“ሀገር ስታምጥ!” የአስቴር (ቀለብ) ስዩም የመጽሀፍ ምርቃት.. !!!
* …. እያሳሰሩ ዋጋ እያስከፈሉ ያንን እየተረኩ መኖር ሊበቃን ይገባል፤ ሁል ጊዜ ሰውን እየማገዱ ዳር ቆሞ የህሊና ጸሎት እያደረጉ መቀጠል አይቻልም፤ የዳር ተመልካች መሆን ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ አይጠቅምም
በምንችለው ሁሉ እየተሳተፍን ይችን አገር የሁላችንም ማድረግ ለነገ የማይባል የዛሬ ተግባራችን ሊሆን ይገባል
ተጋባዥ ተናጋሪ የነጻነት ታጋዩ ታማኝ በየነ
የህወሀት የበላይነት የሰፈነበትን ስርዓት በፅኑ በመቃወሟና በማውገዟ፤ ለዜጎች እኩልነት ፍትህና ዴሞክራሲ በመታገሏ በገዢው መንግስት ቂም ተቋጥሮባት በእስር ስታማቅቅ የነበረችውና የግብር ልጆቹ በሆኑት ላጋሲ አስቀጣዮቹ ብልጽግናዎች ዛሬም በእስር ላይ የምትገኘው ታጋይ አስቴር ስዩም (ቀለብ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆና ያሳተመቸው “ሀገር ስታምጥ” መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሆቴል ተመርቋል።
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰተረውና የታጋይ አስቴር ስዩምን የትግል ህይወት፣ የእስር ቤት ስቃይና ውጣ ውረዷን በሚያስቃኘው በዚህ መፅሀፍ ምርቃት ላይ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ፣ የባልደራስ ጽ/ቤት ሀላፊ ገለታው ዘለቀ፣ መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣
አርቲስት አስቴር በዳኔ፣
የዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ የታሪክ ምሁርና ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱና
ተጋባዥ ተናጋሪ የነጻነት ታጋዩ ታማኝ በየነና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት እንግዶች ጥሪውን አክብረው ተገኝተዋል።
በእለቱም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ በመጽሐፉና በእስር ላይ ሰለምትገኘው ታጋይ አስቴር ስዩም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በእለቱም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ በመጽሐፉና በእስር ላይ ሰለምትገኘው ታጋይ አስቴር ስዩም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።