>

"...ሱዳን ግብጽ በጉልበት የያዘችባትን የሃላይና ሸላቴ መሬት ትታ ትኩረቷን ኢትዮጵያ ላይ ያደረገችው ለምንድ ነው...???"  አቶ ሀሊ ያሂያ ሱዳናዊ የሚዲያ ባለሙያና የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ

“…ሱዳን ግብጽ በጉልበት የያዘችባትን የሃላይና ሸላቴ መሬት ትታ ትኩረቷን ኢትዮጵያ ላይ ያደረገችው ለምንድ ነው…???” 
አቶ ሀሊ ያሂያ ሱዳናዊ የሚዲያ ባለሙያና የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ 

 

👉 በዚህ ሰዓት የሱዳን መንግስት የእኔ መሬት ነው ብሎ ወታደራዊ ሃይሉን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ያስገባው ከተባለ ጉዳዩ ሌላ ነው፤ ከግድቡ ጋር እንጂ ከድንበሩ ጋር እንዳልሆነ እንረዳለን፣
👉 በአፍሪካ አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማስፈጸም የማይችሉትን የተለያዩ አጀንዳዎች ይዘው ይመጣሉ፣ ህወሓት ይዞት የመጣውን አጀንዳ በአግባቡ አልፈጸመም፣
👉 የብሔር ፌዴራሊዝም በህዝቦች መካከል አለመግባባትን እየፈጠረ ለብዙዎች ሞት ፣ መፈናቀልና ንብረት መውደም መነሻ  ሆኗል፤ ህዝቦች ግጭት ውስጥ የቆዩት የብሔር ፌዴራሊዝም ባመጣው ጣጣ ነው የሚል እምነት አለኝ፣
👉 ከለውጡ በፊት የሲቪክ ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም ነበር፤
👉 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መጥተው በሰላማዊ መንገድ በፖለቲካ ውስጥ እንዲሳተፉ እድል ተሰጥቷል፣ይህ ትልቅ እምርታ ነው፣
በሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም፤ በሲቪልና ወታደራዊው ክንፍ በኩል ያሉ አለመግባባቶች እንዲወገዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዋጽኦ አድርገዋል፣
👉 የሱዳን ጋዜጠኞች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ‹‹የሰላም ነብይ ›› እስከ ማለት ደርሰዋል፣
👉 በአባይ ተፋሰስ አካባቢ የሚገኙት ሱዳናውያን አርሶ አደሮች የሚያመርቱት በዓመት አንድ ጊዜ ነው፤ የህዳሴ ግድብ ስራ ሲጀምር ከሁለት ጊዜ በላይ ማምረት ያስችላቸዋል፣ በውሃ ግፊት የሚቸገረው የሩሴል ግድብ የተመጠነ ውሃ ስለሚያገኝ ስራውን በአግባቡ ያከናውናል፣
👉 አስዋን ግድብ በጀማል አብዱል ናስር ሲገነባ የግብፅ መንግስት ማንንም አላማከረም፤ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ከመገንባቷ በፊት ሱዳንንና ግብጽን አነጋግራለች፣
👉 ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ነኝ የምትለው አስቀድማ ወንዙ ከግብጽ ህዝብ ህይወት ጋር የተሳሰረ እንደሆነ በሚዲያዎቿ አማካኝነት ስለሰራች ነው፤ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስለ አባይ ወንዝ እምብዛም አይናገሩም፣
👉 ኢትዮጵያ በሰው ዘር አመጣጥ ታሪክ ቀደምት ነች፤ ግብጽ ኢትዮጵያን የምትቀድማት ሚዲያዎቿን ተጠቅማ ለዓለም ህዝብ ተደራሽ በመሆን ብቻ ነው፣
👉 ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ጉዳይ የውሃ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው፣
👉 የሱዳን ህዝብም ይሁን ምሁራን የድንበሩ ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት አላቸው፣ ማንኛውም የሱዳን ዜጋ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አይፈልግም፣
👉 ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቃ ስትገባ ግብጽ ሱዳን ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን እንቅስቃሴ እደግፋለሁ የሚል መግለጫ ማውጣቷ፣ ግብጽ እንዲህ አይነት መግለጫ ያወጣችው በጉልበት የያዘችውን የሱዳንን መሬት ሳትለቅ መሆኑ ሲታሰብ ደግሞ የበለጠ ያስገርማል፣
👉 ግብጽም ከሱዳን ጋር የመሰረተችው ጋብቻ የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ በማሰብ ነው፤ ሱዳን ከግብጽ ጋር የጀመረችው ወዳጅነት ምንም አይነት ጥቅም አያስገኝላትም፤ በታሪክ እንደሚታወቀው ግብጽ ከሱዳን ስትወስድ እንጂ ስትሰጥ አይታወቅም፣
👉 ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር እየተስማማች መምጣቷ ሲገባቸው እኛ መብራት እንሰጣችኋለን ብለው የኢትዮጵያንና የሱዳንን መልካም ግንኙነት ወደ ማበላሸት ነው የመጡት፣
አቶ ሀሊ ያሂያ ሱዳናዊ የሚዲያ ባለሙያና የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ፡- ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊትና በኋላ ምን አይነት መልክ እንደነበራት፣ ሱዳንና ግብጽ የመሰረቱት ወዳጅነት አንድምታው፣ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቃ መግባቷና የግብጽ አይዞሽ ባይነትና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ያነሷቸውን ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
Filed in: Amharic