>
5:31 pm - Saturday November 12, 8721

በአማራ ህዝብ ላይ አደገኛ የዘር ጭፍጨፋ ጥሪ ከፓርላማ ...!!! ዶ/ር ዮናስ መኮንን

አማራ ህዝብ ላይ አደገኛ የዘር ጭፍጨፋ ጥሪ ከፓርላማ …!!!
ዶ/ር ዮናስ መኮንን

 

⇐ይህች በፎቶ የምታይዋት ሴት ዛሬ ፓርላማ ላይ ህሊናዋን ሳይቆረቁራት እምነቷም ሳይግድባት ተጽፎ የተስጣትን የውሸት ሪፖርት በማውራት  በኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚኖሩ አማሮች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ጥሪ አውጃለች!!
ይህ ደግሞ የአብይ አህመድ አሊ የእጁ ስራ እንደሆነ ለደቂቃ እንዳትጠራጠር። 
ሴትዮዋ በተጨማሪም በአብን አመራሮች ላይ የኦሮሞ ህዝብ እርምጃ እንዲወስድባቸው የታሰበበት መልዕክት አስተላልፋለች!!
ይሄም በአብይ አህመድ አሊ የተቀነባበረ እርኩስ ሴራ መሆኑን ለአፍታ እንዳትጠራጠር!!
* * *
የፓርላማ ተናጋሪወች አሳፋሪ ናቸው !!!
ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢለመ ደሱ ኦዳ) 
 
ቪዲዮ እየቀረፁ ገድለው፤ ከክልላቸው አልፈው የሌሎችን ከተሞች በገሀድ አቃጥለው፤ “ነፍጠኞችንም ከተማቸውንም አቃጠልን” በማለት በማስረጃ አስደግፈው ከፉከራና እብሪት ጋር ዐሳይተውን…
 የተገላቢጦሽ ‘እኛ ተገደልን _ ተፈጀን’ ብለው በፓርላማ ሲናገሩ አለማፈራቸው ይገርማል። ስለፈጣሪና ስለልጆቻችን ስንል ወለጋ ውስጥ የጨፈጨፈው ማነው?
ሸዋ ሮቢት፣ አጣዬ፣ ከሚሴ በነዋሪዎች መንደር እና ከተማ እየገባ በመንጋ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው ማነው?
እስቲ ከብሔር ከረጢት ወጥተን _ እንደ ባለአእምሮ ሰው፤ ለህሊና ለእውነት ለእምነታችን… እስቲ ስለሀቅ እንነጋገር?
የትኛው ኦሮሞ፣ የትኛው የኦሮሞ ቤት እና ከተማ አማራ ነኝ በሚል ቡድን ተቃጠለ?
ስለፈጠራችሁ ከተንኮል ነፃ ሆነን፤ ሟቾችን የራሳችን ቤተሰብ አድርገን… በእነርሱ ጫማ ውስጥ ቆመን እንመዝን!
አዎ ይዋል ይደር እንጂ ፈጣሪ ይፈርዳል።
Filed in: Amharic