>
5:14 pm - Tuesday April 20, 6877

በአማራ ክልል   ሆኖ "የአማራ ልዩ ሀይል ይውጣልኝ"  የሚለው የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አስተዳደር  ...?!? (አያሌው መንበር)

በአማራ ክልል   ሆኖ “የአማራ ልዩ ሀይል ይውጣልኝ”  የሚለው የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አስተዳደር  …?!?
አያሌው መንበር

በአማራ ክልል ያለው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የአገሪቱንም የአማራንም ህገ መንግስት የሚፃረር ነው።
የአማራ ክልል (በCSA መረጃ መሰረት በክልሉ ውስጥ ካሉ ብሄረሰቦች=>አዊ፣ኦሮሞ፣አርጎባ፣ዋግ ውስጥ #የአማራ ብሄር 90% በላይ ነው።ሌሎቹ ብሄረሰቦች ተደምረው ከ10% በታች ናቸው)።የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከእነዚህ ከ10% ውስጥ ሲሆን በቁጥርም አነስተኛ ህዝብ ያለበት ነው።ሆኖም የአማራ ክልል ራሱን “የፌደራሊዝም አርዓያ” ለማድረግ በሚል በጣም ተለጠጦ> 90% ህዝብ የአማራ ብሄር ሆኖ እያለ ሶስት ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችን “የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የሚባለውን ጨምሮ” ፈጥሯል። በተጨማሪም አንድ ልዩ ወረዳ አዋቅሯል።
የመጀመሪያው ስህተት፦
     በኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልል ውስጥ በየትኛውም ክልል ለሌላ ብሄር የተሰጠ ብሄረሰብ ዞን ሳይኖር አማራ ክልል በወያኔና ኦነግ ተዘጋጅቶ የተሰጠውን “ልዩ ዞን” አሜን ብሎ መቀበሉ ነው።
ለምሳሌ ትግራይ በትንሹ ስድስት ብሄረሰብ አለው።ሁሉም በትግራይ እንጅ በብሄረሰብ ዞን አልተዋቀሩም።ኦሮሚያም በተመሳሳይ ከክልሉ ህዝብ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ኦሮሞ ሳይሆን ነገር ግን በውስጡ የብሄረሰብ ዞን የለም።ሁሉም ቦታ ይህ ነው።አማራ ክልል ግን እነ #አዲሱ ለገሰ የጀመሩት የተሳሳተ የፌደራሊዝም ትርጓሜ በኢትዮጵያ በየትኛውም ክልል ሌሎች ብሄሮች ውክልንና አስተዳደር ሳይኖራቸው በአማራ ክልል ውስጥ ግን የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞንን ወልዷል።የእነ አዲሱ ለገሰ ስህተት ክልሉን ለረጅም ዓመታት በመሩት በእነ አቶ አያሌው ጎበዜ፣ ገዱ አንዳርጋቸውም ቀጥሎ እዚህ ላይ ደርሷል። አንደኛው ስህተት ይህ ነው።
ሁለተኛው ስህተት ደግሞ እጅግ የከፋ ነው።
     በአማራ ክልል ውስጥ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ብሎ “ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድሩ” አለ።ቀጥሎ #ኦሮምኛ ቋንቋን በአማራ ክልል ውስጥ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የስራ ቋንቋ ያድርጉ አለ።ልብ በሉ አማራ ክልል ውስጥ ነው።የአገሪቱም የክልሉም የስራ ቋንቋ አማርኛ በሆነበት ክልል ማለት ነው።በዚህ ዞን በርካታ አማራ አለ።ጆሮውን ቢቆርጡት ኦሮምኛ አይሰማም።ይህ አማርኛ ቋንቋ ብቻ የሚናገረው አማራ እና ኦሮምኛ ቋንቋ የማይችለው ኦሮሞ እያስተረጎመ ነው የሚገለገለው።ኦሮምኛ ቋንቋን ለስራ ቋንቋ ሲፈቅድ (ከክልሉ ህገ መንግስት ውጭ) ቢያንስ #አማርኛ ቋንቋን እኩል የስራ ቋንቋ ማድረግ ነበረበት።ትናንት ጠይቄ እንደሰማሁት በአማራ ክልል ውስጥ ሰዎች በአማርኛ አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ክልል አለ ማለት ነው።ይህ የክልሉንም የፌደራሉንም ህገ መንግስት ይፃረራል።የአማራ ክልል ም/ቤት አባለት ይህንን ሳይጠይቁ እንዴት እንደኖሩ፣ ፖለቲከኞች እንዴት ዝም ብለው እንደኖሩ ፈጣሪ ይወቀው።
መቸ ጉዱ በዚህ አበቃና ገና ሶስተኛ ጉድ ልጨምርላችሁ፦
    በዚሁ በአማራ ክልል ውስጥ በሚተዳደረው የወሎ ምድር “የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር” ውስጥ የአማራ ክልል ሰንደቅ አላማ አይውለበለብም አሉ።አይገርማችሁም? እርግጥ እኔ የአማራ ክልልን ባንዲራ በደንብ አላውቀውም፣ አልወደውምም ነገር ግን እኛን ባለቤት ይሆናሉ የምንባለውን ባይገልፅም በክልሉ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ግን እኩል መውለብለብ አለበት ብየ አምናለሁ።ህጉም ያስገድዳል (የህግ ባለሙያዎች አግዙኝ)።
በአማራ ክልል በሚተዳደረው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ውስጥ ግን የሚውለበለበው ሰንድ ዓላማ የአማራ ክልል ሳይሆን በግላጭ የኦሮሚያ ክልል በድብቅ ደግሞ የኦነግ አርማ ነው አሉ።እግዚኦ አትሉም?ይህ የምነግራችሁ እኮ አማራ ክልል ውስጥ ነው።ካስታወሳችሁ የዛሬ ሁለት ዓመት ዶ/ር አምባቸው ከሚሴ ሲገኝ አዳራሹ ውስጥ ከጀርባው አንድ ነገር ተመልክተን ነበር።አስታወሳችሁት አይደል? አወ።የኦሮሚያ ሰንድቅ ዓላማ።በወቅቱ “ዶ/ር አምባቸውን ለማናናቅ የተጠቀሙበት” መስሎኝ ነበር።ምክንያቱም ዶ/ር አምባቸው በእነ ጀዋር በኩል “Ultra Nationalist” እስከመባል ደርሶ ነበር።ያው የእኛዎቹ ጠብሰው ይበሉት ነበር።ሌላኛው ወገንም እንዲሁ።ተናበው የሚሰሩ ይመስል ነበር።እና በወቅቱ የመሰለኝ ጊዜያዊ እንጅ በቋሚነት የተለመደ ሰንድቅ አልመሰለኝም ነበር።
ዛሬ ግን አረጋገጥኩ።አወ በአማራ ክልል ውስጥ የኦሮሚያ ክልል እና የኦነግ ሰንደቅ ዓላማ ይሰቀላል፣ በአማራ ክልል ውስጥ የአማራ ክልል ሰንደቅ አላማ የማይሰቀልበት፣ አማርኛ የማይነገርበት ዞን አለ።
ልቀጥል?…..?
እናንተየ የዚህን ዞን ጉድ ዘርዝሬ አልጨርሰውም፦የዞኑም ፖለቲካና የመንግስት ሪፖርት አፈፃፀምም ወደ አማራ ክልል አይልክም ነበር አሉ።ለኦሮህዴድ ነው የምልክ ብሎ ነበር አሉ።ይህንን የዛሬ ሁለት ዓመት ነው የሰማሁት። በወቅቱ ጆሮውን ይዘው ገምግመውት ተስተካክሎ እንደነበር አስታውሳለሁ።
እና ይህ ሀይል መጨረሻ ምን አለ መሰላችሁ?የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ከአማራ ክልል ይውጣልኝ አለ አሉ።
ከላይ የነገርኳችሁ ስህተት ነው፣ ውሸት ነው የሚል ካለ በራሱ መንገድ ያረጋግጥ።
ግን ግን  ይህ ሁሉ ችግር የማን ይመስላችኋል?
በእኔ እይታ የችግሩ ምንጭ የአማራ ክልልን ከአቶ አዲሱ ለገሰ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የመራ የአማራ የፖለቲካ አመራር፣የአማራ ክልል ምክር ቤትና መንግስት ነው።
አሁን ምን ይደረግ? ካላችሁኝ ቢያንስ በአገሪቱና በአማራ ክልል ህገ መንግስት መሰረት ህግ እንዲከበር ማድረግ!
ከሚሴን በተመለከተ
አሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ማለት በአማራ ክልል ውስጥ አማርኛ የማይነገርበት ወይም በአማርኛ አገልግሎት የማይሰጥበት ዞን ማለት ነው።ይህንን አምኖ የተቀበለ የአማራ ክልል ም/ቤት ስብስብ ነው ያለን።
እናም መፍትሄው ሳይውል ሳያድር የስራ ቋንቋውን ማስተካከል፣በአመራር ውስጥ ያሉ ፅንፈኞችን በአስቸኳይ ቀይሮ በህዝብ አመራር መተካት፣ስፍራውን ጠንከራ የአማራ ፖሊስ እንዲኖረውና ወንበዴ እንዲጠፋ፣ህግ እንዲከበር ማድረግ፣በአማራ ክልል ውስጥ የኦሮሚያ ክልልን ሰንድቅ አላማ እንዳይውለበለብ በምክር ቤት ማገድ (ይህንን ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ስለሆነ) የአጭር ጊዜ መፍትሄ ነው።
የመጨረሻው መጨረሻ #የኦሮሞ ብልፅግንና እና #ኦነግ በአደባባይ በአንድ ማዕድ ሲመጡ ለሁሉም ነገር ጥሩ ነው።በአማራም ጉዳዩ ከፓርቲ ጉዳይ ሁሉ ያለፈ ተደርጎ መያዝ አለበት።ይህ የአማራ ብልፅግና፣ የአብን፣ የኢዜማ፣ የእናት ፣ወዘተ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም።
ይህ የአማራነት ጉዳይ ነው! ይህ የኢትዮጵያ ህውልና ጉዳይ ነው! ይህ አገር የመታደግ ጉዳይ ነው! ይህንን የኦሮሞ ፅንፈኛ አገር አፍራሽ አካሄድ ሶማሌው፣አፋሩ፣ጋምቤላው፣ደቡቡ፣ቤኒሻንገሉ፣ ወዘተ ሊያውቀውና በአንድ ላይ ሊያወግዘው የሚገባ እኩይ አካሄድ ነው!!!
ግልባጭ:- 
አገኘሁ ተሻገር-Agegnehu Teshager
Temesgen Tiruneh – ተመስገን ጥሩነህ
Abiy Ahmed Ali
አብርሃም አለኸኝ ጥሩነህ/Abrham Alehegn Tiruneh
Amhara Communications
Filed in: Amharic