>

ኦሮሞነትን ያስገፋዉ ኦሮሞ ነዉ...!!! (አርቲስት ጃምቦ ጆቴ)

ኦሮሞነትን ያስገፋዉ ኦሮሞ ነዉ…!!!

አርቲስት ጃምቦ ጆቴ

* … ዛሬ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ የሚል አካል ንፁሀንን እያረደ ህፃናትን እየጨፈጨፈ ማውገዝ ካልቻልን  ! ኦሮሞ ገዳይ ነው ብለው በአደባባይ ቢናገሩ እነሱን የመውቀሱ የሞራል ስብእና አይኖረንም!
 
ብዙ ሰዉ ኦሮሞነት ከፍ እንዳይል የተደረገዉ  ኦሮሞ ባልሆኑ ሰወች ክፋት ይመስለዋል፡፡ ይሄ ፈፅሞ የተሳሳተ እሳቤ ነዉ፡፡ ኦሮሞነት ሀገራዊ እሳቤ እንዳይዝ የሆነዉ ከኦሮሞ መሀፀን ተወልደዉ ለኦሮሞ ከልክ በላይ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ሰዎች ነዉ፡፡
 እነዚህ አካላት አዲስ አበባ የኦሮሞ ብቻ ናት ብለዉ ሲቀሰቅሱ ለኛ አስበዉ ያስመስሉታል፡፡ ለዘመናት ከሁሉም አቅጣጫ በመጣ ስብጥር ህዝብ የተገነባን ከተማ ለብቻዬ ልዉሰድ ስንል ሌላዉ ብሄረሰብ ምን ይላል ብለን ማሰብ አለብን፡፡ እንደዚህ አይነት እሳቤን ማስተጋባት ኦሮሞ የኔ ብቻ እንጂ የኛ የሚል ነገር የለዉም ብሎ ለሌላዉ መንገር መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ይሄ የሞ ጠቃሚ አይደለም፡፡
ኢሬቻን በፍቅር አክብረን ሌላዉ ህዝብም አብሮን በፍቅር እንዲያከብር መጋበዝ ሲገባ ክፉወች ግን ሌላዉን አብረን እኛ ብቻ እናክብር ብለዉ ቀሰቀሱ ፡፡በፍቅሩ በዐል ጥላቻ በይፋ ተሰበከበት ፡፡ዛሬ ኢሬቻ በፍቅር ሀሉም የሚያከብረዉ በዐል ሳይሆን ሌላዉ ብሄር ባልመጣ የሚለዉ ኦሮሞ ለብቻዉ ሊፎክር የሚወጣበት በአል ነዉ፡፡
ዛሬ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ የሚል አካል ንፁሀንን እያረደ ህፃናትን እየጨፈጨፈ ማውገዝ ካልቻልን  ! ኦሮሞ ገዳይ ነው ብለው በአደባባይ ቢናገሩ እነሱን የመውቀሱ የሞራል ስብእና አይኖረንም
ኦሮሞነትን መዉደድ እና ኦሮሞን በመጥፎ ማስፈረጅ ይለያያሉ፡፡ ለኛ የተቆረቆሩ መስለዉ እኛን ብቻችንን አስቀርተዉ ክፉ የሚያስብሉንን መታገል አለብን፡፡
Filed in: Amharic