ወንድወሰን ተክሉ
በአቢይ አህመድ አሊ የሚመራው የኦህዴዱ ብልፅግናዊው ኦነግ ኃይል በ2003/4/5ላይ በሱዳን ዳርፉር ከ300ሺህ በላይ በዳርፉር የሚኖሩ ጥቁርና ክርስቲያን ሱዳናዊያንን በመጨፍጨፍ ከሚታወቀው ጃንጃዊድ ሚሊሺያን በጨካኝነቱ በአረመኔነቱና በጨፍጫፊነቱ የሚስተካከል ገዳይ ሚሊሺያ ልክ የካርቱሙ ሰውዬ ኡመር አልበሺር ጃንጃዊድ ሚሊሺያውን በፈጠረበት መንገድ ኦህዴድም መልምሎ አሰልጥኖና እስከአፍንጫውም አስታጥቆ ለዘመቻው ተዘጋጅቶ ይገኛል:::
በዳርፉር የጄኖሳይድ ወንጀል በመፈፀም ስሙ በአለም ገኖ የታወቀው ጃንጃዊድ ሚሊሺያና የኦሮሚያው ጨፍጫፊ ሚሊሺያ መካከል Identical የሆነ ተመሳሳይነትና አንድነት ያለ ሲሆን የሚለያዩበት ነጥብ ቢኖር እምነት (ጃንጃዊድ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም ሲሆን የኦሮሚያው ግን ዋቄፈታ እስልምና እና ክርስትና አማኞች ያሉበት ነው) ዘር ቀለምና ቋንቋ (ጃንጃዊድ የሰሜን ሱዳን አረብ ሲሆን የኦሮሚያው ግን ኦሮሞ) ከመሆን በስተቀር አደረጃጀታቸው አወቃቀራቸው የገንዘብ የሎጀስቲክስ የመሳሪያ ስንቅና ትጥቅና የፖለቲካ ፍኖተ ካርታን በማውጣትና ትእዛዝ በመስጠት ደረጃ የሁለቱም ምንጭና መሰረት በስልጣን ላይ ባሉ መንግስታት ሆኖ ሳለ ሁለቱም ገዳይ ሚሊሻዎች ለተቀረው አለምና ለህዝብ አማፂ ሚሊሻዎቹ በመንግስትም ላይ ያመፁና ከማእከላዊው መንግስት እዝ ጠገግ ያፈነገጡ ፀረ መንግስት አማፂዎች ናቸው ብሎ የመግለፅና የማስተዋወቁ ሁኔታ ሁለቱን አንድ ያደርጋቸዋል:::
የኦሮሚያው ገዳይ ታጣቂ ሚሊሺያ ተደጋግሞ እንደሚነገረን ኦነግ ወይም ኦነግ/ሽኔ ተብሎ በሚጠራ የደቦ ስም የሚጠራ ፀረ መንግስት አማፂ ሚሊሺያ ተደርጎ ይገለፅ እንጂ የሚሊሺያው አጠቃላይ አደራጅ መልማይ አሰልጣኝ አስታጣቂና የፖለቲካ ትእዛዝ እየሰጠ የሚያሰማራው ግን በአቢይ አህመድ የሚመራው የኦህዴድ ፓርቲ ሲሆን የጃንጃዊድንም ሚሊሺያ በበላይነትትእዛዝ እየሰጠ ሲመራ የነበረው የዛሬው እስረኛ የዚያኔው የሱዳን ፕሬዚዳንት የነበረው ሀሰን አልበሺር ነበር
የአልበሺር ጃንጃዊድ ሚሊሺያን የፈጠረበትና የተጠቀመበት መንገድ ዛሬ የአቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና ኦነግሸኔ በሚል የዳቦ ስም እየተጠቀመበት ካለው ተልእኮ ጋር አንድና ተመሳሳይ የመሆኑ እውነታው ሌላው አንድነታቸው ነው፡፡
ኡመር አልበሺር የነዳጅ ክምችት ያለበትንና ጥቁር ክርስቲያን ሱዳኖች መኖሪያ የሆነውን የዳርፉርን ክፍለ ሀገር በሙስሊም አረቦች ለመውረርና ለመቆጣጠር በፈለገበት ቅጽፈት ጥቁር ክርስቲያን ሱዳናዊያኑን ጨፍጭፎ በመጠራረግ የማጽዳት ስራውን መፈጸም ነበረበትና ይህንን ሲፈጽም ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄ እራሱን ነጻ ሊያደርግ ሲል በሱዳን ማእከላዊ መንግስትና በመከላከያ ሰራዊቱ መዋቅር ውጪ የሆነ የ«አማጺ»ስም የሰጠውን የጃንጃዊድ ሚሊሺያን በመፍጠር እጅግ መጠነ ሰፊ የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንደፈጸመ ሁሉ አቢይ አህመድም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲፈጸም ላሰበውና ላቀደው የኦሮሞ ተስፋፊ ወረራ ዘመቻ የኦነግሸኔ የሚል የዳቦ ስም የሰጠውን አረመኔና ጨፍጫፊ ሚሊሺያን ከፌዴራሉ መንግስታዊ መዋቅር ውጪ በሆነ ኢንፎርማል አደረጃጀትና አወቃቀርን ዘርግቶ እጅግ አፈርጥሞ ያዘጋጀው የጥፋት ሚሊሺያ ነው ይህ በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ገዳይ ታጣቂ ቡድን፡፡
ቡድኑ የሱዳኑ አቻው ጃንጃዊድ ከታጠቃቸው ዘመናዊና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ እስካሁን መታጠቁን ያላየንለት ብረት ለበስ (ታንክ ቢ ኤም ወዘተ)አይነቶች በስተቀር እጅግ ዘመናዊ ከበባድ የጦር መሳሪያዎችን መታጠቅ የቻለና የሎጀስትኪስና የትራንስፖርት ስምሪት ፍላጎቶቹን በአግባቡ ያለአንዳች ስጋትና እንከን ከወለጋ ሰሜን ሸዋ ብሎም ደቡብ ሸካ እና በፈለገበት የወረራ ግንባር በቀላሉ ተጋጉዞ የሚደርስበትን የመጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በበቂ ሁኔታ የያዘ ግዙፍ ታጣቂ ሚሊሺያ ነው፡፡
የዚህ እስከአፍንጫው የታጠቀው የአቢይ መራሹ የኦሮሚያ ጃንጃዊድ ሚሊሺያ ሁለንተናዊ ዝግጅት ዘንድሮ በሚካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዋዜማ ጀምሮ አዲስ አበባን ያካተተ በሸዋ፣በወሎ፣በመተከል ግንባር በጎጃምና በደቡብ ለሚከፍተው መጠነ ሰፊ የተስፋፊነት የወረራ ዘመቻው ማስፈጸሚያነት አቅዶ ያዘጋጀው ሲሆን ዋና ግቡንም አማራንና ኦርቶዶክስ ክርስትናን ከመላ ኦሮሚያ ማጽዳት አዲስ አበባን ጨምሮ መላ ሸዋንና ወሎን በኦሮሞ ግዛት ውስጥ ማስገባት በደቡብ የጌዴኦ ጉጂ ነጭሳር ፓርክ አካባቢ ያለውን የደቡብ ክልል ግዛትን ወደ ኦሮሚያ የመጠቅለልና ከዚያም በዘላቂነት ሚሊሺያው በአማራ በኩል ለሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት እያየ የማሸበርና የማዳከም የጭፍጨፋ ስራን እንዲፈጽም የተዘጋጀ ኃይል ነው እንጂ አማጺ የሚባለው ይህ ታጣቂ ሚሊሺያ በአቢይ ከሚመራው የማእከላዊው የፌዴራል መንግስት፣ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር የሚዋጋ እውነተኛ የመንግስት ተቃዋሚ እንዳልሆነ ነው መረዳት የሚቻለው፡፡
የሱዳኑ አልበሺር በጃንጃዊድ ሚልሺያ ተጠቅሞ በትንሹ ከ300ሺህ በላይ ጥቁር ክርስቲያን ሱዳናዊ የዳርፉር ህዝብን መጨፍጨፍ ቢችልም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትግልና ተጽእኖ አልበሺር በ ICC ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት ተፈላጊ ወንጀለኛ ከመሆን አላመለጠም፡፡
አቢይ ለጊዜው ስልጣን ላይ ያለና በያዘውም ስልጣን የንጹሃን ዜጎች ህይወት በመተከል በኦሮሚያ በሰሜን ሸዋ በደቡብ ጉራፈርዳ በትግራይና በጉጂ ጌዴኦ በገፍ እየተቀጠፈ ባለበት ሁኔታ አንድም ሰው ለተጠያቂነት ወደ ፍርድ ደጃፍ ባልተወሰደበት ሁኔታ በምርጫ አስታኮ ሊፈጽማቸው ላቀዳቸው የፖለቲካዊ ስልጣን አላማው ማስፈጸሚያነት መጠነ ሰፊ የወረራና የጭፍጨፋ ዘመቻን ለማስጀመር በመጠባበቅ ላይ ያለ ሰው ሆኗል፡፡
የአማራው ህዝብና በአማራ ክልል ስልጣን ወንበር ላይ ያለው የአዴፓስ ሁኔታና ዝግጁነት ምን ይመስላል ብለን ብናይ የምናየው ሁኔታ አስደንጋጭ ከመሆኑ የተነሳ በተደገሰልን የጥፋት ድግስ ሊያልቅ የሚችለውን የወገን ብዛትን መገመቱ ይዘገንናል፡፡ የአደጋውን አስከፊነትና አስፈሪነት የአዴፓ እንደነ ፋኖ አይነቱን የአማራን ነፍጠኛን የማሳደድና በአይነቁራኛ የመቆጣጠር በሽታ ጀምሮ የህዝባችን መንስኤውን ያላገኘንለት ቸልታ ዝምታና ብሎም ዳተኝነት አደጋውን እንዲጎላ ሲያደርገው ይታያል፡፡
እናም የሆነው ሆኖ ምን መደረግ አለበት የሚለው ወሳኝ ጥያቄ አይቀሬ ነውና መደረግ ባለበት ዙሪያ የምመለስበት ይሆናል፡፡