ሀገር እንደሀገር እየቀጠለች ያለችዉ ጨዋ መንግስት ኖሮን ሳይሆን ጨዋ ህዝብ ስላለን ነዉ…. !
ድምፃዊ አብዱ ኪያር
አሁን የሀገራችን ፓለቲካ ከድጥ ወደማጡ እየሄደ ይመስለኛል። ዛሬ የጎበዝ አለቃ ከሀገር ከመንግስት በልጦ የከሌ ብሄር ከዚህ ዉጣ ብሎ ሲያሻዉ በስናይፐር ሲያሻዉ በገጀራ ሰዉ ሲገል ሲያርድ ይዉላል።
ህፃናት ይደፈራሉ ! ብሄራቸውን እንኳ መለየት የማይችሉ ህፃናት በብሄራቸው ምክንያት ይታረዳሉ
በአፍሪካ መዲና በአዱገነት ሰው በአደባባይ ሰው መገደል ተጀምሯል ! ሰው ተወልዶ ባደገበት እንደ ስደተኛ ተሳቆ እንዲኖር ሆኗል
መንግስት አንዴ የህዝብ ደራሽ ሌላ ግዜ የወንበዴ ጠበቃ ሆኖ ሲወላዉል ይዉላል። እንደ ኪስ ፓርሳ 2 ሚሊየን ብር ጠፋብኝ የሚል ባለስልጣን ክቡር ከሆነው የሰው ልጅ ይልቅ የአበባ መሰረቅ የሚንገበግባቸው ባለስልጣናት ወንበሩ ላይ ተሰይመዋል።
ዘር መርጦ ቤት የሚያድል ዘር መርጦ ሀውልት የሚያቆም የመንግስት ግዙፍ ባለስልጣናት የለት ተዕለት ስራ ከሆነ ቆየ።ባገርና በህዝብ ቁማር መበላላት እመንግስት ቤት ያለ መደበኛ ስራ ሆኖ እንደዝና ይወራል።
እኔ ማንንም ወቅሼ ማንንም የማወደስ ሞራል የለኝም።በቃ መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች ሀገርን ረስተዉ ለተራ ጎጥ እየተራወጡ ነዉ።በመሀል ትልቁ ምስል ሀገር ጠፍቷል ፣አለም አቀፍ ክብርና ዝና ጠፍቷል፣ሉዐላዊነት ተደፍሯል ከሁሉ በላይ ህዝብ ተበድሏል።
ሀገርም እንደሀገር የቀጠለችዉ ጨዋ ተቃዋሚ ወይም መንግስት ኖሯት ሳይሆን ጨዋ ህዝብ ስላላት ነዉ።