>
5:30 pm - Wednesday November 1, 0445

" ትግራይ እስከመቼ ነው የጦር ካምፕ ሆና የምትቀጥለው???"

” ትግራይ እስከመቼ ነው የጦር ካምፕ ሆና የምትቀጥለው???”

 
*….ሰሚ ያጣ ጩኸት ህወሓት ከአዲስ አበባ ጠራርጎ በመውጣት መቀሌ ገብቶ እንደመሸገ ከተደረገ ስብሰባ ላይ የተወሰደ የአንድ አባት ንግግር ትርጉም
*…. ኤርትራውያን ወንድሞቻችን ናቸው :: አይደለም ባድመን ሌላ ሰጥተን ሰላም እናድርግ :: የበለጠ ነገር እናገኛለን :: ስለዚህ የኤርትራ ጉዳይ ከተፈታ : የትግራይ ሕዝብ ከችግር ይወጣል….!

 

እዚህ ችግር ውስጥ የከተተን የኤርትራ ጉዳይ ነው :: ትግራይ ለ100 ዓመት : የወታደር ካምፕ : እንድትሆን ተደርጎ ተቀመጠች :: ዛሬ የገበሬዎቻችን መሬት በታንክ ሲታረስ ይውላል :: ሻዕቢያ ጦርነት ከጀመረ : የተዘራ እህል : የታረሰ መሬት : በታንኮች ነው የሚወድመው :: ለምንድን ነው የትግራይ ሕዝብ የወታደር ካምፕ ተደርጎ የሚቀመጠው : ምን አድርጎ ነው ? እመኑ አትመኑ : ዛሬ በትግራይ : ከአንድ  ነጥብ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ  :  በርሐብና በችግር ውስጥ አለ ::  ሒዱ ማእከል ትግራይ : ሒዱ ተንቤን አካባቢ : ሱቆችና መጋዘኖች ( wear house ) ተሰርቶ : የበሰበሰ የአሜሪካን ስንዴ : እንካ ውሰድ እየተባለ : ሕዝባችን ይሰቃያል ያለው :: ሕዝባችን : ቅዳሜ :ቅዳሜ : በሰልፍ ተሰልፎ : እንኳን ግማሽ ኩንታል ሊያገኝ ቀርቶ : እዛ ተሰልፎ ነው የሚውለው :: ነገር ግን ረሃብ የለም ይባላል :: እዚህ በpower point  የተደገፈ : እነ አባይ ወልዱ መጥተው የሚያሳዩንን አይተን  : እናጨበጭብ ነበር :: ሆኖም : ሁሉም ነገር ውሸት ነው ::  ትግራይን ሔዳችሁ እይዋት : እንደ ትግራዋይ ሕዝባችን ምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ሔደን እንየው ::  በዚህ በጦርነት : በዚህ በወታደር : በዚያ ወታደሩ የሚያደርገው ያለው : :
የኤርትራ ጉዳይ መፍትሔ ( solution ) : ለማምጣት አስቡ :: ኤርትራውያን ወንድሞቻችን ናቸው :: አይደለም ባድመን ሌላ ሰጥተን ሰላም እናድርግ :: የበለጠ ነገር እናገኛለን :: ስለዚህ የኤርትራ ጉዳይ ከተፈታ : የትግራይ ሕዝብ ከችግር ይወጣል :: ካልሆነ ግን ትግራይ ከ20 አመት በላይ የወታደራዊ ካምፕ ሆና እየኖረች ነው :: ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ልንገፋበት ይገባል  :: ስለዚህ ፅናቶች ልትገፉበት ይገባል : እኛም እዚህ ያለነው ተጋሩ : እዚህ ያለው ወታደራዊ ካምፕ በቶሎ ከትግራይ መውጣት አለበት :: ለወታደሮቹ እረፍት እየተባለ ይሰጣል : የት እንደሚውሉና የት እንደሚያድሩ ሁላችንም እናውቃለን :: ሕዝባችን ምን ያህል እየተጨመላለቀ እንደሆነ በአይናችን አይተናል :: ስለዚህ በአቸኳይ ሊፈታ የሚገባው ጉዳይ ነው ወንድሞቼ ::
Filed in: Amharic