>

ለካስ ሳናውቀው የኦነግ ካርታ ተግባራዊ ሆኗል...!?! አይገርምም??? !!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ለካስ ሳናውቀው የኦነግ ካርታ ተግባራዊ ሆኗል…!?! አይገርምም??? !!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እኔ የምለው የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል በክልሉ ውስጥ ያለውን የኦሮሞ ዞንን አይቆጣጠርም እንዴ???
“እንዴት እንዲህ ብለህ ልትጠይቅ ቻልክ?” ብትሉኝ ነቀርሳው ብአዴን ዛሬ ባወጣው መግለጫው ላይ በዞኑ ውስጥ ኦነግ የሚሠለጥንባቸው ስፍራዎች እንዳሉ እየጠቀሰ የዞኑን አሥተዳደር ይከሳል!!!
የክልሉን ጸጥታ የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት የክልሉ ጸጥታ ኃይል በሆነበት ሁኔታ እንዴት ይሄ ሁኔታ ሊፈጠር ቻለ??? የክልሉን ጸጥታ የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከሆነ እንዴት ነው ታዲያ ይሄንን ዞን የክልሉ የጸጥታ ኃይል ሊቆጣጠረው ያልቻለው???
ብአዴን የሚሠራብንን አሻጥር እያያቹህልኝ ነው???
በዚህ ዞን የሚውለበለበው የክልል የሚሉት ጨርቅም የኦሮሚያ የሚሉት ጨርቅ ነው እንጅ ብአዴን “የአማራ ክልል!” የሚለው ጨርቅም አይደለም!!!
ብአዴን እንዴት አድርጎ እንደሚጫወትብን እያያቹህልኝ ነው???
ዞኑ ያለው የአማራ ክልል በሚሉት ከሆነ በምን ሕግና መብት ነው የዞኑ አሥተዳደር የኦሮሚያ የሚሉትን ጨርቅ ለማውለብለብ የሚችለው???
ይሄማ ከሆነ የኦነግ ካርታ ተግባራዊ ሆኗል አትሉኝም እንዴ!!! አይገርምም???
ልብ በሉ ይሄ ዞን ባጀቱን የሚበላው የአማራ ክልልን ነው፡፡ ባጀት ከመብላት ውጭ ያለውን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳይ የሚሠራው ግን የኦሮሚያ ክልል ሆኖ ነው፡፡ ይሄ አሻጥር አያሳዝንም???
የምለው አልገባቹህም እንዴ??? “ነቀረሳው የጠላት ባሪያ ብአዴን አካባቢውን መጠበቅና መቆጣጠር ሲኖርበት ጠላት እንዲደራጅበትና እንዲፈነጭበት ለጠላት ለቆ ሲያበቃ ባጀትም እየመደበ አደራጅቶ የሚያስጨፈጭፈን እራሱ ብአዴን ነው!” ነው እያልኳቹህ ያለሁት!!!
Filed in: Amharic