>
5:33 pm - Saturday December 5, 7007

የዘኪን ነገር .... ነጭ ነጯን ስንነጋገር …  !!! (ዘመድኩን በቀለ)

የዘኪን ነገር …. ነጭ ነጯን ስንነጋገር …  !!!

ዘመድኩን በቀለ

  ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ

  የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ 


 

… ሲጀመር እነሱ የሚፈልጉት ድሀን ማጽዳት፣ ማጥፋት፣ ማስወገድ።
 
* እነሱ የሚፈልጉት ድሀን ማፈናቀል፣ ማባረር፣ መዝረፍ።
*  እነሱ የሚፈልጉት ደሀን ማሳዘን፣ ማስለቀስ፣ ማንገብገብ። 
* እነሱ የሚፈልጉት ደሀን ማስራብ፣ ማንከራተት፣ ገድሎ በግሬደር በአንድ ጉድጓድ መቅበር።
*  እነሱ ሚፈልጉት ደሀን እስላም ቢሆን ኦርቶዶክስ አስርበው፣ አደህይተው፣ አማራጭ፣ ምርጫም አሳጥተው መሄጃ መድረሻ ሲያጣ፣ ሲጨንቀው እምነቱን በሆዱ እንዲቀይር ማድረግ።
* *  እሱ የሚፈልገው ድሀን መሰብሰብ፣ ማጠብ፣ ማቀፍ። 
* * እሱ እና እነርሱ እንደምን ይግባቡ? ፣ ያለ ተፈጥሯቸው??? አልተግባብቶም አለ ያገሬ ሰው
… ሲቀጥል ዘካርያስ በዘሩ ትግሬ ነው። ይሄን ያዙልኝ። ከዚያም ሲቀጥል ዘኪ የጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው። ያውም የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል የሃይማኖት ፍሬ ነው። እናም ስለሁለቱ ምክንያት ዘካሪያስ ኪሮስ ይሀን የመሰለ የበጎ አድራጎት ሥራ እንዲሠራ አይፈቀድለትም። ሥርዓቱ አይፈቅድለትም። አንደኛ ነገር ኢትዮጵያዊ ትግሬ መሆኑ፣ ሁለተኛው ነገር ደግሞ የተዋሕዶ ልጅ ባለማዕተብ መሆኑ የአገዛዙ መንፈስ አይቀበለውም።
… አብዶ፣ መሮት፣ ራሱን እያጠፋ ከከተማዋ ይጠፋ ዘንድ የተፈረደበትን ደሃ ሰብስቦ ማብላት፣ ማጠጣት ማለት በእነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ ወንጀል ነው። ልክም አይደለም። በኮሮና ተጋፍቶ ይረግፍ ዘንድ ቀመር የተሠራለትን ደሃ 24/7 365 ቀናት ሙሉ ውኃና ሳሙና አዘጋጅቶ አላፊ አግዳሚው እጁን ይታጠብ ዘንድ ሲወተውት መዋሉ ለእነሱ የሞት ድግስ እንቅፋት እኮ ነው። አናም የእነ ዐቢይ የብልፅግና ወንጌል፣ የእነ አዳነች አቤቤ የብልጽግና ወንጌል ደሃ ጠል ስለሆነ ከዘኪ እምነት እና ተግባር ጋር ይጋጫል። እናም ዘኪ መከልከሉ የሚጠበቅ ነው።
… እነሱ ከወለጋ፣ ከመተከል፣ ከኦሮሚያ እያፈናቀሉ፣ እየገደሉ፣ እያጸዱ ያባከኑትን፣ ያቅበዘበዙትን፣ መድረሻም ያሳጡትን ህዝብ ዘኪ ጠዋት ጠዋት ሻይና ዳቦ፣ አንዳንዴ፣ እንጀራ፣ አንዳንዴ ሩዝና መኮረኒ እያፈራረቀ እየመገበ ተስፋ ሲሰጣቸው ሲያዩ መንፈሳቸው ይታወካል። በረሃብ መርገፍ ያለበት ዜጋ እንዴት ነፍሱን ማቆያ ዳቦም ቢሆን ይመገባል? ይሄ ዕቅዳቸውን ያጨናግፋል። ስለዚህ ዘኪን መከልከል አለባቸው። ከለከሉትም።
… አሁን ያለው የኦሮሞን ህዝብ እወክላለሁ የሚለው ኦህዴድ ሸኔ ፓርቲ በገጠር በጥይት፣ በካራ፣ በድንጋይ፣ በሜንጫና በዱላ እየቀጠቀጠ ዜጎችን ማስወገድ፣ በከተማ ያሉትን ደግሞ በጭንቀት፣ በኑሮ ውድነት፣ በማፈናቀል በማሳበድ ማጽዳት ነው የተያያዘው። ታስታውሱ እንደሆነ #ወለተ_ኪዳን የምትባል አንዲት የወልድያ ልጅ ከመተከል የተፈናቀሉ አገው ዐማሮችን በተጠለሉበት ሥፍራ ጎጃም ቻግኒ ድረስ በመሄድ ስትራዳቸው፣ ስትረዳቸው፣ መኮረኒ እየቀቀለች፣ ወጥ እየወጠወጠች፣ እንጀራ እየጋገረች ስታበላቸው፣ ስትመግባቸው ያየው የስደተኞቹ ወገን የሆነው ራሱ ብአዴን፣ ጎጃሜው በአስቸኳይ ነው ያባረራት። ማባረር ብቻ አይደለም የስደተኞቹ ቀለብ ተከዝኖበት የነበረውን መጋዘን ነው እሳት የለቀቁበት። እናም አዲስ አይደለም በጎሥራን ማደናቀፍ መከልከል።
… ዘኪ ትግሬ ባይሆን፣ ዘኪ ባለማዕተብ ባይሆን፣ ዘኪ ኦሮሞ ቢሆን በኦሮሞነቱ ላይ ደግሞ ጴንጤ ቢሆን ብላችሁ አስቡት። አቢቹ ለመልካም ወጣት ብሎ ከኖቤል ሽልማቱ ብር ላይ፣ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ በጀት ላይ ቦጭቀው ይሰጡት ነበር። ራዲዮ ፋና ዜና፣ ኢቲቪ ዶክመንተሪ ሁላ ይሠሩለት ነበር። እነ ሶፊያ ሽባባው መዝሙር በጎዳናው ላይ ይዘምሩለትም ነበር። መሬት ሁላ ይሰጡት ነበር። ምንያደርጋል ታዲያ ዘኪ በዘሩ ትግሬ ሆነ፣ በሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ። አከተመ።
… ያልበላንን አንከክ። ያልተጻፈ አናንብብ፣ አጉል ዲፕሎማት አንሁን፣ ሚዛናዊ ጸሐፊ፣ ሚዛናዊ ሃሳብ አቅራቢ ለመሆን አንላላጥ። እውነቷን እንጋፈጥ። ነጭ ነጯንም እናውራ፣ ከዚያ የመሸበት እንደር። አጉል አዛኝ ቂቤ አንጓቾችም አንሁን። ቢመራችሁም፣ ቢያንገሸግሻችሁም የእኔ እውነት ይሄው ነው። አዎ የኦሮሞ ብልጽግና ወንጌል ድሆችን ከገጠር ከከተማ፣ ከሃገር ሳያጸዳ እረፍት ብሎ ነገር አይኖረውም። እግዚአብሔር አላቸው እንጂ የሚያሳዝኑኝስ ያቺን ዳቦ በሻይ ቀምሰው የቲቢ መድኃኒት የሚውጡት ድሆች ናቸው።
… ዘኪዬ ወንድሜ ትግሬ ባትሆን ኖሮ ይሄ አይደርስብህም ነበር። የተዋሕዶ ልጅ ባለማዕተብ ባትሆን ኖሮም ይሄ አይደርስብህም ነበር። እናም በፖሊሶቹም አትዘን። ዐማራነትና ትግሬ መሆን ወንጀል በሆነበት ዘመን የተፈጠርክ ስለሆነ አይታዘንም እንጂ፣ አንተ ወደህ ባላመጣኸው ማንነት አይሸማቀቁም ማዘንስ ትግሬ በመሆንህ፣ ማዘንስ የተዋሕዶ ልጅ በመሆንህ ነው። ለምሳሌ ፓስተር ዮናታንን አክሊሉ ዐማራ ነው። ነገር ግን የብልጽግና ወንጌል አማኝ ስለሆነ የንጉሥ ያህል ተከብሮ ነው የሚኖረው። አየህ ዐማራ ትግሬ መሆን ብቻ ሳይሆን ዐማራ ትግሬም ሆነህ የእነሱ እምነት ተከታይ ብትሆን 20 ሺ ካሬ መሬት ከብዙ ሚልዮን ብር ጋር ይሰጡህ ሁላ ነበር።
… እኔ ግን እልሃለሁ። ወንድም ዓለሜ ። ትግሬነትህን አትሸማቀቅበት። ከፍከፍ አድርገህ ያዘው። አትበሳጭ፣ ማዕተብክንም አጥብቀው። እንዳታላላው። በተለያየ መንገድም የበጎ አድራጎት ሥራ መሥራት ስለሚቻል ነገ የኢትዮጵያ የእውነት ፀሐይ ወጥቶ ይሄ ሁሉ ኮተት እስኪወገድ በመንገድህ ሂድ፣ ጽና፣ በርታ፣ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም በምልጃዋ ከአንተ ጋር ትሁን። አምላከ ቅዱስ ራጉኤል ይጠብቅህ። የድሆች አምላክ፣ የእማማ ዝናሽ አምላክ፣ እርሱ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳህ። ከአንተ ጋርም ይሁን።
… ምን አልባትም በሥራ ሂደት የሳትከው ነገር ካለና እግዚአብሔር ያልወደደልህ ያስቀየምከው ነገርም ኖሮ ፈቃዱን ከነሣህም ንስሐ ግባ ዘኪዬ። ይሄም ምክሬ ነው። በምትሠራው በጎ ተግባር በዚህች ምድር ላይ እሸለማለሁ ብለህ ግን እንዳትጠብቅ።
ሻሎም  !  ሰላም  ! 
መጋቢት 30/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ
Filed in: Amharic