>

በሕወሓትና ኦነግ/ኦህዲድ መቃብር ላይ ኢትዮጵያ ታብባለች! ሰሎሞን ንጉሡ (ከአዲስ አበባ)

በሕወሓትና ኦነግ/ኦህዲድ መቃብር ላይ ኢትዮጵያ ታብባለች!

ሰሎሞን ንጉሡ (ከአዲስ አበባ)


በቅድሚያ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን (2013ዓ.ም) እንደመሆኑ ለኦርቶዶክሳውያን “እንኳን ለአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ዝክረ በዓል አደረሳችሁ፤ ከጻዲቁ አባታችን ረድኤት በረከት ያሳትፋችሁ” ማለት እወዳለሁ፡፡

ከሌሊቱ 11፡00 ሰዓት ባልተለመደ አኳኋን ከአልጋየ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ፡፡ ለበርካታ ዓመታት የሰቀልኩትንም ብዕሬን አነሳሁ፡፡ ውስጤ ሹክ ያለኝን እንደሚከተለው አስቀመጥኩ፡፡ የምላቸው ነገሮች ባይያያዙ አትፍረዱብኝ፤ምክንያቱም የሀገራችንም ሆኑ ዓለም አቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ሁሉ ውስብስብና ተያያዥነት የሚጎድላቸው ናቸውና፡፡

በሚዲያው ረገድ እግዜር ሀገራችንን ጨርሶ አልበደላትም፡፡ ባለትንቢቱ ሰባተኛው ንጉሣችን አፄ ኤዲፐስ ቦካሣ የተባለው “ወላድ አትይህ” ሊባል የሚገባው የዘመናችን ስፊንክስ የመተንፈሻ አካሎቻችንን ሁሉ ለቁጥጥርና ለአፈና እንዲያመቸው ኢትዮሳት ወደሚባል የኢንሳ ቋት ሰብስቦ ማንቁርታችንን ሊጠረቅም ቢታትርም ዕድሜ ለነመረጃ ቲቪ እስካሁን ብሶታችን እነሱ በፈለጉት መንገድ ታፍኖ አልቀረም፡፡ ካሉን ጥቂት ድረ ገፆች ላይ ይህ ቲቪ በነዘመድኩን በቀለና ኢትዮ60 አማካይነት “ነጭ ነጯን” “እግዚዖ! ምኖቹን ጉዶች ነው የሰጠኸን!” እያልን በአግራሞትና በሰቀቀን እየኮመኮምን እንገኛለን፡፡ ለዚህ ማስታወሻየ የወዲያው ምክንያትም ትናንት ማታ (ቅዳሜ) የተከታተልኩት አጃኢብ የሚያሰኝ የኢትዮ60 ግሩም ዝግጅት ነው፡፡ የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ይህን ቲቪ መከታተል እጅግ በጣም ጠቃሚ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መጠቆም እፈልጋለሁ – ድረ ገፆችንና አንዳንድ ዩቲዩበሮችንም ጭምር፡፡ አንዳንድ የቀድሞ “ተራማጅ” አስተሳሰብ የነበራቸው ሕዝባውያን የሚዲያ አካላትና አባላት ጥቅም ለውጧቸው ይሁን ሕዝባዊነት ሰልችቷቸው አላውቅም ወደ ተረኛው መንግሥት ጠጋ ጠጋ እያሉና እውነትን እየተጠየፉ መምጣታቸውን እየታዘብኩ ነው፡፡ አይፈረድባቸውም፡፡ የኢትዮጵያ “አይረን ሌዲ” ወ/ት ብርቱካን ሚዲቄሣ ወደሚገማው የዘረኝነት አዘቅት በወረደችባት ሀገር እነእንትና ቢለወጡ ብዙም አይገርምም፡፡ ሆድ መጥፎ ነው፡፡ “እንኳንስ በጀርባችን አልሆነ፤ ገፍትሮ ገደል ይከተን ነበር” ብሏል ደራሲ ብርሃኑ ዘሪሁን በአንዱ መጽሐፉ፡፡ በርግጥም ብዙ ዜጎች ተስፋ እየቆረጡ አቢያዊ እየሆኑ ነው፡፡

የ“ነጭ ነጯን” የመረጃ ቲቪ መርሐ ግብር አዘጋጅ ዘመዴ ሰሞኑን የጻፋትንና በፌስቡክ መንደር ስትዘዋወር ያገኘኋትን አንዲት ጽሑፍ አነበብኩ፡፡ ጥሩ ናት፡፡ ግን ተስፋን የምታጨልም መሰለኝና በርሷ ላይ አንድ ነገር ማለት እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው አንዱ መነሻየ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

ኤዲፐስ ንጉሣችንን በምን እንመስለው?

ስለዚህ የብዙ ብልሹ ስብዕናዎች ውሁድ ጎልማሣ ንጉሣችን ብዙ ተብሏል፡፡ እነሀብታሙና ኤርምያስም በቀላል አልያዙትም፤ ልጅ ይውጣላቸው፡፡ ምንን ምን ካላሉት ነው ነገሩ፡፡ እኔ ደግሞ ይህን ለኢትዮጵያ ውድመትና ትንሣኤ ዋና ምክንያት የሆነ “ሰው” ሳስብ በትንሹ የሁለት ሰዎች የተለያዩ ታሪኮች ትዝ ይሉኛል፡፡ በተቻለ መጠን እንደወረደ ስለማቀርባቸው ለሚስተዋልባቸው “ብልግና” ከወዲሁ ይቅርታ ማለት እወዳለሁ፡፡ የታሪኮቹ ትምህርታዊ ይዘት ግልጽ ሊሆን የሚችለው በግልጽ ሲነገሩ ነውና፡፡ ሁለቱም እውነተኛ ገጠመኞች እንደሆኑ ሰምቻለሁ፤ ከታሪኮቹም ይህን መገመት አይከብድም፡፡

  1. በአንድ አካባቢ አንድ ዲያቆን ሚስት ይታጭለታል፡፡ አይደርስ የለም የሚፈራው ሠርግ ደረሰ፡፡ ግን ልጁ በራሱ የሚተማመን አልነበረም፡፡ “ህጓን መውሰድ አልችልም፤ ‹ዕቃየ› ያዋርደኛል” ብሎ በብርቱ ያምን ነበር፡፡ በፖለቲካው “ፕላን ቢ” እንደሚባለው እርሱም በሠርጉ ዕለት የሙሽራዋን ድንግልና ባለመገሠሡ እንዳይዋረድ በመሥጋት የርሱን ተፈጥሯዊ “ዕቃ” የሚመስል ነገር ከእንጨት ሠራ፡፡ ያን አርቲፊሻል የወንድ ብልት በቅባት እያራሰ በግሩም ሁኔታ አለስልሶ ለሠርጉ ዕለት ለአግልግሎት ዝግጁ እንዲሆን አደረገው፡፡ ሚዜዎች በጫጉላው ዙሪያ አሰፍስፈው የምሥራቹን መጠባበቁን ተያያዙት፡፡ አጅሬ ሥነ ልቦናውን በ“አልችልም” ቀድሞውን አሸንፎት ስለነበር ክፉኛ በመፍራቱ የራሱ ዕቃ ከዳውና ወደ ሆዱ ገባ፡፡ ሙሽራው በሚገባ ወደተዘጋጀበት ፕላን “ቢ”ው በቀጥታ በማምራት ልጂቷን በእንጨት አበላሻት፡፡ ሙሽሪት ነገሩ ገብቷታል፡፡ ለዓመታት የጠበቀችው ክብር በሕይወት አጋሯ ሰው ሳይሆን በግዑዝ ነገር እንደተወሰደ ቁጭቱ እያንገበገባት ተረድታዋለች፡፡ ሌሊቱ ሲነጋ የዲያቆኑን ጉድ ለሁነኛ ሰው ተናግራ ዐይኑን አልይ በሚል ትታው ጠፋች፡፡ አቢይ አህመድም ኢትዮጵያን በማይገባት(‹ገ› ትጥበቅ) የአመራር “ጥበብ” እያሰቃያት የሚገኘው ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ 
  2. አንድ ሀብታም ሽማግሌ ቀንቷቸው ሁለት ሴቶችን አቅፈው ተኝተዋል፡፡ ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ይባላል አይደል? ከዚያላችሁማ … ሁለቱም ሴቶች እየተፈራረቁ “ማንኛችንን ይበልጥ ታፈቅረናለህ?” እያሉ ለመልስ አስቸጋሪ በሆነ ጥያቄ ያዋክቧቸው ያዙ፡፡ ሰውዬው ሁለቱንም ይወዷቸዋል፡፡ አፍ አውጥተው “አንቺን” ቢሉ ሌላዋን ሊያስቀይሙ ምናልባትም ሊያጧት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ዘዴ መፈለግ እንዳለባቸው ተረዱ፡፡ እንዲህም አደረጉ፡፡ በጀርባቸው ተኙ፡፡ ሴቶቹም ልክ እንደርሳቸው በጀርባቸው እንዲተኙ መላ ዘየዱ፡፡ ከዚያ እጆቻቸውን ወደ ሴቶቹ ላኩና የጥያቄውን መደገም መጠባበቅ ያዙ፡፡ ምርጫቸውን ባለመግለጻቸው የከነከናት አንደኛዋ ሴት ያን መከረኛ ጥያቄ ጠየቀች፡፡ እሳቸውም በሚገባ ተዘጋጅተውበት ነበርና በግራና በቀኛቸው የተጋደሙትን ሁለቱንም ሴቶች በአንዴ ቁንጥጥ እያደረጉ “አንቺን ነው የማፈቅረው!” በማለት ምርጫቸውን ገለጹላቸው፡፡ ሁለቱም ሴቶች በቁንጥጫ የተላለፈውን መልእክት በፀጋ ነው የተቀበሉት፡፡ ሁለቱም ያሰቡት አንድ ዓይነት ነው – “ያቺኛዋ እንዳትቀየማቸው ነው በዚህ መልክ እንደሚያፈቅሩኝ የገለጹኝ” አሉና ተጽናኑ፤ ሁለቱም በአንድ ቅ ጽበት እንደተቆነጠጡ ግን አልገባቸውም ወይም እንዲገባቸው አልፈለጉም፡፡ የንጉሣችን የአፄ ቦካሣ ሁኔታም ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ ለትግራይ ጊዜያዊ መንግሥትና ለአማራ ክልል መንግሥት እንደዚሁም ለዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ በወያኔ ተዘርፈው በተጋሩ ለ30 ዓመታት ሲቀጠቀጡ ስለነበሩ የወልቃይትና ራያ ግዛቶች የሚናገረውን እዚህ ላይ ያስቧል፡፡ አፄው  በአማርኛ ደሴ ላይና በኦሮምኛ ባሌ ወይም ኦቢኤን ላይ የሚናገረውን ያስታውሷል፡፡ ብላቴናው መናገሩን እንጂ ምን እንደሚናገርና ስለሚናገረው ነገር የቀጥታም ሆነ የጎንዮሽ ጉዳት የሚያውቀው የለም፤ የበቀቀን ተፈጥሮም ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ሰውዬው የራሱ የሚባል የስብዕና መገለጫ የለውም – የሁሉምነሽነት የራስ መገለጫ ነው ካልተባለ በስተቀር፡፡

ልጨርስ ነው፡፡ ዘመዴ በትናንቱ ጦማሩ በኢትዮጵያ በቅርቡ ስለሚከሰቱ ሁኔታዎች ግምቱን ሲገልጽ አንዳንድ ከነባር ትንቢቶች የሚጣረሱ ነገሮችን ጠቁሟል፡፡ ከሚታየው ነገር ተነስቶ እንዲያ ቢል ቅር አይለኝም፡፡ እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡

“የሚወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል” ይባላል፡፡ “የማያድግ ልጅ በአባቱ እንትን ይጫወታል” ወይም “እንትኑ ትልቅ ነው” ይባላል፡፡ ለማንኛውም ኦነግ/ኦህዲድ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ከዛሬ ሦስት ዓመታት ወዲህ እያደረገ ያለው እያንዳንዱ ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት አንዳች ሚና የሚጫወት ስለመሆኑ የሚያውቅ ያውቃል፡፡ እርግጥ ነው – የስንሻውና የታንጉት መታረድ ለምንም ዓላማ ይሁን ወደውና ፈቅደው የሚቀበሉት ነገር እንደማይሆን አውቃለሁ፡፡ ቢሆንም ክርስቶስም ልክ እንደንጹሓን አማሮች ሁሉ አላንዳች አበሳው በኦነግ ቄሮ መሰል የዚያን ዘመን መንጋ በስቅሎ ስቅሎ የደቦ ፍርድ በስቅላት ተገድሎ ዓለምን እንዳዳነ ሁሉ በነአቢይና ሽመልስ ትዕዛዝ በወለጋና በመተከል በየቀኑ የሚያልቁት አማሮች ደምም ኢትዮጵያን ከገባችበት የአጋንንት አገዛዝ ነጻ እንደሚያወጣ ብናምን ከታሪክም ከሃይማኖትም ከእውነት ሚዛንም አኳያ ትክክል ነን፡፡ አንድን ድል መስዋዕትነት ይቀድመዋልና፡፡

ስለሆነም እንደኔ ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም፡፡ የሕወሓትና ኦነግ/ኦህዲድ እንዲሁም የአጃቢዎቻቸውና በአዲሱ የነሀብታሙ አገላለጽ የውታፍ ነቃዮቻቸው ድርጊቶች የሚነግሩን የኢትዮጵያ ነጻነት ቅርብ መሆኑን ነው፡፡ የሚሠሩት ግፍ ሁሉ ምናልባት እነሱም እንደሚያስቡት ከደመና በታች የሚቀር አይደለም፡፡ ቋቱ እስኪሞላ እንጂ ሁሉም ክፋትና የክፋት ሥራ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም፡፡ ደርግም ሆነ ወያኔ ከዚህ አላመለጡም፡፡ እነዚህኞቹ ደግሞ ከሁሉም የከፉ በመሆናቸው ማንኛውም ታሪካዊና መለኮታዊ ቅጣት በብዛት ተከምሮ ይጠብቃቸዋል፡፡ አሁን እርግጥ ነው ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው ነው፡፡

በሦስት ዓመታት ውስጥ የሠሩት ግፍና በደል ወያኔ በ40 ምናምን ዓመታት ውስጥ ከሠራው ግፍና በደል ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ ግፍና በደል ምን ሊያስከትል ይችላል ብለን ስንጠይቅ፡-

  1. ከአክራሪ ትግሬና ከአክራሪ ኦሮሞ እንዲሁም ከሆዳም አማራና ከሆዳም ሌላ ዘውግ ውጪ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ አንድ ማዕከል ይስባል፡፡ “እነዚያንም አየናቸው፤ እነዚህንም አየናቸው፤ ሁለቱም የከፉ የከረፉ ናቸው፡፡ ስለዚህ የሚያዋጣን አንተ ማነህ አንቺ ማነሽ ሳንባባል እንደሰውና እንደዜጋ በአንድነት የምንኖርበት ኢትዮጵያዊነት ነው” ወደሚል አማራጭ ይመጣል – ሕዝቡ፡፡ 
  2. ፈጣሪ ፈጥሮ አይረሳም፡፡ የተራበንም የጠገበንም ወቅቱን ጠብቆ ያስታውሳል፡፡ ይህች ኢትዮጵያ ደግሞ በርግጥም የቃል ኪዳን ምድር ናት፡፡ ያጠፋናት እኛው ነን፡፡ ያበላሸናት እኛው ነን፡፡ ሃይማኖታችንን እኛው ራሳችን አረከስነው፡፡ በየቤተ እምነቶቻችን የሚታየውን የነቢብና የገቢር ልዩነት የምናውቀው ነው፡፡ እግዚአብሔርን በአፍ እያወደስን በልባችን ግን ሰይጣንን እናመልካለን፡፡ ስለዚህ ለሀገራችን ጥፋትና ውድመት አነሰም አደገም የእያንዳንዳችን አስተዋፅዖ አለበትና ወያኔንና ኦነግን ወይም እነዚህን ኅሊናቢሶች ጃዝ ብለው የላኳቸውን ዓለም አቀፍ የዐውሬው መንግሥት እንደራሴዎች ብቻ መውቀስ የለብንም፡፡ “ቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ይላሉ” ይላል አራዳ ሌባ፡፡ በተቀደደልን ቦይ መፍሰስን ከመረጥን የተለዬ ውጤት መጠበቁ የዋህነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ኃይል የእግዚአብሐየር ነውና የርሱ ኃይል በቅርብ ይከሰታል፤ የማመንና ያለማመን ጉዳይ የራሳችን መብት ነው፡፡ 
  3. ትልቁ ቁም ነገር ኢትዮጵያ በልጆቿ ተጋድሎ ከባርነት ነፃ ትወጣለች፡፡ ከዚህ ሁሉ ትርምስና የተወሰነ ግን አስፈሪ ዕልቂት በኋላ ስለሀገራችን ቀድመው የተነገሩ መልካም ነገሮች ሁሉ እውን ይሆናሉ፡፡ እኛ ሕዝቡ ግን ቆም ብለን ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ ከክፉ ሥራም እንራቅ፡፡ በተለይ የምንታማበትን ምቀኝነትንና ተንኮልን፣ የርስ በርስ መጠላለፍንና ሤረኝነትን እናስወግድ፡፡ በዘረኝነትና ተረኝነት አባዜ የተለከፍን ራሳችንን ከዚህ ነውር በቶሎ እናጽዳ፡፡ ሌላው ቀላል ነው፡፡ ቢገድሉን አዲስ ነገር አልፈጠሩም፤ ራሳቸውን ገደሉ እንጂ በሞታችን አልዳኑም፣ አይድኑምም፡፡ በጎጠኝነትም፣ በኑሮ ውድነትም፣ በሙስናና በጉቦም፣ በብልሹ አስተዳደርና በማይማን አመራሮችም … ሰንገው የያዙት ሕዝብ በፈጣሪ ረድኤትና እገዛ አንድ ቀን ሆ! ብሎ ከያለበት ይወጣና እንደሮማንያው ኒኮላይ ቻውቼስኮ ሰደቃቸውን ያወጣላቸዋል፡፡ ቀኑም ቀርቧል፡፡ … 
Filed in: Amharic