>
5:21 pm - Saturday July 20, 7405

መንግሥት ከወያኔ አማፅያን ጋር በማሰር ለትንኮሳ እንደጋለጣቸው እነ እስክንድር ነጋ ተናገሩ...!!! (በጌጥዬ ያለው)

መንግሥት ከወያኔ አማፅያን ጋር በማሰር ለትንኮሳ እንደጋለጣቸው እነ እስክንድር ነጋ ተናገሩ…!!!

ጌጥዬ ያለው


በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በሚኖሩበት ጠባብ የእስር ቤት ክፍል ውስጥ የወያኔ አማፂያን ቡድን መሪዎች አቶ ስብሃት ነጋ እና ዶ/ር አብርሀም ተከስተ ተጨምረዋል። የአማፂው መሪዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጀምሮ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ውስጥ የቆዩ ሲሆን ዛሬ የካቲት ዘጠኝ ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ተወስደዋል። ከሌሎች ክፍሎች ተመርጦ እነ እስክንድር ያሉበት ጠባብ ክፍል ውስጥ እንዲያርፉም መደረጉንም የህሊና እስረኞቹ አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል ገልፀዋል።
ይህም የተደረገው በመካከላቸው ያለውን የአመለካከት ልዩነት ተጠቅመው እርስ በእርስ ለትንኮሳ እንዲገባበዙ ታቅዶ እነደሆነም አስረድተዋል። “ሌሎች ክፍሎች አሉ። እኛን ወደዚያ ቀይሩን፤ ይህ ካልሆነም እነርሱን ወደ ሌላ ክፍል ውሰዱልን” የሚል ጥያቄ ለወህኒ ቤቱ አገዛዝ እንዳቀረቡ የገለፁት የህሊና እስረኞች ‘ከበላይ አካል ታዝዘናል’ በሚል ጥያቄያቸው ተቀባይነት አለማግኘቱን ተናግረዋል።
“ኦሕዴድ/ብልፅግና እንደሚፈልገው ፈፅሞ ለትንኮሳ እና ለብሽሽቅ አንጋበዝም። ይህንን ለእስር ቤቱም አስረድተናል” ብለዋል።
ባልደራስ በበኩሉ መንግሥት ሓላፊነት ተሰምቶት እስረኞች አዕምሯቸው ሳይረበሽ እንዲኖሩ ያደርግ ዘንድ ባልደራስ አሳስቧል። “ይህንን ሳያደሮግ ቢቀር ግን በእስረኞች ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ችግር በሕዝብ፣ በታሪክና በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆኑን በድጋሜ ሊያጤነው ይገባል” በማለትም አስጠንቅቋል።

Filed in: Amharic