>
5:31 pm - Friday November 13, 0268

ኢትዮጵያን የምትፈልጓት ሁሉ ጎዣምን አምጡልኝና፤ ኢትዮጵያችንን ከነሰንደቋ ጠቅልዬ አድላችኋለሁ! ! ! (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ስጋዊ ወመንፈሳዊ)

ኢትዮጵያን የምትፈልጓት ሁሉ ጎዣምን አምጡልኝና፤
ኢትዮጵያችንን ከነሰንደቋ ጠቅልዬ አድላችኋለሁ! ! !

  ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ስጋዊ ወመንፈሳዊ



. . .ብው  ! ! ! ሲያደርጉ «ጎጃምን ምታ ፦» ይላሉ. .
. . .ብም ! ! !ብም ! ! !ቡዋ ፦» ሲያደርጉት «ጎንደርን ምታ ፦»ይላሉ. .
. . .«ጣጣጣጣጣ ? ? ? ጥጥጥጡዋ » ሲያደርጉት «ትግራይ ምታ ፦» ብለው
ዞር ሲሉ. . . «ጎጃምም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ ፥ ጎንደርም ትግራይም ሲወጋ እዚሁ ነበርኩ» ሲላቸው
. . . «ውይ ልጄ ፦ እናትም የለህ ፧» ሲሉት
. . .«ታዲያ እናት ቢኖረኝ ይታራብኛል እንዴ !» ብሏቸው አረፈው እላችኋለሁ።ሙሉውን የገጠመኝ ትረካ ከአማርኛ ውክፔድያን ላይ አሁኑኑ ማግኘት ትችላላችሁ ።

ወደተነሳሁበ ዐቢይ ርዕሰ-ጉዳይ ልውሰዳችሁና፣ኢትዮጵያዊ ሆኖ ስለኢትዮጵያ ሕልውና የማያስብ ካለ፤”መቀመጫዬን እግዚአብሔር ለእኔ አልሰጠኝም” ብሎ የሚያስብ እና እንደውም ለምንስ ስለመቀመጫችን  ሁላችንም ማሰብ አስፈለገን ብለው  በቸልታ የሚያደርጉትን እና የሆኑትን ሰዎች በሙሉ ይመለከታል።

          የእኔ መቀመጫ በተፈጥሮ ለራሴ ብቻ የተሰጠኝ መቀመጫዬ ነው፤መጀመሪያ መቀመጫዬን ብዬ የጀመርኩበት ምክንያት፣ዝንጀሮ “መጀመሪያ መቀመጫዬን ብላለች” ስለተባለም አይደለም፤በማንኛውም የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ጉዳይ የመቀመጫን መኖር ማረጋገጥ ዐቢይ እና አስፈላጊ ነገር በመሆኑ ነው፤በጹሁፌ ውስጥ “መቀመጫ”ሕብር ቃል መሆኑ ይታወቅልኝ።
እናት ሀገሬ መቀመጫዬ ነች ስል ለክፉም ሆነ ለደግ የተፈጠርኩባት የዘር ማንዘሬ የትውልድ አገሬ ናት ማለቴ ነው፤”የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ”እያስባለ የሚገመድ የትውልድ ሀረግ ነው።ዘሩን ለማወቅ የማይፈልገውን እና የሚክደውን አስቆሮታዊ ወይም ዘር አሰዳቢ ብለው ይጠሩታል፤ምክንያቱም በዘር ውስጥ ፈለግንም አልፈለግንም የደማችን መታወቅ እና አለመታወቅ ትልቅ ግምት ነበረው፣በተለይም ከወሊድና ከዕምነት ጋር በተያያዘ ትልቅ ግምት ይሰጠው ነበር፤በዚህ የጠለቀ ዕውቀት ከጎዣም ክፍለ ሀገር የበለጠ የትኛውም አገር   ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ በዓለም ዙሪያ ፍፁም አልነበረም፤የኢትዮጵያን ሉሲ ከግምት ውስጥ አስገብተን ዘመናትን በዓይነ ሕሊናችን  አድርገን ከተመለከትን።
እናም ከዚህ ውጤት የምናገኘው የኢትዮጵያ ሕልውና ጉዳይ ከጎዣም ክፍለ ሐገር ሕላዌ ጋር የተጋመደ ነው፤ዘራችንን በወንዱ በኩል ያለውን ስንቆጥር ከታች ወደላይ ፦አባት፣አያት፣ ቅድመ አያት፣ቅማት፣ቅማያት፣ሽማት፣ምዝላት እና እንጅላት ቢያንስ በተገቢው በቃል ተመዝግቦ ይያዛል፤እነዚህን ባሕላዊና ሳይንሳዊ ምክንያቶችን በምሥጢር የያዙበት ዕሴቶች አሁንም አልፎ አልፎ በሚያውቁ ሰዎች ብቻ የማሕበረሰቡ አባላት ቁጥጥር  ይደረግባቸዋል፤የማህበረ ሰቡን ምክር ጥሰው ጋብቻ የፈፀሙ ከቤተሰቡ እንዲገለሉ ይደረጋሉ።ይህ ሁሉ የትውልድ  ዘር ሐረግ መጓተት የመጣው የኋላ ቀርነት ምልክቶች ስለሆኑ ሳይሆኑ ምክንያቶቹ እና ሰበቦቹ በሚሥጥር ተይዘው ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ በመሆናቸው ነው።
ዓለም ወደሥልጣኔ እየገሰገሰች መሆኗ ቢታወቅም ከትውልድ የመጡትን የዕውቀት ውጤቶች እንድንዘነጋቸው ትውልድም ሆነ የሳይንሱ ጥበብ በፍፁም አይመክረንም፤ እንደውም እንድንጠብቃቸውና እንድንከባከብቸው የጠበቀ ምክር ይለግሱናል።ከዚህ አንፃር የተረገሙ ኢትዮጵያውያን ልጆቿ ጎጃምን ከኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጎኗ ላይ በሚሥጥር በፖለቲካ ሥልጣናቸው ደብዛዋን ለማጥፏት ቢሞክሩም በፍፁም አልቻሉም፤ እንዲያውም የጎጃምን የአካሏን ብልት ገዝግዘውና ቆርጠው ለማውጣት ውድ ልጆቿን በመግደል ለማረሳሳት ቢሞክሩም የኢትዮጵያ ታሪክ የተጻፈው በዜጎቿ ደም ስለሆነ መቼም ጊዜ ሊአጠፉትም አልቻሉም።ለምሳሌ የአኮሱም ዕውነተኛ ታሪክ ትግሬን እንደማይመለከተውና ዳሩ ግን በኢትዮጵያዊነት የታሪኩ ተቋዳሽ ቢሆንም የአገው የታሪክ ባለቤትነት ከመጠሪያው ጀምሮ ሌሎች ጠቋሚ መረጃዎችን እንደሚያመላክቱ ተገኝተዋል፤እንደሰሜን ተራራዎቹ
እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ቅርሶች ምዝገባ እና አያያዝ ሽወዳዎች ይታወቃሉ።
አንባቢዎቼ ወዴት እና እንዴት ወደርዕሳችን ጉዳይ እያመራሁ እንደሆነ በሙሉ ልብ ተከታትላችሁኝ ካልሆነ የተጠቃለለ አመላካች አንቀፅ ልስጣችሁ፤ስለጎዣም ክፍለ ሐገርነት የማይነሳበትና በተለይም በአካባቢው ሰዎች በየጊዜው የሚገደሉበት ሳይሆን የሚታረዱበት ሚሥጥር ምንድን ነው?እነማን ናችው ይህንን አረመኔያዊ ተግባር የሚፈፅሙት?ኦሮሞም ሆነ አማራ የሚለው የነገድ ስያሜ ለግለሰብ በመጠሪያነት በዚህ ትውልድ  ላይ ለምን የሰውን ሰውነት አግኝተው በሕብረተሰባችን ውስጥ ተፈጠሩ?ብታምኑም ባታምኑም ጎዣምን ሊያጠፏት፦ አንዴ መተከል ሌላ ጊዜ ጉምዝ፣ሲያሻቸው ጋምቤላ ሲጨንቃቸው ወለጋ የሚቅነዘነዙበት ምክንያትና ዓላማቸው አንዲት ናት፦”ኢትዮጵያን ማጥፋት”ከጎጃም መጀመር ነበር፤ ይህችን ተግብረውታል።
እነዚህ ሁሉ ተንኮሎች ተፈፅመው ግን ጠላቶቻቸን አላበቁም፤
እንትናቸውን. . .ብው  ! ! ! ቢያደርጉም«ጎጃም ሕዝብ በክርን ደቁሰዋቸዋል ፦  »
» . . .ብም ! ! !ብም ! ! !ቡዋ ፦ ሲያደርጉት «ጎንደር  ሕዝብ ተፍትፏቸዋል ፦  »
» . . .ጣጣጣጣጣ ? ? ? ጥጥጥጡዋ » ሲያደርጉት «ትግራይ ሕዝብ ርቋቸዋል ፦  »
» . . . «ጎጃምም ሲዋጋ ፥ ጎንደርም ትግራይም ሁሉም ሰማንያ ሦስቱም ጎሳዎች ሲዋጉ  »
» . . .እንደቀድሞው ሁኔታ እኛ ጀግናዎች ነን ብለው የተቅበዘበዙት፣በየቱቦው፣ በየጢሻው፣ በየወንዝ ዳርቻው እንደ አይጥ በየመንደሩ፣እንደቅማል በየሰዉ ጎን ተሸሽገው የሰው ደም ለመጥመጥ በሕዝብ ላይ በሠላም ሥም ሊታራበት » አይቻላቸውም።
ጎጃምና ዘላን ጎዦን ይወዳሉ፤
አሉ ግጅሌዎች የተግጀለጀሉ።
ባለጎዦ፣ጎዣሜ ባይወድም መነቀል፤
አዎ ዘላን እንጂ ሁሌ የሚንቀለቀል።
መተከል እያሉ ጎዦና ጉልቻ፤
ከኢትዮጵያ ለማጥፋት
ምነው ጎጃም ብቻ።
እንዴት ዝም ይባላል
ርስት ሲጠፋብን፤
ጎጃም ከኢትዮጵያ
እፍብን አለብን።
ትዳርና ንብረት
ሚሥጥር የታየባት፤
ጎዦ ወጣ ሳይሆን
አወጣ ነው አባት።
እንጅልኝ ወዲያልኝ ሰው መኾን ሰለቸኝ ፤
በላይ ቤት አልሠራኹ፣በምድር አልተመቸኝ።
Filed in: Amharic