>

እነ እስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር ለምን ፈለጉ? መስካሪዎቹስ እነማን ናቸዉ? ሸንቁጥ አየለ

እነ እስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር ለምን ፈለጉ? መስካሪዎቹስ እነማን ናቸዉ?

ሸንቁጥ አየለ

ለምን እስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ተደብቀዉ ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር ፈለጉ?
መስካሪዎቹ እነማን ናቸዉ?
መስካሪዎቹ ማንን ነዉ የፈሩት?
መንግስትን እንዳይባል መንግስትን ሊፈሩ ጨርሶ አይችሉም::መንግስት እማ ከመስካሪዎቹ ጎን ነዉና::
እና ማንን ፈሩ?
ህዝቡን ነዉ የፈሩት ከተባለስ ለምን ህዝቡን ፈሩት?
ህዝቡን እንዲፈሩ ያደረጋቸዉ ምንድን ነዉ?
ሰዎቹ ታዋቂ ናቸዉ?
እነዚህ በ እስክንድር ላይ እንዲመሰክሩ የተዘጋጁት እስክንድርን የከዱ ናቸዉ?
መቼም ህዝቡ እንዳያጠቃን ፈራን ሊሉ አይችሉም::ምክንያቱም በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አቅም የለዉም:: እንኳንስ ከመንግስት ጋር የሚሞዳሞዱ እና በጨለማ ለመመስከር የተዘጋጁትን ለማጥቃት ይቅር እና እራሱንም ለመከላከል አቅም የለዉም::
እና ለምን እስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ተደብቀዉ ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር ፈለጉ?
መስካሪዎቹ የሀሰት ምስክር ስለሆኑ ነዉ የሚለዉ ህሳቤ አያስኬድም::
ምክንያቱም የሀሰት ምስክሮች ደረታቸዉን ጠፍጥፈዉ በአደባባይ ያልተደረገዉን ሲደረግ አይቻለሁ ብለዉ መጽሃፍ ቅዱስ ቀጥቅጠዉ መትተዉ መመስከር ልማድ በሆነበት ሀገር ምንም የሚያስፈራቸዉ ነገር ሊኖር አይችልም::
እንኳንስ መንግስት ከጀርባቸዉ የቆሙ ሰዎች ይቅርና ሰዎች እርስ በርስ እየተነጋገሩ በሀሰት አንዱ በአንዱ ላይ ሲመሰክሩ ምንም በማይመስላቸዉ ሁኔታ ዉስጥ የወደቀ ሀገር የሀሰት ምስክር ስለሆነ አደባባይ ላለመዉጣት ይፈራል ማለት ዘበት ነዉ?
እና ጥያቄዉ ለምን እስክንድር ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ተደብቀዉ ከመጋረጃ ጀርባ ለመመስከር ፈለጉ?
ህዝብ በደንብ ሊጠይቀዉ የሚገባ መሰረታዊ ጥያቄ ነዉ?
መስካሪዎቹ እነማን ቢሆኑ ነዉ መንግስት ህግ ጥሶ ምስክር ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ ይመስክር እያለ የሚያሽሞነሙናቸዉ?
ስለ መስካሪዎቹ የሰማችሁትን በዉስጥ መስመር አድርሱኝ::
መስካሪዎቹ እነማን እንደሆኑ ከብዙ አቅጣ መረጃዎች እየደረሱኝ ነዉ::ግን በደንብ የዳበረ መረጃ እፈልጋለሁ::
ስለዚህ መረጃ ያላችሁ ወዲህ በሉ::
በንጹሁ ሰዉ ደም ላይ የሚደረግ ሸፍጥን እማ እግዚአብሄር እራሱ የሚገልጥበት መንገድ ይቀረዋል ።
Filed in: Amharic