>
12:51 pm - Tuesday June 6, 2023

ወገን ሆይ! ጨርሰህ ከመጥፋትህ በፊት ማወቅ ያለብህ ነገር!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ወገን ሆይ! ጨርሰህ ከመጥፋትህ በፊት ማወቅ ያለብህ ነገር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሰሞኑን እንዳያቹህትና እንደሰማቹህት አገዛዙ እሳት በየስፍራው ማንደድን ጨምሮ ጭፍጨፋውንና የንብረት ውድመቱንም በየስፍራው አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል!!!
በእሳት የመጋየቱ ተራ አሁን በመጨረሻ የየረር ሥራሴና የየረር በዓታ ለማርያም ጥንታዊ ገዳማት የሚገኙበትና ትንቢት የተነገረለት የየረር ተራራ ሆኗል፡፡ አገዛዙ በዚህ በምታዩት መልኩ ሆን ብሎ ጋዝ አርከፍክፎ እያቃጠለው ይገኛል!!!
የወያኔ አገልጋዮች ኦሮሙማዎቹ አዲስ ሀገራቸውን መመሥረት የሚፈልጉት የአማራን ቅርስና አሻራ አውድመው አጥፍተው በመሆኑ ነው እንዲህ በየስፍራው የገዳማትን ጥብቅ ደኖችን ከዝቋላ እስከ አሰቦት ከሰሜን ሸዋ እስከ ሰሜን ተራሮች ያሉ ጥብቅ ደኖችን ጋዝ እያርከፈከፉ እያጋዩ የሚገኙት!!!
ደኖቹ ሆን ተብሎ ጋዝ ተርከፍክፎባቸው እየጋዩ እንዳሉ ለመረዳት ባለሞያ መሆን የሚጠይቅ አይደለም፡፡ እንደምታዩት እሳቱ የተያያዘው ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተዘርግቶ ዙሪያውን መስመር ሠርቶ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ የሆነ የሰደድ እሳት በዚህ መልኩ አይቀጣጠልም፡፡ ተፈጥሯዊ የሆነው የሰደድ እሳት በጣም ደረቅና ነፋስ በበዛበት ወቅት የሆነ ቦታ ላይ እንጨት ከእንጨት ጋር ሲጋጭ ሰበቃ ይፈጥርና እሳት ይነሣል፡፡ ከዚያም እሳቱ ነፋስ ወደመራው አቅጣጫ ዙሪያውን እያነደደና እያወደመ ይቀጥላል እንጅ ፈጽሞ በዚህ መልኩ አይቀጣጠልም!!!
እሳቱ መሥመር ሠርቶ መንደዱ የሚያረጋግጠው ሀቅ እሳቱ ሆን ተብሎ ተቀጣጣይ ነገር ተርከፍክፎበት የተለኮሰና የተቀጣጠለ መሆኑን ነው፡፡ ይሄንን ያህል ኪሎ ሜትር ጋዝ አርከፍክፎ እሳት የመለኮስ አቅም ያለው አገዛዙ ብቻ ነው!!! ከዚህም በተጨማሪ የአገዛዙ የጸጥታ አካላት ሕዝቡ እሳቱን ለማጥፋት ወደ እሳቱ በሚተምበት ጊዜ “አይቻልም!” ብለው ሕዝቡን መከልከላቸውና መመለሳቸው የሚያሳየው የእሳቱ ባለቤት አገዛዙ መሆኑን ነው!!!
እግዚአብሔር በደላችን ምን ቢከፋ ከእነዚህ አጋንንት ወያኔ/ኢሕአዴግ እጅ እንደጣለን ነው ግርም የሚለኝ ነገር!!!
በጣም የሚገርመው ነገር ነገሮች ሊቀለበሱ በማይችሉበት መልኩ እጅግ እየከበዱ እየመጡ እንደሆነ እያየን አሁንም ዘልማዳዊ በሆነው መንገድ ከንፈራችንን እየመጠጥን መቀጠላችንና “በቃ!” ለማለት አለመቁረጣችን ሲታይ ነው!!!
ብዙ የዋሃን ወገኖች የዋሃን ብቻ ሳይሆኑ አሜሪካ ያለው የባልደራስ አማካሪ ቦርድ አባላትና ብአዴን ከጀርባ የሚዘውራቸው በቅማንቶች የሚመሩ የአማራ ማኅበራት በሙሉ “ሀገር በየአቅጣጫው ችግር ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት ‘እንዲህ ሆንን እንዲህ ተደረግን!’ ብለን በመውጣትና በመበጥበጥ ተጨማሪ ችግር መሆን የለብንም፡፡ ይሄ አለመብሰልና ለሀገር አለማሰብ ነው!” እያሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሕዝቡን በሰፊው እያዘናጉትና እያጃጃሉት ይገኛሉ!!! አገዛዙ እያጃጃላቸው እንደሆነ ፈጽሞ ሊረዱ አልቻሉም!!!
እነዚህን ነቀርሳው ብአዴን የሚያጃጅላቸውን ቅጥረኞች ትቸ በእነኝህ ቅጥረኞች እየተጃጃለ ያለውን ወገን መመለስ ያለበትን አንድ ወሳኝ ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ፦
በየስፍራው የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ጨምሮ ብዙዎችን ችግሮች የሚፈጥራቸው እራሱ አገዛዙ እንደሆነ ቢያንስ በዚህ ጊዜ የማያውቅ ወገን ያለ አይመስለኝም!!!
ታዲያ አገዛዙ የጥፋት ተልእኮውን አጠናክሮ ቀጠለበት እንጅ “በዓባይ ጉዳይ ከሱዳንና ግብጽ የገባሁት ችግር ባለበት ሁኔታ ሌላ ቀውስ የሚፈጥር ነገር መፈጸም የለብኝም!” ብሎ አሰበ ወይ??? አገዛዙ ሆን ብሎ ጥድፊያ በሚታይበትና ፋታ በማይሰጥ ሁኔታ ጥቃት እየፈጸመ ባለበት ሁኔታ እኛ የአገዛዙ የጥቃት ሰለባዎች “ተጨማሪ ችግር ላለመሆንና የሀገርን ጥቅም ለማስቀደም!” ብለን በሰፊው የሚፈጸምብንን ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት በዝምታ ካሳለፍን ይሄ ቂልነት እንጅ እንዴት ሆኖ ታስቦ ነው ብስለትና ለሀገር ማሰብ የሚሆነው???
የጥፋት ኃይሎች እኛ የጠፋንባትንና የተወገድንባትን ሀገር ለመፍጠር በምታዩት መልኩ በጥድፊያና ፋታ በማይሰጥ መልኩ በርትተው እየሠሩ ባለበት ሁኔታ ማን ለሚኖርባት ሀገር አስበን ነው ለመሆኑ “ተጨማሪ ችግር ላለመሆንና የሀገርን ህልውና ለማስቀደም!” በማለት አሳሳቢ አደጋ ላይ ለወደቀው ለህልውናችን፣ ለደኅንነታችንና ለመብታችን ወቅቱና ሁኔታው በሚጠይቀውና በሚያስገድደው መልኩ የጥፋት ኃይሎችን ባለ በሌለ ኃይላችን ከመጋተር የምንታቀበው ለመሆኑ??? እስኪ ይሄንን ጥያቄ መልሱልኝ እነ ጅሎ???
እናም እያንዳንድሽ በቅጥረኞች የምትጃጃይ ጅል ሁሉ ይሄንን የቂል ሐሳብሽን ትተሽ ለህልውናሽ፣ ለደኅንነትሽ፣ ለመብትሽ፣ ለጥቅምሽና ለነጻነትሽ ጊዜ ሳታጠፊ ፈጥነሽ ብትቆሚና በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ስሜት ወያኔ/ኢሕአዴግንና ግብረ አበሮቹን ለማጥፋት ፈጥነሽ ብትነሽ ይሻልሻል!!! ለኢትዮጵያ የሚያስብ ካለ ኢትዮጵያ ልትተርፍ የምትችለው በዚህ መንገድ ብቻ መሆኑን መረዳት አለበት!!! ሀገሪቱ በፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ኃይሎች እጅ መሆኗን እያየና ሳያሠልሱ ጠፋት እየፈጸሙባት እንደሆነ እያለ “ተጨማሪ ችግር ላለመሆን የኢትዮጵያን ህልውና ለማስቀደም!” ምንንትስ ቅብርጥስ ማለት ከባድ ድንቁርናና ዘገምተኝነትም ነው!!!
Filed in: Amharic