>

ኢትዮጵያዊነት ኦሮሙማው የጉልበት እጥረቱን ለማሟላት እየተጠቀመበት ያለ ጊዜያዊ ካርድ ነው...!!! (አሰፋ ሀይሉ)

ኢትዮጵያዊነት ኦሮሙማው የጉልበት እጥረቱን ለማሟላት እየተጠቀመበት ያለ ጊዜያዊ ካርድ ነው…!!!

አሰፋ ሀይሉ

ዐዋቂ አልባው እና ልብ አልባው የአማራ ፖለቲካ በአብይ እየተመራ ያለውን የኦሮሙማውን ሴራና እኩይ አካሄድ ቀድሞ ማየት ካልቻለ ይቀደማል! ኢትዮጵያዊነት ኦሮሙማው የጉልበት እጥረቱን ለማሟላት እየተጠቀመበት ያለ ጊዜያዊ ካርድ ነው። አብይ በዋና ከተማዋ 22ሺህ ኮንዶሚኒየም ለኦሮሞ ብቻ መርጦ እያደለ፣ ለአማራው፣ ለጋሞው፣ ለጌዲኦው፣ ለሱማሌው፣ ለወላይታው፣ ለኦርቶዶክሱ ፍጅትና እርድ ቃል ለማውጣት እየተናነቀው – ዓላማዬ 80 ብሔሮች በእኩልነት የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ መገንባት ነው ይለናል። በኦሮሙማው ያልተቀማ ነገር የለም። ጩኸት ተቀምቷል። ሚዲያ ተቀምቷል። ስልጣን ተቀምቷል። ጦር ተቀምቷል። ባንኩም ታንኩም ጄቱም ተቀምቷል። ነገ የቀሩን ነገሮች ሁሉ ይቀማሉ። ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዕውቀት ጥላቻ ተሰኝቷል። እውነት አስፈርቷል። አጎብዳጅነት አስተዋይነት ሆኗል። ጮሌነት ህጋዊ ጥበብ ተደርጓል። መዋለል ዘመናይነት ተብሏል። ይህ የመጨረሻ የፌስቡክ ፖስቴ ነው። ልብ ሲሰጠን እንገናኝ። መልካም ጊዜ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ።
Filed in: Amharic