>

አዲስ አበባን አሳልፎ የሰጣት ኢዜማ ነው! ጌታቸው ሽፈራው

አዲስ አበባን አሳልፎ የሰጣት ኢዜማ ነው!

ጌታቸው ሽፈራው

~ኦነግ ወደ ሀገር ቤት ከገባ በኋላ በተደረገው ሰልፍ በርካታ የአዲስ አበባ ወጣቶች በ”ግንቦት  7″ ሰበብ ታሰሩ።  አሁን ጥላቻ የሚነዛው መንጋ ፀጥ ረጭ ነው ያለው። ኦነግን በእጅጉ ይፈራዋል።
~እነ ጃዋር ሞሃመድ ወጣቱን ስለት አስይዘው ሕዝብ ለ10 አመት የቆጠበበትን ቤት ሲያስቀሙ ኢዜማ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበር።
~እነ ታከለ ኡማ ከገጠር እያመጡ መታወቂያ ሲያድሉ የኢዜማ ሰዎች እነ ታከለን “በርቱ” እያሉ ነበር።
~አዲስ አበባ ለልዩ ጥቅም በየቦታው ስትቆነጠር የኢዜማ ሰዎች ቤተመንግስት እየተመላለሱ፣ ከንቲባ ፅ/ቤት እየዋሉ “ከጎናችሁ ነን” እያሉ ነበር።
~የእነ ለማ ቡድን አባል ሆኖ የኦሮሞ ብልፅግና ውስጥ አቅም እያገኘ የነበረውን፣ ድሮ ከተማዋን ሲጎዳ ሲያበረታቱት የነበረውን ታከለን ለመምታት ከጊዜው ስልጣን ካለው ኃይል ጋር ሆነው አንድ ሪፖርት እንዲያወጡ ተፈቅዶላቸዋል። እነሱ ያወጡትን ሪፖርት ግን የባልደራስ አመራሮች ቦታው ድረስ እየሄዱ ሲያጋልጡ ከመንግስት ጋር ሆነው ሲጎትቷቸው ነበር። እነ እስክንድር ለአዲስ አበባ ከገዥዎቹ ጋር ሲጋፈጡ ኢዜማ ተደርቦ ይወቅጣቸው ነበር። እነ እስክንድር በኢዜማ መንጋ “እብድ” እየተባሉ ተሰድበዋል። ለአዲስ አበባ ሕዝብ ስለቆሙ ብቻ።
ኢዜማ እነ ጃዋርን ፈርቶ፣ ኦነግን ፈርቶ አዲስ አበባን አሳልፎ ሲሰጥ በድፍረት ለአዲስ አበባ ከቆሙት ድርጅቶች መካከል ከባልደራስ ቀጥሎ የሚጠቀሰው አብን ነው። ያኔ አዲስ አበባን ገዥዎቹን “አይዟችሁ” እያለ፣ ገዥዎቹን ሲያጋልጡ የነበሩትን “እብድ” እያለ እያሸማቀቀ የነበረው መንጋ አሁን አብንና ባልደራስን በአዲስ አበባ ጉዳይ ለመውረፍ የመጣው የገዥዎቹን ተልዕኮ ይዞ ነው።
ኢዜማ  የገዥዎቹ አሯሯጭ ሆኖ በደንብ እየሰራ ነው። እነሱ እስከፈቀዱለት ድረስ የፈለገውን ያደርጋል። የኢዜማ መንጋ በራሱ ፈቃድ የሚፈፅመው ብቸኛው ነገር በአማራ ላይ ጥላቻውን መንዛት ነው። ይሁንና በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልው የኢዜማ መንጋ ሕዝብን ስለጠላ ስሜታዊ መሆን አያስፈልግም። ኢዜማን በራሱ ስሜት ሄዶ መታገል አያዋጣም። እሱ አማራን ስለጠላ “አማራ ክልል አትደርስ” ሊባል አይገባም። ይህን በእጅጉ ይፈልገዋል። አንደኛው የሚፈልገው የሚጠላውን አማራን ስህተት አሰርቶ ዘመቻ ማቀጣጠል ነው። ኦሮሚያ ክልል ስለተገደለው አመራሩ የረባ መግለጫ አልሰጠም። አማራ ክልል ላይ ባነር ቢቀደድበት ግን አመቱን ሙሉ መቀስቀሻ ያደርገዋል። ስለሆነም አማራን ለሚጠላው ኢዜማ ከማጋለጥና ከምርጫ ካርድ ውጭ ሌላ የአፀፋ መልስ አያስፈልገውም።
 ኢዜማን መቅጣት የሚቻለው እሱ መጡባችሁ ብሎ እንደሚቀሰቅሰው “መጣብህ፣ እንዳይመጣ” ተብሎ አይደለም። ኢዜማን መቅጣት የሚቻለው በአስተሳሰቡ ነው። ባሕርዳርም፣ ጎንደርም፣ ደሴም፣ ደብረብርሃንም፣ አዲስ አበባም ይኑር። ጥላቻውን ለሕዝብ እየነገርን በምርጫ እንዲቀጣ እናደርጋለን እንጅ ጥላቻን በጥላቻ መልሰን እንዲያሸንፍ አናደርገውም።
አማራውን እየጠላ አዲስ አበባን እየሸጠ የከረመበትን እያጋለጥን ከሕዝብ ልብ እንዳይደርስ እናደርገዋለን እንጅ  እሱ “አማራ መጣባችሁ” እንደሚለው አይነት አካሄድ ሄደን አንሸነፍለትም።
ቀላል የቤት ስራ ለኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ!
የኢዜማ አመራሮች በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ተሰብስበው ሊይዙት የነበረውን አቋም ጠይቁ እስኪ። ስብሰባው ለምን ያለ ውሳኔ ተበተነ? ይችንም ጠይቁ።
ጉዳዩን እያወቅን ዝምታን የመረጥነው ለምን መሰላችሁ?
1) ይህን ምርጫ እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማለፍ ያስፈልጋል።
2) መተባበር ባይቻል እንኳ መጓተት አያዋጣም በሚል
3) ኢዜማም ውስጥ ቢሆን አልፎ አልፎ ደሕና ሰዎች ስላሉ ነው።
የሆነ ሆኖ ኢዜማ በተናካሽነቱ ከቀጠለ ይህንም ጉዳይ በግልፅ  እናወጣዋለን!
ለተናካሽነቱ ማሳያ:-  ‘ ባልደራስ አማራ ስለሆነ አትምረጡት!” ሌላም ሌላም በማለት ለአማራ ያላቸውን የቆየ ጥላቻ ገሃድ እያወጡት ነው:: 
 
እስከዛው ግን ከእኔ ይልቅ የሚቀርቧችሁን አለቆቻችሁን፣ የምታደንቋቸውን አመራሮች በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ምን አይነት አቋም ይዛችሁ መግለጫ ልትሰጡ ነበር? ለምን ቀረ?  ብላችሁ ጠይቋቸው። ሕሊና ካላችሁ እንደሰማችሁ ትቀየሟቸዋላችሁ። የምታከብሯቸው ጥቂት ሰዎችም ይኖራሉ።
Filed in: Amharic