>

"ኢትዮጵያ አትፈርስም" በዲስኩር  በተግባር ግን  ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለ መሪ....!!! (ሳሚ ዮሴፍ)

“ኢትዮጵያ አትፈርስም” በዲስኩር  በተግባር ግን  ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለ መሪ….!!!

ሳሚ ዮሴፍ

እርካብና መመንበር….. አደማሳያ
ገጽ 36…
“በመልካሙ ጊዜ ሕዝብን በፍቅር መያዝ አስፈላጊ ነው። ፍላጎታቸውን በመፈጸም የልብ ትርታቸውን ማዳመጥ፣ ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር በማድረግ በሕዝብ ልብ ውስጥ ተደላድሎ መቀመጥ ይቻላል። ታዲያ አመጸና የመክዳት ምልክት የታየ ጊዜ በሁለተኛውና በተለበጠው ማንነት መገለጥ ተገቢ ይሆናል። ተመጣጣኝ ቅጣትን ተግባራዊ በማድረግ በፍቅር ጊዜ መልአክ፣ በአመጽ ጊዜ ግን ሰይጣን ሊሆን እንደሚችል ማሳወቅ አለበት። ማንም ውሃና እሳት አብረው ቀርበውለት ማንም እጁን ወደ እሳቱ መክተት ምርጫው አያደርግም፤ ያንቀላፋ ሰይጣንንም በራሱ ላይ ቀስቀሶ በራሱ ላይ ችግርን ማምጣት የሚሻ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። (መግደል መሸነፍ ነው ተረት እዚህ ጋር ይሞታል፤ እየሞትን እንጂ እየገደልን ሥልጣናችንን አናስጠብቅም የሚለው ዲስኩር እዚህ ጋር ያበቃለታል) ቢኖር እንኳን የሚተባበረው ስለሚያጣ ብቻውን ይቀራል። መቼም ሥልጣን ብቻውን ዝም ብሎ አይገኝም፣ መሀሉ ላይ መውጣትና መውረድ፣ መውደቅና መነሳት፣ ይኖረዋል። የተሳካለት ባለሟል ግን ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት እንዳለው ሳያሳብቅ ጥሩ ተዋናይ በመሆን በትረ ሥልጣኑን መጨበጥ የቻለ ነው። (ይሄ መስመር ሰባተኛው ንጉሣችንን በደንብ ይገልጸዋል)…. 
ለማንኛውም ጠቅለል ስናደርገው ይሄ አንቀጽ ለቲም ለማ የተጻፈ ነው ግማሾቹ ተገድለዋል፣ የተወሰኑት ታስረዋል፣ ሌሎቹ ደግሞ አማካሪ፣ የስራ አጥ ሚንስትር ተብለው ስማቸው እንኳን እንዳይነሳ ተደርገዋል።
ገጽ 38…
“እንደ ውሻ በመጮኽ ማምለጫን ማመቻቸት ዘላቂ መፍትሄ ባይሆንም ለጊዜው ይጠቅማል። ምክንያቱም እንዳይመለስ ሆኖ ያልተሸኘ ጠላት ጊዜ ጠብቆ ዳግም ለማጥቃት እንደሚመለስ ጥርጥር የለውም። ታዲያ ጊዜው ሲደርስ ልክ እንደ ነብር ኮቴን ሳያሰሙ ከጀርባ ቀብ ማድረግና ህልሙን በአንድ ጀንበር ማምከን መረሳት የለበትም። ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸው በጥቅም ሂድባቸው የሚፈልጉትን ነገር እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው።
ከዚያም ‘በሬ ሆይ! ሣሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ’ የሚለውን ተረት ተርትባቸው”
ይሄ የኢትዮጵያ ሙሴ ለሚሉት የተጻፈ ነው። 
ገጽ 39….
“እብሪተኛ ከመሆን ይልቅ ለሌሎች በጎ በመሆን የደነደነ ልብ ያላቸውን ተጠራጣሪዎች ለራስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላል። የበጎነትና ታማኝነት ስብዕና የተላበሱ ሰዎችን ለማዘናጋት በቀላሉ ለመሸንገልና ለመደለል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል”
ይሄ ጠንካራ የሰባዊ መብት ታጋዮች ለነበሩ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቴች የተጻፈ ነው። የምናከብራቸውን ሰዎች  በስም እየጠራ አሞግሶ አደንዝዟቸዋል።
እዛው ገጽ 39 ላይ…
“የበላይነትን ከምናረጋግጥባቸው መንገዶች  መካከል አንዱና ዋንኛው ፕሬስ ሲሆን በቤተ እምነቶች፣ በቤተ መጻሕፍት፣ በትምህርት ቤቶችና በማህበራት ላይ አተኩሮ መሥራትም ሳይቀር ተጽዕኖ ማሳደሪያ ለዘብተኛ ኃይል ሆነው ይወሰዳሉ።
በማንኛውም ጊዜ አብሮን የሚሆን አካል አለን፤ የሚለውን ፅኑ እምነታቸውን ለማግኘትም ያበቃል። በተለይም ወዳጅና ጠላት የሚለየው በችግር ቀን ነው፤ ብሎ የሚያምነው ሕዝባችን ውስጥ ከነዕድፍ ተደላድሎ ለመቀመጥ በችግር ጊዜ መድረስን የመሰለ ጥሩ አጋጣሚ አይገኝም”
ይሄ አንቀጽ ምን ያህል በኃይማኖታቻችን ተጠቅሞ የራሱን አላማ ለማሳካት እንደሚቻል የተጻፈ ነው ይሄንንም በተግባር አይተነዋል። የእሱ ኃይማኖት ተከታይ ነቢያት ነን የሚሉ ቤተ መንግሥት በመግባታቸው ሲደሰቱ፣ ሙስሊሙንና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን በማስታረቅ ሰበብ ጠርንፎ መያዙን በግልጽ አይተናል ይሄ እንግዲህ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያለ ከሥር አባቱ ኦነግ ለሃምሳ ዓመት ያልቻለውን ነገር እሱ ግን ማደንዘዣ እየወጋ ሊያፈርሳት ጫፍ የደረሰው ሙሴያችን ሥልጣን ላይ ከመምጣቱ በፊት የጻፈው መጽሐፍ ነው።
ደራሲውና ዳይሬክተሩ እሱ ሲሆን ተዋንያኖቹ ደግሞ በእሱ ፍቅር የታወሩ፣ ከእሱ ሥልጣን ጠብ ይልናል ብለው የታወሩ ፓርቲዎች ደጋፊና ሆድ አደር ካድሬ ነው። ተመልካቹ ደግሞ በየቀኑ የመኖር ዋስትናውን የተቀማው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነውና።
Filed in: Amharic