>

በአማራ ጥላቻቸው የፈጠራቸውን ሕወሓትን የሚያስንቁ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች!    (አቻምየለህ ታምሩ)

በአማራ ጥላቻቸው የፈጠራቸውን ሕወሓትን የሚያስንቁ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች!   

አቻምየለህ ታምሩ

 

“የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሙዩኒኬሽንስ ቢሮ ኃላፊ እቴነሽ ንጉሠ በትናንትናው እለት ከVOA Amharic ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ “በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ከ7መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል” ስትል ተናግራለች።
ሕወሓት የሰረቀው ሁሉ ይገባናል የሚሉት ዐይነ ደረቆቹ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች “ምዕራብ ትግራይ” ሲሉ የሚጠሩት ሕወሓት በጠራራ ፀሐይ ከጎንደር የዘረፋቸውን እነ ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ ጠለምትና ሁመራን ነው። ሕወሓት የትግራይን ተፈጥሯዊ ወሰን የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ በወረራ የያዛቸውን እነ ወልቃይ፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራን  «ምዕራባዊ ዞን» የሚል የዳቦ ስም በመስጠት የትግሬ ግብርና ዞን ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም  ከ1983 ዓ.ም. በፊት አለም እስከተፈጠረበት ዘመን ድረስ ወደኋላ ብንጓዝ ግን የትግራይ የነበረ  አንድ ኢንች መሬት ከተከዜ ወዲህ አናገኝም።
እቴነሽ ንጉሠ “ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሰባት መቶ ሺህ ሕዝብ  በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል” ስትል የሰጠችው መግለጫ ዐይን ያወጣ ውሸት ስለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ ሕወሓት ራሱ እ.ኤ.አ. በ2007 ያደረገውን የሕዝብና የቤት ቆጠራ ማየቱ ይበቃል። ከ2007 ወዲህ የሕዝብና የቤት ቆጠራ እንዳልተካሄደ ልብ ይሏል። ስለዚህ እ.ኤ.አ. በ2007 የተካሄደው የሕዝብና የቤት ቆጠራ የመጨረሻው የሕዝብና የቤት ቆጠራ ነው።
ሕወሓት እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ባካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብና የቤት ቆጠራ መሰረት “ምዕራባዊ ዞን” ተብለው በተከላሉት በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ ውስጥ ባጠቃላይ 356,598 ሕዝብ ይኖራል። ልብ በሉ! ይህ የሕዝብ ብዛት የኔ ፈጠራ ሳይሆን የሕወሓት ራሱ ያካሄደው የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት ነው።
በሕወሓት ባካሄደው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሰረት የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓመት ውስጥ የሚያድግበት ከፍተኛው መቶኛ ስሌት ሶስት በመቶ ነው። በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. 356,598 የነበረው “ምዕራባዊ ዞን” ሕዝብ ባለፉት የሕዝብና የቤት ቆጠራ ባልተካሄደባቸው 13 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 10,697 እያደገ እ.ኤ.አ. በ2020 ዓ.ም. በዞኑ ውስጥ በአጠቃላይ የሚኖረው የሕዝቡ ቁጥር 495,671 ይሆናል።
አሁንም ልብ በሉ! ይህ “ምዕራባዊ ዞን” ብለው በፈጠሩት ዞን ውስጥ እ.ኤ.አ. በ2020 የሚኖረው 495,671 የሚሆን ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር  ሕወሓት ራሱ ያካሄደው የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት ነው።
እንግዲህ! እቴነሽ ንጉሠ “በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ከ7መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል” ያለችውን ይዘን በሕወሓት የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት መሰረት “ምዕራባዊ ዞን” በተባለው ዞን ውስጥ በ2020 የሚኖረውን 495,671 ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር ስናጤን “ምዕራባዊ ዞን” ተብሎ ከፈጠረው አካባቢ “በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል” የተባለው ከሰባት መቶ ሺሕ በላይ ነዋሪ በጠቅላላ በተፈጠረው ዞን ውስጥ ከሚኖረው የሕዝብ ብዛት በ204,379 ሕዝብ ይበልጣል።
ይህ ማለት “ምዕራባዊ ዞን” ተብሎ ወደ ትግራይ በተካተተው አካባቢ ተፈናቀለ የተባለው ሕዝብ በሕወሓት በራሱ ቆጠራ መሰረት ሕወሓት በስልጣን ላይ እስከነበረበት እ.ኤ.አ. 2020 ዓ.ም. ድረስ “በዞኑ” ከሚኖረው ሕዝብ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ በልጦ ከሚመጣው ትውልድ 204,379 ሕዝብ በመበደር እንዲፈናቀል ተደርጓል ማለት ነው።
የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍልም  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሚመጣው ትውልድ ከሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ተበድረው ባካባቢው የሌለ የሕዝብ ቁጥር እንደተፈናቀለ አድርገው በአደባባይ ሲዋሹ የመረጃ ምንጫቸውን ሳይጠይቅና በአካባቢው እንደሚኖር  በሕወሓት በራሱ ከተቆጠረው ሕዝብ በላይ እንዴት ሊፈናቀል ይችላል ብሎ ሳይሞግት ፕሮፓጋንዳቸውን ብቻ ተቀብሎ አስተላልፎላቸዋል።
እኛም እንላለን! የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች ተደርገው የተቀመጡት የትግሬ ብሔርተኞች ሕወሓት የዘረፈው ሁሉ ለኛ ይገባል የሚሉ፣ ከሕወሓት በላይ የሚዋሹና  በአማራ ጥላቻቸው የፈጠራቸውን ሕወሓትን የሚያስንቁ ስለመሆናቸው የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ያስተላለፈላቸውን ይህንን ፈጠራቸው ማየቱ ይበቃል እንላለን።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተባለው  እስከ አረና፤  ከትዴት እስከ ትግራይ ብልጽግና፤ ከውናት እስከ ሳልሳይ ወያነ፤ ከባይቶና እስከ  ፈንቅል ያሉት የትግሬ ብሔርተኞች ሁሉ የስልጣን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በአማራ ጥላቻቸው የፈጠራቸውን ሕወሓትን የሚያስንቁ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። ሁሉም ሕወሓት የዘረፈው ሁሉ ይገባናል የሚሉ ቀማኞች ናቸው። ሁሉም የመንፈስ አባታቸው ሕወሓት በቅኝ ግዛት ከያዘው ከማይካድራ 1100 አማራዎችን ብቻ ጨፍጭፎ በመፈርጠጡ ጥንቢራቸው እስኪዞር ድረስ የሚበሳጩ አረመኔዎች ናቸው። የተስፋፊነት ሕልማቸው ላይ በግልጽ እንደሚታዬው  በአማራ ላይ  ያላቸውን የበቀል ቁጭት  ለመወጣት ከቅኝ ግዛታቸው ነጻ ወደወጡት የአማራ ወረዳዎች ለመመለስ ጥርሳቸውን በመንከስና ዐይናቸውን በማጉረጥረጥ ላይ ናቸው!
እነዚህ የሕወሓት ቅጥያዎች የአሁኑ የአማራ ትውልድ እንደ ብአዴኑ ትውልድ የአማራ ጠላቶች በአማራው መቃብር ላይ ፍላጎታቸውን እስከጥግ ድረስ ሲያስፈጽሙ ዝም ብሎ የሚያይ፤ የጠላት ጉዳይ ለማስፈጸም እስኪያልበው ድረስ የሚታዛዝና  በልቶ ማደርን ብቻ የሕይዎት መመሪያው ያደረገ አለመሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም። የአሁኑ የአማራ ትውልድ ካሁን በኋላ ከሕወሓት ቅኝ ግዛት ነጻ ያወጣቸውን ወረዳዎቹን ክንዱን ሳይንተራስ ወደ ቅኝ ግዛት እንዲመለሱ የሚፈቅድ ምስለ ብአዴን አለመሆኑን ደቂቀ ሕወሓት ሁሉ ቢያውቁት ይመከራል።
Filed in: Amharic