>
9:21 am - Friday June 2, 2023

የዐቢይ አሕመድ የዛሬ ማብራሪያና ምላሽ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

የ ዐቢይ አሕመድ የዛሬ ማብራሪያና ምላሽ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

*…. ብዙዎቻቹህ አቶ ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለፓርላማ ተብየው በሰጠው ማብራሪያና ምላሽ አጣዬና አካባቢው ላይ እያስፈጸመው ስላለው ጭፍጨፋ “በኦነግ ላይ በማሳበብ አስተባብሎ ያልፋል!” ብላቹህ ጠብቃቹህ ነበር፡፡ አየ ወገኖቸ! የወያኔ ቅጥረኞች እነ ኦሮሙማ መቸ እፍረት አላቸውና ጭራሽ ጩኸታችንን ቀምተው “የምኒልክ ብርጌድ በሚባል የአማራ ልዩ ኃይል የተጨፈጨፍነው እኛ ነን!” ብለው ከተፍ አሉላቹሃ!!! 
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተብየዎቹ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ተጽፎ የሚሰጣቸው ከአገዛዙ እንደሆነ ታውቃላቹህ አይደለ??? አሠራራቸው እንደዚህ ነው!!! ከዚያ ስማቸው እየተጠራ በየተራ እንዲያቀርቡት ይደረጋል!!!
ይሄ ብአዴንን የመኮነን ወይም በጥፋተኝነት የመክሰስ የፓርላማ አባለቱ ወይም የአገዛዙ ሥራ ሁለት ዓላማ እንዳለው ልብ በሉ፡፡ አንደኛው ብአዴንን የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ በማሳየት ለብአዴን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራን ጥፋት የፈጸመ አድርጎ መሣል ካልተቻለ አሳቦ መጨፍጨፍ አይቻልምና እንዲህ በፈጠራ መክሰስና መወንጀል ግድ ስላሆነባቸው ነው ጩኸታችንን ቀምተው እኛኑ ጥፋተኛ እያደረጉን ያሉት!!!
ያሳቀኝ ነገር ግን አጠገቡ ያሉትን ጥቂት የጉምዝን አሸባሪ ቀስተኞች እንኳ ማጥቃት ያልቻለውንና ወኔ የሌለውን የአማራ ጠላት ሁሉ ቅጥረኛ የሆነውን ብአዴንን “የምኒልክ ብርጌድ የሚል ሥያሜ ለልዩ ኃይሉ አውጥቶ ‘የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን!’ በማለት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዘምቷል!” ተብሎ መከሰሱ ነው!!!
አይገርምም??? አሁን ይሄ ክስ ማንን ያሳምንልናል ብለው ነው በሞቴ እንዲህ የሚቀደዱት??? ለማየት ያብቃቹህ ሰሞኑን ይሄንን ክስ እውነት ለማስመሰል ብአዴንን “ዘራፍ!” እንዲል ሲያደርጉት ታያላቹህ ትሰማላቹህ!!! ሲጀመር የአማራ ልዩ ኃይል የኦሮሞ ልዩ ኃይል እንዳሻው በአጣዬ ሕዝብ ላይ ጥቃት መፈጸም እንዲችል የኦሮሞ ልዩ ኃይል ጥቃት መፈጸም ከመጀመሩ አስቀድሞ አይደለም ወይ አጣዬን ለቆ የወጣው እንዴ??? እንኳንና ኦሮሞን ከአካባቢው ለማጥፋት ከኦሮሞ ገበሬዎች ጋር ውጊያ ሊከፍት ይቅርና???
አሁን ታዲያ ያንን ሁሉ ከባድ መሣሪያ በአጣዬ ሕዝብ ላይ እያዘነበ ያለው የአካባቢው የኦሮሞ ገበሬ ነው ማለት ነው??? እንዴት ነው የሚያሾፉት ባካቹህ??? የገባኝ ነገር ቢኖር ኦሮሙማዎች በዚህ በኩልም የከፈቱት ጥቃትና ጭፍጨፋ ቀጣይነት ያለው መሆኑንና እንደሚሉትም ወሎን እስከመጠቅለል የሚዘልቅ መሆኑ ነው!!!
አየ አማራ ፍዳህ!!! ዙሪያህን ጠላቶችህ ቆርጠውና ጨክነው ተነሥተውብሀል አንተ ግን ለሽ ብለህ እንደተኛህ ነው!!! እንጃልህ ተጨፍጭፈህ ማለቅህ ነው!!! አሁን እኮ የቸገረው ነገር አማራ ልነሣ ብሎ እንዳይነሣም እነኝህ ጠላቶቻችን ብአዴን የሚባል ዘበኛ በመሀከላችን አስቀምጠዋል በየት በኩል ይነሣ??? እጅግ የቸገረ ነገር እኮነው የገጠመን!!! ነቀርሳው ብአዴን ሲፈልግም በጌቶቹ ይታዘዝና ይሄው አሁን እያሉ እንዳሉት አገዛዙ መልሶ ለትግሬ ለሚሰጠው ነገር ባለፈው አማራን ለመፍጃ ሰበብ እንዲሆናቸው በማሰብ ላደረጉት የውሸት ጦርነት “ርስትህን አስመልስ!” ብሎ በማታለል ቀስቅሶ አስገብቶ ላሴሩብን የሴራ ጦርነት አስገብቶ ያስፈጀናል!!!
ታዲያ አማራ በየት በኩል ከዚህ ነቀርሳ የጠላት ዘበኛ ብአዴን ነጻ ሆኖ ተደራጅቶና ዘምቶ ነው ሊያጠፉት ከተዘጋጁት ጠላቶቹ ጋር ተፋልሞ ህልውናውን የሚታደገው ታዲያ??? ወይ አስቀድሞ ብአዴንን ካላጠፋ በስተቀር!!! “አስቀድሜ ብአዴንን አጠፋሁ!” ብሎ ቢነሣ ደግሞ ጌቶቹ ዝም አይሉም ሠራዊታቸውን ነው በአማራ ላይ የሚያዘምቱት!!! ወይ ያው በብአዴን ላይ ስንነሣ በጌቶቹም ላይ መነሣታችንንና ከእነሱም ጋር መግጠማችንን አውቀን “ሞት ካልቀረልን በየተራ ተጨፍጭፈን ከምናልቅ እንነሣና የተሠዋው ለክብሩ ተሠውቶ የተረፈው ይትረፍና ቀን ይውጣለት!” ብለን “ሆ!” ብለን አንድ ላይ ካልተነሣን በስተቀር!!!
እስኪ ይታሰባቹህ በዚች ምድር ላይ እንዲህ በእጅጉ የቸገረና የተወሳሰበ ነገር ከአማራ ሕዝብ ውጭ ማንን ገጥሞት ያውቃል??? አናሳዝንም???
ሌላው አቶ ዐቢይ የተናገሩት ደግሞ ብዙ ሰዎች አቶ ዐቢይ ስለወልቃይት፣ ራያና የአማራ ልዩ ኃይል የተናገረው ነገር ጥሩ መስሎ ይታያቹህ ይሆናል፡፡ ምን እንደተናገረ ስላልገባቸው ነው ጥሩ መስሎ የሚታያቹህ፡፡ ሲጀመር ወያኔ በሕግ ወይም ሕዝቡ ፈቃድና ይሁንና መሠረት ያልወሰደውን የጎንደርና የቤተ አማራ ወይም የላኮመልዛ (ወሎ) መሬት የመሬቱ ባለቤት አማራ ዋጋ ከፍሎ ካስመለሰው በኋላ “ጥያቄው በፌዴሬሽን ምክር ቤትና በፓርላማ በሕግ ታይቶ ይፈታል!” ማለት በግልጽ አማርኛ “መሬቱን ለትግሬ ለማስረከብ ሴራ ሸርበናል!” ብሎ ማለት ነው!!! “እንዴት?” ቢባል የፌዴሬሽን ምክርቤት የሚሠራበት ሕግ ሰፋሪ የወልቃይትና የራያ ትግሮችን በሕዝበ ውሳኔ አስወስኖ ሰፋሪው ትግሬ በወሰነው ውሳኔ መሠረት የሚሠራ ስለሆነና መሬታችንን ለትግሬ አሳልፎ የሚሰጥ ስለሆነ!!!
ስለ አማራ ልዩ ኃይል የተናገረውም “የአማራ ልዩ ኃይል የፈጸመው ወንጀል ካለ ይጠየቃል!” ማለቱን ልብ በሉ፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል ወንጀል ይፈጽማል ብሎ ማንም የሚያስብ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ከተባበሩት መንግሥታት ጀምሮ እስከ የአሜሪካ መንግሥት፣ ከአውሮፓ ኅብረት እስከ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድረስ “የአማራ ልዩ ኃይል በትግራይ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል!” እያሉ እየከሰሱበት የቆዩት ሐሰተኛ ክስ እንዳለ ታውቃላቹህ፡፡ በዚህ ሐሰተኛ ክስ መሠረት ለተባበሩት መንግሥታት፣ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ ኅብረት እና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ተብየዎች ክብር ሲባል “የአማራ ልዩ ኃይል ጥፋት ፈጽሟል ወንጀለኛ ነው!” ተብሎ ተጠያቂ ከማድረግ እንደማይመለሱ መገንዘብ ቀላል ይመስለኛል!!!
ሌላው ደግሞ አቶ ዐቢይ “እጅግ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ የመከላከያ ሠራዊት አባል የሚሆን ሰው ጠፍቷል!” ሲል ትውልዱን ለመክሰስና ለመውቀስ ሞክሯል፡፡ አቶ ዐቢይ በዚህ ጉዳይ ላይ ሕዝቡን ሲከስና ሲወቅስ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ አሁን ይሄንን ክስ ምን ትሉታላቹህ??? ሰውየው ግን ጤነኛ ነው ለመሆኑ??? ይሄ ሰውየ ወይ የለየለት ንክ ነው ወይም ደግሞ ደንቆሮ ነው!!!
አቶ ዐቢይ ሆይ! ወጣቱ የመከላከያ ሠራዊት አባል ለመሆን ላለመፈለጉ ተጠያቂው ማን ነውና ነው ጣትዎትን ወደ ትውልዱ ወይም ወደ ሕዝቡ የሚቀስሩት??? ክልላዊ ስሜቱ ጽንፈኛና መርዘኛ በሆነ የጥፋት ስብከት እየተገነባ ኢትዮጵያዊ ስሜቱ ግን እንዲጠፋ ተደርጎ የተቀረጸ ትውልድ እያየነው እንዳለው ሁሉ የክልል ልዩ ኃይል ለሚባለው አሰፍስፎ ይሰለፋል እንጅ እንዲጠላት ተደርጎ ለተቀረጸበት ሀገር የመከላከያ ሠራዊት እንዴት ብሎ ነው የሚሰለፈው አህዮ??? የወያኔ ቀኝ እጅ ሆኖ በገዛ ሕዝቡ ላይ በምዕራብ ጎንደር፣ በመተከል፣ በወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ ወዘተረፈ. የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲፈጽም ለኖረና አሁንም ከኦነግ፣ ከኦሮሞ ልዩ ኃይልና ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ጋር እየተመሳጠረ በሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ ላለ ወንበዴ ሠራዊት ማን የታመመ ሰው ነው አባል የሚሆነው???
“ነፍጠኛ ቅኝ ገዝቶናል!” እያለ በሚዲያ በሚለፈልፍ ደንቆሮ ባንዳ ብርሃኑ ጁላ ለሚመራ ሠራዊት ማን ያበደ ሰው ነው የመከላከያ ሠራዊት ተብየው የወንበዴ ቡድን አባል የሚሆነው??? በነገራችን ላይ ይች “ነፍጠኛ ቅኝ ገዝቶናል!” የምትለዋ የፈጠራ ትርክት የእርስዎም ትርክት መሆኗን በቪዲዮ በተያዘ መረጃ ዓይተን ያረጋገጥነው ጉዳይ ነው!!! ከግራኝ አሕመድ አውዳሚ የወረራ ሰይፍ የተረፈውን በከባዱ ጦርነት ያለቀንና የደከመን ሕዝብ በመጨፍጨፍ የሰው ሀገር ወረው ይዘው ሲያበቁ አሁን የሀገሩን ባለቤት “ቅኝ ገዝቶናል!” የሚል እፍረተቢስ ክስ በማሰማት እናንተ በዓለም የመጀመሪያዎቹ ነውረኞችና ዓይነ ደረቆች ሳትሆኑ አትቀሩም!!! እግዚአብሔር ይፍረድባቹህ እንጅ ሌላ ምን ይባላል!!!
አማራ ሆይ! ኧረ እባክህ ንቃ በተኛህበት ድንገት ቁርስ ሆነህ መቅረትህ ነው!!!
Filed in: Amharic