>

ለዚህ እልቂት ዋና ተጠያቂ “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት!” የሚል ራዕይ የያዘው አገዛዝ ቁንጮ ዐቢይ አሕመድ ነው!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ለዚህ እልቂት ዋና ተጠያቂ “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት!” የሚል ራዕይ የያዘው አገዛዝ ቁንጮ ዐቢይ አሕመድ ነው!  
አቻምየለህ ታምሩ

ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ኦሮምያ በሚባለው ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ እየተካሄደ እንዳለው አይነት ጭፍጨፋ በኦነግ የተካሄደው በደርግ ዘመን በ1982 ዓ.ም. አሶሳ ላይና በሕወሓት ዘመን በ1984 ዓ.ም. ሐረርጌና አርሲ ውስጥ በተካሄዱት ጭፍጨፋዎች ነው።
ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ግን በራሱ በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ [ከማል ገልቹ የተናገረውን ልብ ይሏል] ከኦሮሞ ልዩ ኃይል ውጭ የሆነው ኃይል እንዳይታጠቅ የተከለከለውን የግልና የቡድን መሳሪያ እስካፍንጫው እንዲታጠቅ የተደረገው ኦነግ በ1982 ዓ.ም. በአሶሳ፤ በ1984 ዓ.ም. በሐረርጌና የአርሲ በአማራ ተወላጆች ላይ ያካሄደው አይነት ጭፍጨፋ በየቀኑ  በማድረግ ላይ ይገኛል።
ኦነግ በደርግ ዘመን መጨረሻ  በ1982 ዓ.ም.  አንድ ጊዜ በአሶሳ እና  በሕወሓት ዘመን መጀመሪያ በ1984 ዓ.ም. በሐረርጌና በአርሲ አንድ ጊዜ በአማራ ተወላጆች ላይ ያካሄደው አይነት ጭፍጨዳ በዐቢይ አሕመድ ዘመን በተለይም በወለጋ በየዕለቱ ሲያካሂድ የሚውለው “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት” የሚለውን ስንቅ፣ ትጥቅ፣ መረጃና ለጭፍጨፋው የሚያስፈልገውን ሁሉ የሚያቀርብለት  የኦነግን ራዕይ የያዘ የዐቢይ አሕመድ ፓርቲ በመንግሥትነት ስለተሰየመ ነው።
በሌላ አነጋገር ኦነግ በደርግ ዘመን በ1982 ዓ.ም. በአሶሳና በሕወሓት ዘመን አንድ ጊዜ በሐረርጌና በአርሲ በአማራ ተወላጆች ላይ  ያካሄደውን ጭፍጨፋ በዐቢይ አሕመድ ዘመን በየዕለቱ ሲያካሂድ የሚውለው “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ  ለማጥፋት እየሰራን ነው” የሚሉት እነ ዐቢይ አሕመድና ሽመልስ አብዲሳ በመንግሥትነት ስለተሰየሙና የማይነጥፍ ትጥቅና ያልተገደበ ፍቃድ ስለሰጡት ነው።
ባጭሩ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ የሚኖረው አማራ ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጎ፣ ድረሱልኝ፣ አድኑኝ እያለ የሚደርስለት አጥቶ እነ ሺመልስ አብዲሳ በሚመድቡት የሕዝብ ማመላለሻ መኪና እየተጓጓዙ ወደግፉዓኑ ቀበሌ የሚላኩት የኦነግ ወታደሮች የሚፈጽሙትን እልቂት በፌስቡክ በቀጥታ እያሳዩ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስኪን የአማራ ተወላጆችን በየቀኑ የሚጨፈጨፉት “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት” የሚለውን  የኦነግ ራዕይ የያዘው የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ በመንግሥትነት ስለተሰየመ ነው።
በመሆኑም  “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት” የሚለው የኦነግ ራዕይ እውን ይሆን ዘንድ በወለጋ  በየቀኑ እየተካሄደ ያለው በመቶዎች የሚቆጠር የአማራ ተወላጆች ጭፍጨፋ ዋና ተጠያቂው አማራንና አማርኛን ከኦሮምያቸው  ለማጥፋት እየሰራ የሚገኘው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና  ፓርቲ ሊቀመንበር ዐቢይ አሕመድ ነው!
ከዚህ በተጨማሪ “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ማጥፋት” ሲታገል የኖረውን የኦነግ ራዕይ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን በወለጋ፤ በሐረርጌ፣ በሻሸመኔ፣ በዝዋይ፣ ወዘተ በማስጨፍጨፍ ሲያስፈጽም የሚውለውን ዋናውን አበጋዝ  ዐቢይ አሕመድን እየደገፈ ኦነግን የሚቃወም ሆዳም አማራና “አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ለማጥፋት እየሰራን ነው” ያለውን የጭፍጨፋው መመሪያ ሰጪ አብዲሳን ባሕር ዳር ድረስ ጠርቶ ካባ የሸለመው ብአዴንም ከአራጆቹ ባልተናነሳ በየቀኑ የሚጨፈጨፉ ንጹሐን የአማራ ተወላጆች እልቂት ባለደሞች ናቸው! ይኼው ነው።
Filed in: Amharic