገባል
አዲስ አበባን እንደስሟ አበባ ለማድረግ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ያሉት ወ/ሮ አዳነች ለዚህም ስኬት የኪነጥበብ ፋይዳን ማጉላትና ማበረታታት እንዲሁም የባህል ማዕከላትን በማስፋፋት መሆኑ ተናግረዋል ።
ታዋቂዋ የኪነጥበብ ባለሙ
ያ አለምጸሃይ ወዳጆ ባለፉት 20 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ የነበራትን ልምድ በመያዝ የባህል ዘርፉን ለማሳደግ፣ ቅርሱን ለማስተዋወቅ እና በኪነጥበቡ ዘርፍ የዳበረ እና የበለጸገ ትውልድ ለማፍራት እያደረገች ላለችው አስተዋጽኦ ምክትል ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቅርሱ እድሳት የሚውል የሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተየጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተካሂዷል።