አቻምየለህ ታምሩ
ከታች የምትመለከቷቸው የቦታ ስያሜዎች በአውሮፓዊቷ ሀገር በቼክ ሪፐብሊክ ውስጥ የሚገኙ የአውራጃ ስሞች ናቸው።
የአውራጃዎቹ ስሞች ቦረና ሆራ፣ ሊበን፣ ረቢ፣ ዱቢ፣ ቢሊና፣ ወዘተ ነው። እነዚህ የቦታ ስሞች እኛ አገር ውስጥ ቢገኙ ኖሮ ኦነጋውያን የኦሮሞ ናቸው ብለው እስከዛሬ ድረስ ሰልቅጠዋቸው አልያም ሊሰለቅጧቸው አምዣብበውባቸው ነበር።
መቼም በቤተ ኦነግ ማፈር ብሎ ነገር የለምና እንደነ አክሱማ፣ ስሬ፣ አደ ጋራቲና መቃሌ ሁሉ ወደ አውሮፓም ተሻግረው ከታት የሚታዩትን የቼክ ሪፐብሊክ አውራጃዎች “ስማቸው ኦሮምኛና የኦሮሞ ጎሳዎች ስም ስለሆነ የኛ ናቸው”፤ “እንደ አክሱም ሐውልት ሁሉ ዲሞክራሲን ጨምሮ የአውሮፓ ስልጣኔ በሙሉ የኛ ስልጣኔ ነው” ይሉን ይሆናልኮ?! በቤተ ኦነግኮ የሰው ልጅ ሊያፍርባቸው የሚገቡ ወራዳ ተግባሮች የኩራት ምልክቶች ከሆኑ ውለው አድረዋል!