>

መንጌ አንረሳህም...!!!  (አሰፋ ሀይሉ)

መንጌ አንረሳህም…!!! 

አሰፋ ሀይሉ

 

(መታሰቢያነቱ በፊንፊኔ ኬኛ ቡሊጢቀኞች ስቅይት ላሉት ያዲሳባ ልጆች!)
መለስ ዜናዊ ከአዲሳባ ስቴዲየም አጠገብ የኦሮሞ ሀውልት ገንብቶ ዕድሜ ልካቸውን ‹‹ፊንፊኔ ኬኛ›› እያስባለ ሲያስለፈልፋቸው ይኖራል! መንግሥቱ ኃይለማርያም ከአዲሳባ ጥቁርአንበሣ ሆስፒታል አጠገብ ትግላችን የሚል ሀውልት ገንብቶ ዕድሜ ልካችንን ኢትዮጵያን እንዴት ተባብረን እንደምናሳድጋት በቁማችን በህልማችን እያሳሰበን ይኖራል!
የመለስ ሥርዓት ዓላማ የመጨረሻው የዘቀጠ የጎሰኝነት ልክፍት ነው፡፡ የውርደታችን ወለል ነው፡፡ የመንግሥቱ ኃይለማርያም ሥርዓት ዓላማ ደግሞ ከፍ ያለ ብሔራዊ የሀገር ፍቅር ልክፍት ነው፡፡ የከፍታችን የመጨረሻው ነጥብ ነው፡፡
የመንግሥቱ ህልም አልተሳካለትም፡፡ የመለስም ህልም አይሳካለትም፡፡ ሊፈራርስ አንድ ሐሙስ ነው የቀረው፡፡ የመለስንና የመንግሥቱን ዋናው ልዩነታቸው ከተግባር ይልቅ የህልም ልዩነት አድርጌ እወስደዋለሁ፡፡ አዲስ ትውልድ የሚሸከመው የመሪዎቹን ህልም ነው፡፡ የመለስና የመንግሥቱ ትልቁ ልዩነት የህልም ነው፡፡
መለስ የመጨረሻው ወደ እንስሳነት የተጠጋ የጎሰኝነትና የዘረኝነት ጋጥ ውስጥ ሁላችንንም ወስዶ ሊወሽቀን ያልማል፡፡ መንግሥቱ ኃይለማርያም ደግሞ ከፍ ወዳለ የድል ኮረብታ ላይ፣ ከፍ ወዳለ ሀገራዊ አርበኝነት ላይ፣ ከፍ ወዳለ የሰው ልጅ እኩልነትና፣ ዘመናዊውን የሰው ልጅ አስተሳሰብ ያነገበ የዕድገት ከፍታ ላይ ሊያወጣን ያልማል፡፡
መንግሥቱ ኃይለማርያምን የምንወደው በሀገር ፍቅሩ ብቻ አይደለም፡፡ በህልሙም ጭምር ነው፡፡ መለስና የፈለፈላቸው ኬኛዎች የህልም ድርቅ የመታቸው፣ አንሰው የሚያሳንሱ፣ ባለ ሚጢጢ አንጎል ማፈሪያዎች ናቸው፡፡ በእኔ አረዳድ ልዩነቱ ይህ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ ከሚጢጢዎቹ ጎሰኞች በላይ ነው፡፡ ጎሰኞቹ ሙሉ የሰው ልጅን አይመጥኑም፡፡ ከጎሰኞቹ የወረደ ጋጣ ገብቶ ያልተቡካካ፣ የማይቡካካ፣ የተሻለ ከፍ ያለ ህልምና ራዕይ ያለው መሪ ያስፈልገናል!
«ካሣ ካሣ፣ የቋራው አንበሣ
ዳኘን ዳኘን፣ አንድ ሕልም አሳየን»
እንዲል አርቲስቱ፣ ቢያንስ ከስንት ሚሊዮን ሕዝብ መሐል ከፊንፊኔ፣ ከምናምን… ከወረደ የዘርማንዘር ጋጣ የወጣ፣ ጸዳ ያለ አዕምሮ፣ ከፍ ያለ ህልም ያለው መሪ የግድ ያስፈልገናል! ከእነዚህ የጠበቡ ሰዎች የጠበበ ህልም ጋር ነጋ ጠባ እየተነታረክን እኮ የትውልዳችንን አዕምሮ አጨቀየነው! ጎጥ፣ ጋጣ፣ ጎሰኝነት፣ ኬኛ፣ ፊንፊኔ፣ ምናምን… መረረን! ሰለቸን! በቃን!
በታሪክ ‹‹አዲሳባ›› ሲባል እንጂ ‹‹አዲሳበቤ›› ሲባል ተሰምቶም፣ ተነግሮም፣ ተጽፎም አይታወቁም! እነዚህ የወረዱ ጋጠኞች ሁሉንም በእነርሱ ልክ አውርደው አውርደው ጨርሰው የቀራቸው አዲሳባ ነበር፡፡ እሱንም ፊንፊኔ ኬኛ እያሉ ሰዉን አዲሳበቤ ምናምን እንዲል አደረጉት! አዲሳባ የሁሉም ናት! የምን ኬኛ ፊኛ ፊንፊኛ.. ምናምን ነው?
እነዚህን ጠባቦች ያዲሳባ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን ሳይለቅ ጠራርጎ ከጫንቃው ላይ ማውረድ አለበት! ያዲሳባ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ! እስከ መቼ በእነዚህ በጎሰኝነት በናወዙ ጠባቦች እንመራለን? እስከመቼ ብርሃናማ ህልማችንን፣ በጨለመ ህልማቸው ውስጥ ቀብረን እንኖራለን?
የአዲሳባ ልጅ ተቆራጭ ኬክ መብላት ባይችል፣ ተቆራጭ ኬክ እያሰበ መዋል የሚፈልግ ዘመናዊ ሰው ነው! እዚያው ተቆራጭ ጡታቸውን ይዘው… ከነ ኬኛቸው፣ ፊንፊኔ፣ ምናምናቸው… ጥንቅር ብለው ወደሚሄዱበት ቢሄዱልን እንዴት ግልግል ነበር? መረረን፣ ሰለቸን እኮ! በቃን!
መንጌ አንረሳህም!
________________________
«ትግላችን» ኃውልት የግድግዳ ላይ ቅርጽ ጥበብ – ንድፉ በኢትዮጵያውያን፣ ሥራው በኮርያውያን የተሠራ፡፡ 1978፡፡ ፎቶው የራሴ፡፡
Filed in: Amharic