ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት‼
*.. ስለህወሓት ጁንታ፣ ስለኦነግ ሸኔ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የተናገሩት‼
*… የአማራ ልዩ ሀይልን በሚመለከት የተናገሩት
ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው፤
እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤
አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤
ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤
በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን፤
ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች፤
ስለህወሓት ጁንታ፣ ስለኦነግ ሸኔ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት‼
የህወሓት አመራሮችን፣ የማዕከላዊ ኮሚቴውን ሁሉ እባካችሁ ብዬ ለምኛለሁ፤ አስለምኛለሁ፤
ዋና ዋና ባለሃብቶችን ታዋቂ ግለሰቦችን አሰባስቤ በሚስጥር ልኬ እባካችሁ ለምኗቸው ብዬ ሽምግልናም ልኬያለሁ፤
እብሪት ከፉ ነው፤ አሁንም ያላችሁ አመራሮች ከእብሪት ልትቆጠቡ ይገባል፤
በህግ ማስከበሩ ከ300 በላይ የኦነግ ሸኔ ሽፍታ አብሮ ሲዋጋ ይዘናል፤
ኦነግ ሸኔ ለማንም አይበጅም፣ ለሰው ዘር አይበጅም፤ ለኢትዮጵያም ጠላት ነው፤
ወለጋ ህዝብ ስቃይ ውስጥ በነበረበት አንድም ሰው አልተናገረለትም፤ ከውጭም ከውስጥም፤
ኦነግ ሸኔ በሰላም ተወዳደር ሲባል እንቢ ብሎ የህውሓት ቡችላ ሆኖ ነው አርሶ አደር ገድሎ ሲፎክር የነበረው፤
ወለጋ ውስጥ የሞቱት አማራ አርሶ አደሮች አማሮች አይደሉም፤ የኦሮሞ አካል ናቸው፣ እነሱን መግደል ኦሮሞን መግደል ነው፤
በትግራይ ውስጥ ሰዎችን ማፈን አለ፤ ሌለው ቀርቶ እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች ይታፈናሉ፣ ይገደላሉ፤
እርዳታ እንዳይሰጡ ተደርጓል፤ በትግራይ ብዙዎች የደረሰውን በደል እያወቁም ሊክዱ ፈልጋሉ፤
በአንድ ቀን በ200 ቦታዎች ላይ ነው በተጠና መልኩ በተመሳሳይ ሰአት ጁንታው ጥቃት የፈጸመው፤
ኦነግ ሸኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው፤ ለኦሮሞ አይበጅ፤ ለአማራ አይበጅ ለማንም አይበጅም
ትግራይ ውስጥ አሁን ሰው ይታፈናል፤ ርዳታ የሚሰጡ ሰዎች ሳይቀር እየታፈኑ ነው፤ ከዚህ ቀደም ካደረጉት ጥፋት በላይ አሁን የሚያደርጉት ይብሳል፤
ጁንታው ያኔ 200 ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ሰአት አንድ ላይ ነው ጥቃት የፈጸመው፤
አማራ ክልል ላይ ጥቃት የፈጸመው ይሄው ሃይል ነው፤ ዓላማውም ጎትቶ ወደ ግጭቱ ማስገባት ነው፤
ኤርትራ ላይ የተኮሰው ይሄው ሃይል ነው፤ ችገሩን ቀጣናዊ ለማድረግ አስቦ ነው፤
በትግራይ ከ30 ሺህ በላይ እስረኛ ተለቋል፤ መቀሌ ብቻ 10 ሺህ እስረኛ ተለቆ ዝርፊያ ፈጽሟል፤
ለትግራይ ህዝብ ጦርነት ግጭት አይገባውም፤
የእኛ የህግ ማስከበር ሶስት ግልጽ አላማዎች አሉት
– በዘሩ ብቻ በማንነቱ ብቻ ለይተው መከላከያ ሰራዊትን የጨፈጨፉትን ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ነው፤
– ኢትዮጵያን አምነው ለ20 አመት በክልሉ የኖሩ ታግተው የተወሰዱ ከ1000 ሺህ ባለይ መኮንኖችን ማስፈታት ነው፤ መቶ በመቶ አስፈትተናል፤ የገደሏቸውን ቀብረናል፤ የተዘረፍነውን አስመልሰናል፤
– ይህ ክልል ወደ ምርጫ ሄዶ ራሱን እንዲያስተዳድር ነው፤ አሁን ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደር ራሱን እያስተዳደረ
ነው፤ ሊታገዝ ይገባዋል፤
የተበተነው ርዝራዥ ሃይል በየቦታው እየሆነ በመከላከያ ላይ እየተኮሱ ሽንቆጣ ፈጽመዋል፤
ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ማለት ነው፤ ከዚህ በኋላ ተሰብስቦ ዱቄት አይሆንም፤
የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ በትግራይ ክልል ወንጀል የፈጸመ ካለ በህግ ይጠየቃል፤
በትግራይ ክልል ስለተፈጸመ ችግር የሚያነሱ በሰሜን ዕዝ ላይ ስለተፈጸመው ግፍ አያነሱም፤
በማይካድራ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም አካባቢ አልተፈጸመም፤ ግን ተረስቷል፤
ቤንሻንጉል ላይ ስላለው ጭፈጨፋ ማንም አይናገርም፤ ትኩረት ሁሉ አንድ አካባቢ የሆነው የተንሸዋረረ እይታ ስላለ ነው፤
በትግራይ ከተካሄደው ኦፕሬሽን በኋላ 4.2 ሚሊዮን ህዝብ መግበናል፤
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።
የአማራ ልዩ ሀይልን በሚመለከት የተናገሩት
የህግ ማስከበር ዘመቻው ሲጀመር የአማራ ልዩ ኃይል ተደራጅቶ መሬት ለማስመለስ የገባ በማስመሰል የሚነገረው ስህተት ነው፤ ተገቢም አይደለም፤
ሶሮቃና ቅራቅር ላይ ጦርነቱን የጀመረው አማራ ልዩ ኃይል አይደለም፤
ልዩ ኃይሉ ባህርዳር ተቀምጦ ነው ጦርነት የተከፈተበት፤
በዚህም ምላሽ አልሰጠም፤
የአማራ ልዩ ኃይል በህግ ማስከበር ዘመቻው ተጋብዞ ነው የተሳተፈው፤
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስት ስለነበርን የአማራ ልዩ ኃይል ኃላፊነት ተሰጥቶት በህግ ማስከበር ዘመቻው ተሰማርቷል፤
የአማራ ልዩ ሀይል እየሞተ ያለው ሀገር የመጠበቅ መንግስት የሰጠውን ተልእኮ እየፈፀመ ስላለ ነው፤
የአማራ ልዩ ሀይልን ከፈለግን ሶማሌ ክልል ላይ ወስደን ተልዕኮ መስጠት እንችላለን፤
የአማራ ልዩ ሀይል ያጠፋው ጥፋት ካለ ታይቶ በህግ ይዳኛል፤
ለጊዜው ግን ልክ ከሌላ ሀገር እንደመጣ አጥፊ ማየት ተገቢ አይደለም፤
መሬትን በሚመለከት በድንበር ኮሚሽንና በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል በሕግ ይፈታል