>

ጀግናው አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በ104 ዓመታቸው በሞት ተረቱ! (ጴጥሮስ አሸናፊ)

ጀግናው አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በ104 ዓመታቸው በሞት ተረቱ! 

ጴጥሮስ አሸናፊ

አንጋፋውና የሩጫ ትራኩ ጀግና አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በ104 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል።
አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ የተወለዱት በ1909 ዓ/ም በቀድመሞው ሸዋ ከፍለ አገር በመናገሻ አውራጃ ሱሉልታ ወረዳ በአካኮና መናበቹ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነበር። ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በተለያዩ የሩጫ መድረክ ላይ አገራቸውን ያስጠሩበት ድል አስመዝግበዋል። ከነዚህ መካከል በ1ሺ500፣ 3ሺ፣ 5ሺ፣ 10ሺ፣ 21 ኪሜ፣ 25 ኪሜ፣ በ32 ኪ.ሜ በአገር አቋራጭ እና የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ላይ በመሳተፍ 51 የወርቅ፣ 44 የብር እና 30 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ማገኘት ችለዋል። ከዚህም ሌላ 21 ሰርተፍኬት፣ 4 ዲፕሎማ እና ከ40 በላይ ዋንጫዎችን ወስደዋል። በተለያየ ወቅትም የኢትዮጰያ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አስችለዋል። የሶምሶማ እሩጫ በአገራችን እንዲለመድ ለማድረገ ጥረት ያደረጉ መሆናቸውም ይነገርላቸዋል።
ነፍስ ይማር ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ!
Filed in: Amharic