ዶ/ር ዮናስ አበራ
*….የዛሬ ዓመት ይህችን ፅፌ ነበር፤ ዛሬ ነገሮች ጭራሽ በ 10 እጥፍ ብሰዋል!!
ዛሬ 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሃገር “ለአማራ ዶክተሮች የስራ መስክ የለኝም” ወደሚል ቧልት ዘቅጣለች… ዛሬ ሐኪም ሰልፍ ወጥቷል ፤ ነገ መሐንዲስ፣ መምህር ይቀጥል!!!
* * *
ባንተቤት መኪና እና ቤት መግዛት ያልቻለ ኢኮኖሚስት ምሁር አይደለም፤ ቀበሌ ያላስተዳደረ የፖለቲካ ሳይንቲስትም ምሁር አይደለም።
ስለዚህ በአንተ እሳቤ ለ27 ዓመታት የወያኔ አሽከር ሆነህ እየተላላክና ጆሮ እየጠባህ፥ አሁን ውሃ አይንካችሁ የምትላቸውን ኦሮሞ ዘመዶችህን ሳይቀር እያሳሰርክና ከሃገር እያሰደድክ ከርስህን በመሙላትህ፥ ከህዝብ ካዝና በተዘረፈ ገንዘብ መኪና ስለገዛህ እና ቤት ስለገዛህ ስኬታማ ምሁር መሆንህ ነው?! ለመሆኑ ምንድነው የተማርከው?! ባለ PhD ዎችንና የአፍሪካ መሪዎችን እንደዚህ በጅምላ የምታበሻቅጠው አንተ ምን ሰርተህ ነው ለመሆኑ?!! ንገረኝ እስኪ?!! እንዴ?!! እንዴት አይነት ሞራ አንጎል ነው ያለህ ግን?!! ኖቤሉን የሰጡህ ሃገር ከነገባው የምትሸጥ መሆንህን አውቀው ነው እኮ፤ የተለየህ ምሁር ሆነህ መስሎሃል እንዴ? ወጠጤ!! “ባደረግሁት ጥናት” ይላል ደግሞ። ሃሃሃ ሰው ሲል ሰምተህ ነው?
ይሄንን እርጥብ ጅል (first rate imbecile) መሪያችን ነው እያላችሁ በባዶ ሆዳችሁ ሳይቀር በየቀኑ እያላገጠባችሁም በቅምጣችሁ የምታጨበጭቡለትስ ምን አይነት ባለሞራ አንጎል ብትሆኑ ነው?!
ኢትዮጵያ ውስጥ ጫማ በቅጡ መቀየር እንኳን ተስኗችሁ፥ አግባብ ያልሆነ የደሞዛችሁን 1/3 ኛ በቤት ኪራይ እየተበዘበዛችሁ፥ በትራንስፖርት እጥረት በታክሲ ወረፋና በባቡር ወረፋ ፍዳችሁን እያያችሁ፥ በሃቅ ለመኖር እየተውተረተራችሁ ዘወትር ኑሯችሁ ቁልቁል እየሆነባችሁ በዘመድ አዝማድ ፊት መቆም ሁሉ ያፈራችሁ፥ ለማግባት ሳይሆን የሙሉ ልብስ መግዣ አጥታችሁ የሰው ሰርግ ላይ በአጃቢነት ለመቆም ሁሉ የተሸማቀቃችሁ፥ የማንም ሌባ ታክስ አጭበርባሪ “ባለሃብት” እልፍኝ በጭብጨባ በሚሾምበት ሃገረ ኢትዮጵያ የምትገኙ ወገኖቼና ምሁሮቼ በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሳይቀር ዛሬም ኢትዮጵያችንን ቀና ለማድረግ እየወደቃችሁ እየተነሳችሁ ሰለሆነ ለእናንተ ያለኝ ክብር እጅግ የገዘፈ ነው!! I very know the feeling!! I was there too!! God Bless you። እንደ አብይ ባሉ ሁሉን አውቅ ባይ ደፋር ጅላጅል ግብዞች ዘወትር ለሚለቀቅባችሁ ቅርሻት ቁብ ባለመቁጠር ለኢትዮጵያችን የመጀመሪያም የመጨረሻም ተሰላፊ የቁርጥ ቀን ልጆቿ ናችሁና አይዟችሁ ቀን ይመጣል!! አይዟችሁ ቀን ይወጣል!! አይዟችሁ ጠሃይቱ መልሳ በኢትየጵያ ሰማይ ላይ ዳግም ትበራለች፤ ዳግም ትናኛለች!! እመኑኝ !! ፅኑልኝ !!
የምሁራን ጠላት ይውደም !!
ድል ለዴሞክራሲ !!