የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው ጅምላ ጭፍጨፋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል። ጨፍጫፊው ኦሕዴድ/ብልፅግና መሆኑንም ድርጅቱ በግልፅ አመላክቷል። ከጭፍጨፋው አስቀድሞ አማሮች ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ በኦሮሚያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተነገራቸው መሆኑንም ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
በአጣየ፣ በከሚሴና ከጎራባቾቻቸው በአማራው ላይ አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ መፈፀሙን የጠቀሰው መኢአድ ካሳለፍነው ሳምንት መግቢያ ጀምሮ እስከያዝነው ሳምንት ድረስ በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ፤ ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ መንግሥታዊው የኦሮሙማ የሽብር ቡድን አማሮችን በጅምላ እየጨፈጨፈ መሆኑን አብራርቷል። በዋናነት የወንጀሉ ፈፃሚዎች የኦሮሚያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። ጥቃቱን ለማስቆም ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጋር እየሠራ መሆኑን የገለፀው መኢአድ
ተከታዮችን ስድስት ጥሪዎች አቅርቧል፦
1ኛ.በተፈፀመባቸው ጥቃት ወገኖቻቸውን ላጡና ችግር ላይ ለወደቁ ወገኖቻችን መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
2ኛ.እስካሁን ድረስ በአማራው ላይ ጥቃት በተፈፀመባቸው ሁሉም ክልሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተሳተፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ መንግስት አመራሮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
3ኛ.የኦሮሚያ ብልፅግና የሚመራው መንግስት በአማራው ላይ የሚፈፀመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ለማስቆም ፍላጎት የሌለውና በአማራው ህዝብ ጥላቻ የናወዘ መሆኑን በመረዳት በየትኛውም የሀገሪቱ ጥግ የሚኖር አማራ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ራሱን አደራጅቶ ከሚሰነዘርበት ጥቃት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡
4ኛ.ጥቃት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግስት ተገቢውን ክትትል፣ ካሳ እና የመልሶ ማቋቋሚያ እገዛ እንዲያደርግላቸው፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት ውስጥ አስላጊውን እርብርብ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
5ኛ.የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ወዳጅ ሀገራት በሙሉ በአማራው ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት እንድታወግዙና በመንግስት ላይ ተገቢውን የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ በማሳደር የፌደራል መንግስትም ሆነ የክልል ባለሥልጣናት በአለም አቀፉ የወንጀል ሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ በአስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞቹ ለፍትህ እንድትቀርቡ እንድታደርጉ ስንል እንጠይቃለን፡፡
6ኛ.መላው የሀገራችን ሕዝብ በዘር፣ በኃይማኖት፣ በብሔር ሳንከፋፈል በአንድነት ፀንተን እንድንቆምና በአማራው ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመከላከል የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንድንገነባ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን፡፡
"አማራን በጅምላ እየጨፈጨፉ ያሉት የኦሮሚያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው.. !!!" መኢአድ
Filed in: Amharic