>

በታላቁ እስክንድር ነጋ የትግል ህይወት ዙሪያ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም...!!!

በታላቁ እስክንድር ነጋ የትግል ህይወት ዙሪያ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም…!!!
* …. ካወቅኩት ጀምሮ የእስክንድር ህይወት በመከራ የተሞላ ነው፤ ዛሬ በሚድያ የምንሰማው በዜጎች ላይ በየእስር ቤቱ የደረሱ አሰቃቂ ታሪኮች በአብዛኛው እሱ ያለፈባቸው ፈተናዎች ናቸው…!
ባለቤቱ ጋዜጠኛ  ሰርካለም ፋሲል
 
*…. እስክንድር ፈጽሞ የማይሸነፍ ጠንካራ ልብ ያለው፤ በፍጹም ልቡ አገሩን የሚወድ የጥንካሪ ተምሳሌት የሆነ ሰው ነው፤  ለ13 ጊዜያት በግፍ ታስሯል፤ ያ ግን ከአቋሙ ዝንፍ የማያደርገው ብርቱ ሰው ነው….!
አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ
 
*…. እስክንድር ልዩ ሰው ነው፤ አንድ ጋዜጣ ብቻውን የሚያዘጋጅ ሰው ነው፤ ሲጽፍ ውሎ አድሮ የማይታክተው ነው፤ በዛ ላይ ያነባል።
ቢሮ ውስጥ ውሎ ያድራል ስለ ምቾት አይጨነቅም… ራሱ እስክንድር ሊጻፍ የሚገባው ሰፊ ታሪክ የሚወጣው ሰው ነው….!
ጋዜጠኛ አበበ ገላው
 
*…. እስክንድር በጫና እንደማይንበረከክ እኔ አይደለሁም በነጻው ፕሬስ ውስጥ ያለፉ ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው….!
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና

https://www.facebook.com/nanush.shegaar/videos/2642997592665090/

Filed in: Amharic