>

ከጠቅላይ ምኒስትሩ እንቶ ፈንቶ ተረቶች ጀርባ ያሉ መልእክቶች...!!! (መር እድ እስጢፋኖስ)

ከጠቅላይ ምኒስትሩ እንቶ ፈንቶ ተረቶች ጀርባ ያሉ መልእክቶች…!!!
መር እድ እስጢፋኖስ

እንጭጩ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለአፍሪካ ህብረት ሰላምና የደህንነት ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከ4ወር መተኛት ብኋላ፥ አገሪቱ ላይ ብዙ ጥፋት ከደረሰ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ  እሳቸውን ወደስልጣን ያመጣው ከለውጡ በፊት የተከሰተውን  ከለውጡ ብኋላ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አስረድተዋል፡፡
ሕዝባዊ እንቅስቃሴውንም ተከትሎ የመጣውንም ለውጥ ለማደናቀፍ ሕወኃት ሃገሪቷ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሲፈጥር መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡

የጥፋት ኃይሉ ከኢትዮጵያ ባሻገር የቀጠናውን ሰላም ለማወክ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱንም አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባሻገርም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ውጪ ምርጫ ማካሄዱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷በክልሉ ውስጥ መደበኛ ያልሆነ ሚሊሻና ልዩ ኃይል ሲያሰለጥን መቆየቱንም ነው የገለጹት፡፡
በመጨረሻም ጥቅምት 24 ላይ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ቡድኑ ጥቃት መሰንዘሩን አስረድተዋል ፡፡
በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎም መንግስት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡
የህግ ማስከበር ዘመቻውም በአጭር ጊዜ ውስጥ
መጠናቀቁን ነው ያስረዱት፡፡
በክልሉ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ክሶች መሰረተ ቢስ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የፌደራል መንግስቱ እስካሁን ለ4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች 84 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ መቅረቡን ነው የጠቀሱት፡፡
ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አክሱምን ጨምሮ በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የራሱን ገለልተኛ ምርመራ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም መንግሥት ከሚመለከታቸው የተባበሩት መንግስታት ተቋማት ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ህብረት ሰላምና የደህንነት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ምርመራዎችን እንዲያካሂድ ፈቃዳችንን እንገልፃለን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጨረሻም የአፍሪካ ህብረት በአስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆሙ ምስጋናቸውን አቅርብአዋል።
ጠ/ሚ አብይ አህመድ  ይህ ከለይ የተጠቀሰውን ማብራሪያ መስጠት የነበረባቸው ከጥቅምት 24 ጀምሮ ነበር።እሳቸው ግን እጅግ ዋጋ የሚያስከፍል ጦርነት ጀምረው “ወጧ እንዳማርላት ሴት” በየመድረኩ ያልተጨበጠ ድል ይዘው ማናፋት ጀመሩ።በህግ የተደገፈ ህግን የማስከበር ጦርነት ብለውት ሲያበቃ”ከአለም ጆሮና አይን እንዲርቅ አደረጉት።ወያኔ ያሸነፈችው በዚህ ጊዜ
ነበር ።”መሪያችን አልገባቸውም እንጂ።
ቀልማዳውና ውሽታሙ መሪያችን ደብረፅዮንን በሰችዊሽን ሩም ሆኜ እያያሁት ነበር አሉን ።”ሲሉ ሰምታ ዶሮም ታንቃ ሞተች “እናዳሉት ነው።ጠ/ሚ አብይ መሆን የሚችሉትን እና መሆን የሚፈልጉት እያተቀላቀለባቸው ተችግረዋል።
እንግዲህ የልጅ ነገር  ይችን የሰችዌሽን ሩም ጨዋታ በኦሳማ ቢን ላደን ላይ የተደረገ ራይድ …አለምን ያስደነቀ በመሆኑ በዚያን ግዜ ጭንቅላታቸው ውስጥ ግብታ ኖሮ አሁን በትግራይ ላይ በእራስህ ህዝብ ላይ  በተደረገው ጦነት እንዴት አርጎ አመሳስሎ እና አጣፍጦ ፓርላማ ላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያቀርባት እንቅልፍ አጥቶ ነበረ።እናም   እኛም እንሰማም በማንልበት መድረክ እሱም በግድ ስሙ በሚልበት መድረክ መከረኛ ፓርላማ ላይ ቀርቦ…ሰችዌሽን ሩም …. የድሮውን…ትርክት እንደተለመደው አርቲ ቡርቲ አውርቶ ወረደ
ድል ተገኝ ከተባለበት  ህዳር 22 ጀምሮ ” ሾሌ ያነጪ ጠላ!”ውዝዋዜ ውስጥ ነው የገባው ጠቅላያችን።ወታደራዊ ለብስ የየለበሰ ከውጣት አየር ወልድ ወታደሮች ጋር ፎቶ በነሳት ነው ያሳለፈው።
በየቦታው እያንዛርጠ ነው የከረመው።ኬንያ ሄዶ ስለሊሙ ወደብ ማውራት…..ሳምንት ሳይሞላ “stupid kid” እንዲባል። …።ከዚያ ሲመለስ ደግሞ …..እንደ ጌታ እራት የሚቆጠረውን “የሸገር ገበታ ” ላይ ብቻ ነበር ትኩርቱ።ጥዋት ተነስቶ ….።ሽገር ገበታ ለጎጎራ ነው…..በዚያ ጎርጎራ ቅንጡ መናፈሻ ቱልቱላውን ሲነፋ …የለማቋረጥ የአማራ ልጆች በየቀኑ ቢያንስ ሀምሳ አባወራ በአብይ አይመድ አሊ ዘሮች(በኦሮሞዎች) በወለጋ ምእራብ እና ምስራቅ እየተገደሉ ነው…….።እንደመሪ ይቅር እንደሰው ሀዘኑን ገልፆ አያውቅም ……እስከአሁን
የትግራይ ተፈናቃይ 60ሺ ደረሰ ምን ይደረግ ተብሎ ሲጠየቅ እንደመጣለት የሚያወራው እና እንጭጩ መሪ…..”60ሺ አለ ? ምን አላት ለኔ ..። ይቺማ ቁርስ ናት አለ”ከአፉ የሚወጣውን እንኩኳ የማያውቅ ዘባተሎም መሪ…..
ትግራይን እንገነባታለን ሲልን በፍጥነት በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱትን ጠግነን ወደኖርማል ይመለሳል መስሎን ነበር።ለካስ ጠቅላያችን መጀመሪያ ነብሰበላው ኢሳያስ ለአራት ወር ያክል የዘረፈውን ዘርፎ የገደለውን ገድሎ ትግራይን ካወደማት በኋላ እንገነባታለን ማለቱ ነበር… ኢሳያስን ለማስደሰት ሲል ብቻ…..።
የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለ ጓደኞቹ አስተማሪዎቹ ነበሩ።”እየተንጠራራ ያቅፋቸው ነበረ አስተማሪዎቹን….ትምርት ጨርስው ወደየቤት ሲመለሱ ከአስተማሪው ከውንዱ ወይ ከሴቷ አንዷን ተንጠራርቶ አቅፎ ነበር የሚመለሰው  የዛሬው ዶ/ሩ መሪያችን….አርቲ ቡርቲ ማውራት የማይሰለቸው
“እብዱ ህዝቤ ሆይ ይል ነበር”  አንቲ ጎን የተባለ ጥንታዊ የግርክ ንጉስ በአደባባይ። ህዝቡም ግን “በተራው እብዱ ንጉሳችን ሆይ ” ይል ነበር በጓዳ……….
ክሾርት ሚሞሪያችን ወስደን ስናበቃ  በቅርብ ጌዜ ታሪካችን “ለመሆን በመፈለግ እና ሆኖ በመገኘት መካከል ያለውን የሰማይ እና የመሬት ያክል ልዩነት ያለገባው መሪ የገጠመን ወቅት ላይ እንገኛለን….፡
አሁን አገር በፀሎት እየተመራች ነች ነው።ፅሎቱ ባልከፋ በተንበረከከ ልብ ከሆነ…..ችግር የሚያደርገው ግን ” ትንቢት መጣልኝ ….ጌታ ተናገረኝ……እራእይ አየሁልህ የሚሉት የነፓስተር ዮናስ ቅዥት ፖለቲካችን ውስጥ ገብቶበታል።” ለዚያ ነው ።በጎ ተመኝ ታገኛለህ…..።ካፍህ መልካም ይውጣ እንጂ ምላስ የራሷን ፍሬ ትበላለች የሚሉት ነገር…..ከቃል መጣልኝ ህዝቡን ወደከነአን እየመራኽው ነው።እያሻገርከው ነው….።” ከሚለው ጋር ተደማምሮ…..መሪያችን የቀን ቅዥት ውስጥ ሊገቡ የቻሉት……።
አሁን አክተሩ መሪያችን ሌላ ስህተት እየሰሩ ነው።የተመድ አጣሪ ኮምሽን ይግባ ብለዋል።ውጤቱን ግን ያሰቡበት አይመስልም መካሪም የላቸውም።ቀጣዩ ግን 19ቁጥር ሚስማር መሆኑን ሊገነዘቡት በተገባ(ለመሆኑ እዚህ ግባ የማይባሉት በተለያየ ጊዜ ስለ ራሳቸው የሚያወሩን አርቲ ቡርቲ ወሬ መልእክታቸው ምንድነው? እናየዋለን….kidu መሪይችን

ይቀጥላል

Filed in: Amharic